African Leadership Excellence Academy
2.34K subscribers
2.55K photos
96 videos
6 files
119 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
ኢትዮጵያ ወደ ተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲ ትግበራ ገባች
👍3
የ2016 ዓ.ም ሪፖርት፣የ2017 ዕቅድና የ100 ቀናት ዕቅድ ላይ ውይይት ተካሄደ::
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ከአካዳሚው ሰራተኞች ጋር በ2016 ዓ.ም ሪፖርት፣በ2017 ዕቅድና በ2017ዓ.ም የ100 ቀናት ዕቅድ ላይ ውይይት አካሄደ፡፡
የዕቅድ በጀት እና ለውጥ ስራ አመራር ዳይሬክተር አቶ ምትኩ ጫኔ በሪፎርም ማስፋት እና ትራንስፎረሜሽን ፕሮግራም አፈፃፀም፣ተቋማዊ የማሰፈፀም አቅም፣የሀብት አጠቃቀምና አገልግሎት አሰጣጥ አሰራር ማጎልበት ስራዎች አፈፃፀም፣ የአመራር ልማት ስራዎችን ማሳደግ፣የጥናት ምርምርና ማማከር ስራዎችን ማሻሻል፣ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ የመፍትሄ እርምጃዎች ላይ  ማብራሪያና ገለፃ አድርገዋል፡፡
አቶ ምትኩ የ2017 ዓ.ም ዕቅድ መነሻ ሁኔታዎች፣የዕቅዱ ታሳቢዎች፣ስትራቴጂያዊ አቅጣጫዎችና ግቦች፣የዕቅድ ዝግጀት ክትትል እና ግምገማ ላይም ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ዳይሬክተሩ የአፍሪካ አመራር ልህቀት  አካዳሚ የ100 ቀናት ዕቅድ ላይም ገለፃ አድርገዋል፡፡
በቀረበው ገለፃ ላይ በስራ አመራር ኦፕሬሽን ዘርፍ ም/ርዕሰ አካዳሚ ዶ/ር ወንድዬ ለገሰ  አወያይነት ከተሳታፊዎች በርካታ ጥያቄዎች እና አስተያየት ተነስተው ለጥያቄዎቹ ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
በመጨረሻም ክፍትት ያለባቸውን ስራዎች አሰራር አዘጋጅቶ መሰራት እንዳለባቸውና  የግምገማ ስራ ጠርቶ መሄድ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
የሥራ ባህል ሽግግር ማዕከል ለመገንባት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ::

#የአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ እና #የሥራና_ክህሎት_ሚኒስቴር በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ።

ስምምነቱን የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ እና የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ሙፈሪሃት ካሚል ተፈራርመዋል።


ሁለቱ ተቋማት በአራት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ በቅንጅት ለመስራት የተስማሙ ሲሆን የዘርፉን የአመራር ብቃት ለማሳደግ የሚያስችል የአመራር ልማት ፕሮግራም፣ የሥራ ባህል ሽግግር ለመፍጠር የሚያግዝ ማከል ግንባታ፣ ሥራ ፈጣሪዎችን ለማበረታታት እና ከስር ያሉትን የሚያተጋ የልህቀት ሽልማት እና በዘርፉ ያሉ ችግሮችን ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ለመፍታት እንዲቻል የጋራ ምርምር ሥራዎችን ለመስራት ተስማምተዋል።

የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዝደንት ዛዲግ አብርሃ በፊርማ ስነስርዓቱ ላይ እንደተናገሩት ስምምነቱ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ስራና ክህሎት ለመፍጠር የሚያደርገውን ተግባር የሚያግዝና ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር እንደሆነ ጠቅሰው በስምምነቱ መሰረት የአመራሮችን ብቃት የማሳደግ ሥራ ትኩረት ተሰጥቶት ይሰራል ብለዋል።

የዘርፉ ምሁራን እና ተመራማሪዎች ሀሳብ የሚያፈልቁበት የስራ ባህል ሽግግር ማዕከል ግንባታ አስፈላጊ መሆኑ ስለታመነበትም የመሰረት ልማት ግንባታው የስምምነቱ አንድ አካል እንዲሆንና በቅርቡም የመሰረት ድንጋይ የማኖር ስነስርዓት እንደሚፈፀም ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል::
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በበኩላቸው ስምምነቱ በሥራና እድል ፈጠራ ዘርፍ የተያዘውን ዕቅድ ከማሳካት ባለፈ ተወዳዳሪ የሰው ሀብት ልማት ማፍራት ላይ ያተኮረ መሆኑን ተናግረዋል።

በሥራ ዘርፉ ላይ ያሉ አስፈፃሚ አካላትን ለማብቃት እንዲሁም የሥራ ዕድል ፈጠራን የሚያግዝ ስልጠናዎችን ለማዘጋጀት ከአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ጋር እንደሚሰራ ጠቁመዋል።
በአካዳሚው ዕቅድ አፈፃፀም እና በ2017 ዓ.ም ዕቅድ ላይ ማብራሪያ ተሰጠ::

የአካዳሚው ፕሬዝዳንት አቶ ዛዲግ አብርሃ በተቋሙ የ2016 ዓ.ም ዕቅድ አፈፃፀም እና በ2017 ዓ.ም ዕቅድ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል::

ፕሬዚዳንቱ በዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በ100 ቀናት ዕቅድ ላይ ከተቋሙ አመራሮችና ባለሙያዎች ለተነሱት ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል ።

አቶ ዛዲግ እንደገለጹት በርካታ ዓለምአቀፍ እና የሀገር ውስጥ ተቋማት አካዳሚውን በገንዘብና በሀሳብ እየደገፉ  መሆኑን  ጠቅሰው ያለፈውን አመት አፈፃፀም መሰረት በማድረግ የ2017 ዓ.ም ዕቅድ በላቀ መልኩ እንዲፈፀም ሁሉም ዘርፎችና የስራ ክፍሎች የተሻለ የዕቅድ አፈፃፀም እንዲመዘገብ በቁርጠኝነት መስራት እንዳለበት አሳስበዋል ።

በተያያዘ ዜና በአገልግሎት አሰጣጥ ዙርያ ስልጠና ተሰጥቷል።

የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ  ለተቋሙ አመራሮች እና ሠራተኞች በአገልግሎት አሰጣጥ ዙርያ ሱሉልታ በሚገኘው የተቋሙ አዳራሽ ስልጠና ሰጠ።

የፕሮግራም ዘርፍ አስተባባሪ ዶ/ር እሸቴ አበበ እንደተናገሩት የስልጠናው ዓላማ የስልጠና ተግዳሮቶችን ለመለየት ደንበኛ እና የደንበኞች አገልግሎት ለመለየት እና የአፍሪካ አመራር ልህቀት የአገልግሎት አሰጣጥ ልክ እንደስሙ የላቀ ለማድረግ መሆኑን ገልፀዋል ።

ዶ/ር እሸቴ የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቫንት ባህሪ እና ባለ ጉዳይ ላይም ማብራሪያ ሰጥተዋል።
👍2
#AFLEX_Environmentally_Friendly_Academy
We are determined to keep our environment sustainable and friendly. We have established a treatment plant and recycled the water for our nursery garden and for the neighborhood community as a way of Corporate Social Responsibility.
አካዳሚው 27 ከሚሆኑ ተቋማት ጋር በመቀናጀት በሁለት ዙር የSpecialization Leadership Development Program ስርዓተ ስልጠና (curriculum) እንዳዘጋጀ የሪፎርም ኮሚቴ አስተባባሪው ሞገስ ሎጋው (ዶ/ር) ገለጹ። አቶ ሙሉነህ አባተ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የትምህርትና ስልጠና ቡድን መሪ ናቸው። የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ለሚያዘጋጀው የJudiciary Specialization Leadership Development Program ስርዓተ ስልጠና (curriculum) ተቋማቸውን ወክለው ተገኝተዋል። ያላቸውን ዕውቀትና ልምድ ይዘው በስርዓተ ስልጠና (curriculum) ቀረጻው ላይ ሙያዊ አስተያየቶችንና ምክሮችን ሲያቀርቡ ነበር። አቶ ሙሉነህ እንደገለጹልን አካዳሚው የተሟላ የአመራር ልማት ፕሮግራም ማዕቀፍ ለማዘጋጀት በሚያደርገው ተግባር ውስጥ ባለድርሻ አካላት መካተታቸው ምሉዕ የሆነ የስርዓተ ስልጠና ሰነድ ለማዘጋጀት መደላድል እንደሚፈጥር ያምናሉ።
በተለይም ደግሞ የፍትህ ዘርፉን አመራር አቅም በተቀናጀ እና በተደራጀ መልኩ ለመገንባት የሚያስችል ስርዓተ ስልጠና (curriculum) መዘጋጀቱ፤ ለዘርፉ የሚኖረው ፋይዳ በቀላሉ የሚገለጽ እንዳልሆነ የሚጠቅሱት አቶ ሙሉነህ፤ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ስር ላሉ ሶስት ፍርድ ቤቶችና ተጠሪ ተቋማት አመራር አቅም ግንባታ ላይ መስራት የሚገባ ከሆነ የስርዓተ ስልጠና (curriculum) የሚኖረው ሚና ከፍተኛ ነው። ስለ ስርዓተ ስልጠና ምንነት እና አዘገጃጀት ገለጻ ከመስጠት ጀምሮ በቡድን መንፈስ ለመስራት የነበረው ሂደት አዳዲስ ዕውቀቶችንና ልምዶችን እንዲያገኙ እንዳስቻላቸው ተናግረዋል።
👍2