African Leadership Excellence Academy
2.34K subscribers
2.55K photos
96 videos
6 files
119 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
የጠዋቱ ውይይት እንደቀጠለ ነው። አሁን ጊዜው የጥያቄ እና የአስተያየት ነው።
አቶ ታሪኩ ተረዳ ባነሱት ሀሳብ ላይ እንደገለጹት ሀብቶቻችንን በአግባቡ መጠቀም የምንችለው ያለንን ብዝሀነት በአግባቡ ማስተናገድ ስንችል ነው። የማንነት ጥያቄዎችንም በአግባቡ ለመፍታት አሉታዊ ትርክቶችን በሚያግባባ ገዥ ትርክቶች በማስተካከል ዕድሎችን በአግባቡ መጠቀም ያስፈልጋል። በብዝሀነት ውስጥ ያለውን አንድነት ማክበር ያስፈልጋል። አካታችነትን መሰረት ያደረጉ እንደ አድዋ ዜሮ ዜሮ ያሉ ፕሮጀክቶች አንድነትን የሚያጠናክሩ እና ብዝሀነትን የሚያከብሩ በመሆናቸው ሊበረታቱ ይገባል። በአማራ ክልል የተፈጠረውን የጸጥታ ችግር በውይይት ለመፍታት ጥረት መደረጉ የሚበረታታ ነው።
የጠዋቱ ውይይት እንደቀጠለ ነው። አሁን ጊዜው የጥያቄ እና የአስተያየት ነው።
አቶ አልአዛር ፈንታው በበኩላቸው አገራችን ለውጡን ካስተናገደች በሁዋላ ተስፋ ሰጭ የነበሩ ሁኔታዎችን በአግባቡ ባለመጠበቃችን እና ባለመንከባከባችን የሀዘን እና የችግር ጊዜ እያሳለፍን ነው። በየቦታው በሚፈጠሩ ችግሮች በበርካታ ወገኖቻችንን እያጣን ነው። ይህ እስከመቼ ነው የሚቀጥለው? በሲቪሊያን ላይ የሚደርሱ ሞቶች እና ጉዳቶች ያሳስቡኛል። ችግሮቻችንን ለመፍታት ትክክለኛው ጊዜ አሁን ነው። የሚከፈለውን የሰላም ዋጋ በመክፈል ወደ ሰላም ለመምጣት መስራት ይገባናል። ችግሮችን መሸፋፈናችን ዋጋ እያስከፈለን ነው። ከሩዋንዳ ብዙ መማር ይገባናል። ችግራችንን ለመፍታት ከዚህ የተሻለ ጊዜ ከየትም አይመጣም። ወጥቶ ለመግባት ስጋት ላይ ነን።
የኑሮ ውድነቱ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። መንግስት ትኩረት መስጠት ይኖርበታል። የዲፕሎማሲ ስራው ላይ መንግስት በስፋት በመስራት የዓለምን ሀሳብ መግዛት ይኖርበታል። የባህር ወደብ እንደሚያስፈልገን ቢታመንም ልናገኝ የሄድንበት መንገድ ሁሉንም የሚያግባባ መሆን አለበት።
የጠዋቱ ውይይት እንደቀጠለ ነው። አሁን ጊዜው የጥያቄ እና የአስተያየት ነው። አቶ አማረ በበኩላቸው ከዚህ ቀደም ሀገራችን አስያውያንን እና አፍሪካውያንን ትረዳ ነበር። አሁን ግን ሀገራችን ውስጥ ያለው ሰላም አሳሳቢ በመሆኑ ለሰላም ቅድሚያ በመስጠት መስራት ይገባል።
በየክልል መንግስታቱ ያለው ግንኙነት አንድነትን የሚተርክ ትርክት አላቸው ወይ? ወደ አንድነት የሚያመጡ ትርክቶች ላይ መስራት ችግሩን ሊፈታ የሚችል ይመስለኛል።
ሌብነት ዋነኛ መለያችን ሆኗል። መንግስት በሌቦች ላይ ተግባረዊ እና አስተማሪ እርምጃ ካልወሰደ በቀር ሌባ የማያፍርባት ሀገር እየፈጠርን ነው።
የጠዋቱ ውይይት እንደቀጠለ ነው። አሁን ጊዜው የጥያቄ እና የአስተያየት ነው።አቶ ሲሳይ ዘሪሁን ባነሱት ሀሳብ የግብርና ስራችን ላይ የሚመለከታቸው ሁሉ ምርታማነት ላይ ትኩረት ሰጥተው መስራት አለባቸው። ያለንን የውሀ ሀብትና የሚታረስ መሬት በአግባቡ ባለመሰራቱ የኑሮ ውድነቱ እየባሰ ነው። ምርታማነትን በሚያሳድጉ ስራዎች ላይ በመስራት የሀገራችንን ኢኮኖሚ ማሳደግ ይቻላል።
የውጭ ምንዛሪ እጥረትን ለመፍታትም የኢንዱስትሪው ሚና የላቀ በመሆኑ ትኩረት ተሰጥቶት ሊሰራበት ይገባል። የሰርቪስ ዘርፉም ሊሻሻል እና የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ሊደግፍ በሚችል መልኩ ሊሰራበት ይገባል።
የህግ የበላይነትን ለማስከበር መንግስት መስራት አለበት። የሰላም ችግሩ ከቤተሰብ አራርቆናል። መንግሰት ጥያቄ አለን የሚሉ እና ነፍጥ አንግበው ጫካ የገቡትን ወደ ጠረጴዛ ውይይት መጋበዝ አለበት።
የጠዋቱ ውይይት እንደቀጠለ ነው። አሁን ጊዜው የጥያቄ እና የአስተያየት ነው። አቶ አዲሱ ኡርጌሳ በበኩላቸው እናታችን ችግር ውስጥ ናት ግን ደግሞ በእናት ተስፋ አይቆረጥም። ተጋግዘን ሀገራችን ከገባችበት ችግር ውስጥ እንድትወጣ መስራት ይገባል። በሀገራችን ጨለማም ብርሀንም አለ ስለ ሁሉም በሚዛን ነው ማውራት ያለብን። ሁላችንም የመፍትሔው አካል መሆን አለብን።
የጠዋቱ ውይይት እንደቀጠለ ነው። አሁን ጊዜው የጥያቄ እና የአስተያየት ነው። አቶ ሲሳይ ከፍያለው በሰጡት አስተያየት ሰላም በንግግር ብቻ አይመጣም። የኢኮኖሚ ዕድገትም በንግግር ብቻ አይመጣም። ሁላችንም ወደ ተግባራዊ ሰላም እና የኢኮኖሚ ዕድገት እንድንመጣ ከመንግስት ጎን መቆም አለብን። ከፋፋይ ሀሳቦችን እና ትርክቶችን በመታገል ሀገራዊ አንድነታችንን ማጠናከር ይገባል። በተለያዩ መንገዶች ተደራጅተው ሰላማችንነ የሚያውኩትን በመለየት ለሰላም የድርሻችንን መወጣት ይገባል።
የጠዋቱ ውይይት እንደቀጠለ ነው። አሁን ጊዜው የጥያቄ እና የአስተያየት ነው። ወ/ሮ ዘውድ እሸት በበኩላቸው ሁሉም የሚጠበቅበትን ማድረግ አለበት። ባልተገቡ ድርጊቶች እና በአፍራሽ ሀይሎች ሴራ መጠለፍ የለብንም። ያለችን ሀገር አንድ ናት ሁላችንም ተደምረን ለሀገር ዕድገት እና ሰላም መስራት ይገባል። መንግስትን ደግፈን መቆም ቢያቅተን እንኳን ለውጡን እና የለውጡን ሀይሎች ባናደናቅፍ የሚል ሀሳብ አለኝ።
በውይይቱ ማጠቃለያው ላይ ተገኝተው ሀሳብ የሰጡት የፕሮግራም ዘርፍ ምክትል ርዕሰ አካዳሚ ተወካይ አቶ ጥላሁን አረጋ በበኩላቸው መንግስት ነጠላ ትርክትን በገዥ ትርክት ለመተካት እና አካታች የሆኑ ሀገራዊ ትርክቶች ላይ እየሰራ ነው። ሀገራዊ የኩራት ምንጮቻችንን እንደ ገዥ ትርክት በመውሰድ አዎንታዊ ተግባር ላይ በመሳተፍ ለሀገራችን ሰላም በጋራ ልንሰራ ይገባል ብለዋል።
ፍትሀዊ የኢኮኖሚ ዕድገቱን ለማረጋገጥም በስራው ላይ የሚጠበቅብንን በማድረግ ተስፋ ሰጭ ስራዎች ወደ ዳር እንዲደርሱ መትጋት ያስፈልጋል ብለዋል። የፖለቲካ፤ የማንነት፤ እና የፍትሀዊ ሀብት ክፍፍል ጥያቄዎች የሚፈቱበትን መንገድ መንግስት እየፈጠረ ነው። ህዝቡን ማዕከል ያደረገ የሰላም ማስከበር ስራ ለመስራት መከላከያ ሰራዊታችን እየሞከረ ነው። በየትኛውም ወገን ያለ አካል ለንግግር እና ለውይይት ራሱን ማዘጋጀት አለበት። መንግስት ሆደ ሰፊ ሆኖ ለሰላም ቅድሚያ በመስጠት የጀመረውን መንገድ አጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።
የአፍሌክስ ም/ርዕሰ አካዳሚ ወንድዬ ለገሰ (ዶ/ር) በበኩላቸው ከአካዳሚው አመራሮች እና ሰራተኞች ለተነሱት ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ምላሽ እና ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ሰላም የሁላችንም ናት በጋራ ልንጠብቃት ይገባል። ባለፉት ዓመታት ያጋጠሙንን ችግሮች ለመፍታት መንግስት ብዙ ርቀት ሄዷል። በውስጣችን ያሉ የተዛቡ የታሪክ አረዳድ እና ትርክቶች እንዲታረሙ መንግስት ገዥ እና ታላቅ አገራዊ ትርክት እንዲኖረን እየሰራ ነው ብለዋል።
በሀገራችን ያለውን የጸጥታ ችግር ለመፍታት መንግስት አሳታፊ የሰላም መንገዶችን እየፈጠረ ነው። ከታጣቂ ሀይሎች ጋር የሰላም ድርድር እና ውይይት ለማድረግ መንግስት ቁርጥ አቋም አለው። የኑሮ ውድነቱን ለመቅረፍም መንግሰት እየሰራ ነው ብለዋል።
ክላስተር አስተባባሪው እና ፕሮጀክት ዳይሬክተሩ ስለ አፍሌክስ ሪፎርም፤ ማስፋትና ሽግግር በተደረገላቸው ገለጻ አመስግነው ከአፍሌክስ ጋር አብረው ለመስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
በአመራር ልማት ፕሮግራሞቹ ቀረጻ ላይ ድጋፍ እንደሚያደርጉ የጠቀሱት ክላስተር አስተባባሪው ስቴፋን ሊድስባ Stephan Lidsba, cluster coordinater for climate change ሲሆኑ በሌሎች የአፍሌክስ ፕሮጀክቶች ላይ አብሮ ለመስራት ሰፊ ውይይት እንደሚያስፈልግ ጠቁመው በተለይም የሀሳብ ማመንጫ ማዕከላት ግንባታው ላይ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች በኩል ድጋፍ ማድረግ የሚቻልበት ዕድል እንዳለ ተናግረዋል።
አቶ ዛዲግ አብርሃ ከ ጂ አይ ዜድ (giz) የክላይሜት ቼንጅ ክላስተር አስተባባሪ ስቴፋን ሊድስባ Stephan Lidsba, cluster coordinater for climate change እና የኢነርጂ ልማት ፕሮጀክት ዳይሬክተር አል ሙዳቢር ቢን አናም Al Mudabbir Bin Anam, Project Director for Energising development ጋር ተወያዩ።
የአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ ከጂ አይ ዜድ ከከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር በአፍሌክስ ሪፎርም፤ ሽግግር እና ማስፋት ዙሪያ የተወያዩ ሲሆን የአካዳሚውን የሪፎርም (Reform)፤ የማስፋት (Scaling Up) እና የሽግግር (Transformation) ስራዎች ለሀላፊዎቹ አብራርተዋል።
ርዕሰ አካዳሚው እንዳብራሩት አካዳሚው ለኢትዮጵያ እና ለአፍሪካውያን የልህቀት ማዕከል ለመሆን እየሰራ እንደሆነ እና ይህንን ዓላማውን ለማሳካትም አራት የጠቅላላ እና ሰላሳ ሰባት ልዩ የአመራር ልማት ፕሮግራሞችን ቀርጾ በሶሰት ዓመት ውስጥ ለመፈጸም እየሰራ ነው ብለዋል።
አፍሌክስን የዓለም አቀፍ የኮንፈረንስ ማዕከል ለማድረግም ሱሉሉታን እንደ ዳቮስ የሚል ፕሮጀክት ተቀርጾ እየተሰራ እንደሆነ እና የኢትዮጵያ የልማት አጋሮችም ይህንኑ ዓላማ ለማሳካት በሚደረገው ጥረት ውስጥ ዓለም አቀፍ ስብሰባዎችን በአፍሌክስ ውስጥ እንዲያደርጉ አቶ ዛዲግ ጥሪ አቅርበዋል።
አፍሌክስ ለሚቀርጻቸው ጠቅላላ እና ልዩ የአመራር ልማት ፕሮግራሞችም ጂ አይ ዜድ የባለሙያዎች ድጋፍ እና ለሚገነቡ የሀሳብ ማመንጫ ማዕከላት የመሰረተ ልማት ግንባታ ድጋፍ እንዲያደርግ የጠየቁት አቶ ዛዲግ ከጂ አይ ዜድ ጋር በመሆንም የአፍሌክስን ሪፎርም፤ ማስፋትና ሽግግር እውን ማድረግ እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።
የባለስልጣኑ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ በሰጡት አስተያየት አፍሌክስ በአጭር ጊዜ ውስጥ የሪፎርም፤ የማስፋት እና ሽግግር ፕሮጀክት መቅረጹን አድንቀው፤ በአመራር ልማት ፕሮግራሙ ላይ ለመሳተፍ እና የባለሙያ ድጋፍ ለማድረግ ተቋማቸው ከአፍሌክስ ጎን እንደሚቆም ገልጸዋል።
የሀሳብ ማመንጫ ማዕከሉን በአፍሌክስ ውስጥ ለመገንባት ፈቃደኛ እንደሆኑ ጠቅሰው በአፍሌክስ የአመራር ሽልማት በኩልም የሲቪል ማህበረሰቡን አርአያዎች ለመሸለም ዝግጁ እንደሆኑም ተናግረዋል።
አቶ ዛዲግ አብርሃ ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ ጋር ተወያዩ።
ለዋና ዳይሬክተሩ እና ለም/ል ዋና ዳይሬክተሩ ስለ አፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ሪፎርም፤ ማስፋትና ሽግግር በርዕሰ አካዳሚው ሰፊ ገለጻ ተደርጎላቸዋል።
አፍሌክስ አፍሪካዊ ስያሜ እና ተልዕኮ ቢኖረውም የሚጠበቅበትን ያህል እየሰራ እንዳልሆነ የጠቀሱት ርዕሰ አካዳሚው በሪፎርም፤ ማስፋት እና ሽግግር ስራዎቹ ውስጥ ተቋሙ አፍሪካዊ መልክና ይዘት እንዲኖረው እየሰራን ነው ብለዋል።
አቶ ዛዲግ አያይዘውም አፍሌክስን የአፍሪካ የኮንፈረንስ ማዕከል ለማድረግ ሱሉሉታን እንደ ዳቮስ የሚል ፕሮጀክት መቀረጹን ጠቁመው ሸገር ሲቲን ከዳቮስ ከተማ ጋር በእህትማማች ለማስተሳሰር ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመሆን ስራ መጀመሩን ተናግረዋል። ባለስልጣኑ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎችን፤ ወርክሾፖችን፤ ሲምፖዚየሞችን እና ስብሰባዎችን በአፍሌክስ ውስጥ እንዲያደርግም ጋብዘዋል።
ለሲቪል ማህበረሰቡ የሚያገለግል የሀሳብ ማመንጫ ማዕከልም በአፍሌክስ ውስጥ በመገንባት የተሻለ ሀሳብ እንዲፈልቅ እና ችግሮችን ሊፈቱ የሚችሉ ጥናት እና ምርምሮች እንዲደረጉ አቶ ዛዲግ ግብዣ አቅርበዋል።
ባለስልጣኑ የሚመራቸውን እና የሚቆጣጠራቸውን የማህበረሰብ ድርጅቶችን በማስተባበር በአመራር ልማት ፕሮግራሞች በዲዛይን ቀረጻ፤ በአሰልጣኝነት እና በተመራማሪነት አፍሌክስን እንዲደግፍ አቶ ዛዲግ ጥሪ አቅርበዋል።
አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው ዕለት የተሰጠው ሹመት የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ሲመክሩበት ቆይተው የወሰኑት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን በ15ኛ መደበኛ ስብሰባው የተለያዩ ሹመቶችን ባጸደቀበት ወቅት ነው፡፡

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)÷ ፓርቲው ከበርካታ እጩዎች ውስጥ ባላቸው ልምድ ኢትዮጵያን ማገልገል የሚችሉ እጩዎችን ወደ ፊት ለማምጣት የወሰነበት መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

በተለይም ከተሿሚዎች ውስጥ ሁለቱ ከብልጽግና ፓርቲ አባል ውጪ መሆናቸው ለኢትዮጵያ ቅድሚያ የተሰጠበት እና ልምድ እና እውቀት ብቻ መስፈርት የሆነበት መሆኑን አውስተዋል፡፡

ከየትኛውም ፓርቲ ቢሆን ልምድና እውቀት ያላቸውን ወደፊት ማምጣቱ እንደሚቀጥልም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተናገሩት፡፡

የብልጽግና ፓርቲ ባለው የመተካካት ባህል የቀድሞ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከሥራ አስፈፃሚነታቸው በክብር መሸኘታቸውን ተናግረዋል።

ምክር ቤቱ በዛሬው ዕለት አቶ ተመስገን ጥሩነህ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር፣ አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንዲሁም ዶ/ር መቅደስ ዳባ የጤና ሚኒስትር ሆነው እንዲሾሙ የቀረበለትን ሹመት መርምሮ አጽድቋል፡፡