African Leadership Excellence Academy
2.34K subscribers
2.55K photos
96 videos
6 files
119 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ ከማዕድን ሚኒስትሩ ኢ/ር ሀብታሙ ተገኝ ጋር ተወያዩ::

ፕሬዚደንቱ ለማዕድን ሚኒስትሩ እና ለሚኒስትር ዴኤታዎች አካዳሚው በሶስት ዓመት ውስጥ ስለሚተገብራቸው የአመራር ልማት ፕሮጀክቶች እና የሪፎርም ፕሮግራሞች ገልፃ አድርገዋል::

አቶ ዛዲግ በውይይቱ ላይ እንደጠቀሱት፤ በአካዳሚው የለውጥ፤ የማስፋት እና የሽግግር ስራዎች ውስጥ ሁሉን አቀፍ እና አካታች የአመራር ልማት ፕሮግራም መነደፉን አስታውሰው፤ በጠቅላላ (General) አራት እና በልዩ (Specialized )ሰላሳ ስምንት የአመራር ልማት ፕሮግራሞች ተቀርጸው ወደ ስራ እንደተገባና ለሁሉም ፕሮግራሞች ማስፈፀሚያ የሚሆን ከ2,500 በላይ ገፆች ያሉት ዝርዝር ስትራቴጂ እንደተዘጋጀም አብራርተዋል::

በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ ውስጥ ተራርቀውና ተነጣጥለው ያሉ ተቋማትን እና መሪዎችን እንደ ድልድይ ሆኖ ለማገናኘት ሰፋፊ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሆኑም አቶ ዛዲግ ተናግረዋል።

ፕሬዚደንቱ አያይዘውም የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ከበርካታ ዓለምአቀፍና የሀገር ውስጥ ተቋማት ጋር በትብብር እየሰራ እንደሆነ ጠቅሰው፤ ከማዕድን ሚኒስቴር ጋርም በአመራር ልማት ፕሮግራም፤ በአመራር የልህቀት ሽልማት፤ በሀሳብ ማመንጫ ማዕከል ግንባታ እና በጥናትና ምርምር ዘርፎች አብረው መስራት እንደሚፈልጉ ተናግረዋል::

የማዕድን ሚኒስትሩ ኢ/ር ሀብታሙ ተገኝ በበኩላቸው፤ አፍሌክስ በሶስት ዓመታት ውስጥ ሊሰራ ያቀደው እና ፕሬዚደንቱ ዕቅዱን ያቀረቡበት መንገድ ከአፍሌክስ ጋር ለመስራት የሚያነሳሳ መሆኑን ጠቅሰው፤ አካዳሚው በአመራር ልማት ዘርፍ የሰነቀው ራዕይ ከተቋም ግንባታ ባሻገር ለሀገርና ለአፍሪካ ብልፅግና የሚኖረው ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል::
👍2
የማዕድን ሚኒስትሩ ኢ/ር ሀብታሙ ተገኝ አካዳሚው የሚሸጥና ዋጋ የሚያወጣ ሀሳብ ይዞ እንደቀረበ ጠቅሰው፤ ፕሬዚደንቱ ያቀረቡትን የአብረን እንስራ ጥያቄ በደስታ መቀበላቸውን ተናግረዋል::

በውይይቱ ላይ የተሳተፉ ሚንስትር ዴኤታዎችም በሰጡት አስተያየት፤ አካዳሚው ከተሰጠው ተልዕኮ አንጻር የቀረጸው የሶስት ዓመት ስትራቴጂ እና ሁሉን ዓቀፍ የሆኑ የአመራር ልማት ፕሮግራም ማዕቀፎቹ በታቀደው ልክ ተግባር ላይ ከዋሉ የሀገራችንን የአመራር አቅም በማጎልበት የመፈፀም አቅም እንደሚያሳድግ ተናግረዋል።

ሁለቱ ተቋማት በጋራ ሊሰሩ የሚችሉባቸውን ዘርፎች ለይቶ ሰነድ የሚያዘጋጅ ኮሚቴ ተቋቁሞ ውይይቱ ተጠናቋል::
የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ምክክር በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ
**************************************

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ የውይይት መድረኮች ሀገራዊ ችግሮችን በጋራ ለመፍታትና የዳበረ የዴሞክራሲ ስርዓት ለመገንባት ጥሩ መሰረት የሚያኖር መሆኑን የፖለቲካ ፖርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ገለጸ።

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላት በወቅታዊና ዋና ዋና ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ውስጥ ምክክር አድርገዋል።
የአፍሪካ የአመራር ልህቀት አካዳሚ አመራሮችና ሠራተኞች አረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ።
የአፍሪካ የአመራር ልህቀት አካዳሚ አመራሮች፣ ሰራተኞችና በሸገር ከተማ የመና አቢቹ ክፍለ ከተማ አመራሮችና ማህብረሰቡ በአፍሌክስ የአመራር ልማት ማዕከል ውስጥ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሂደዋል፡፡
በመርሃ ግብሩን ላይ ንግግር ያደረጉት በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የስራ አመራር ዘርፍ ምክትል ርዕሰ አካዳሚ ወንድዬ ለገሰ (ዶ/ር)፤ በኢትዮጵያ የአረጓዴ ኢኮኖሚን በማሳደግ የዜጎችን የምግብ ዋስት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ በአረጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አረጓዴ ኢኮኖሚን እየገነባች ነው ያሉት ምክትል ርዕሰ አካዳሚው የአፈር መሸርሽርን ፣ የአየር ንብረት ለውጥን የመከላከል፣ ምርትና ምርታማነትን የማሳደግ፣ ለምግብ የሚያገለግሉ ፍራፍሬዎችን መጠንና ምርት በማሳደግ ብልፅግናን እውን የማድረግ ስራ እየተሰራ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የአፍሪካንና የሀገር ውስጥ አመራሮችን በአመራር ልማት ፕሮግረም ብቁ ከማድረግ ባለፈ ሱሉሉታ በሚገኘው የአመራር ልማት ማዕከሉ ውስጥ 50 ሄክታር መሬት ላይ የተለያዩ የልማት፣ የአረጓዴ ልማቶችን፤ የአፈር ጥበቃ ስራ የመስራት ላይ እንደሆነም ወንድዬ ለገሰ (ዶ/ር) አብራርተዋል፡፡
በ2016 በጀት ዓመት አራት ሄክታር መሬት ላይ የነበረን የባህር ዛፍ ደን በማጽዳት መሬቱን የማከም፤ እርከን የመስራት ተስራ ተስርቷል፤ የታከመውንና እርከን የተሰራበትን መሬት በፍራፍሬ ተክሎች ለመሸፈን እየተሰራ ነው ያሉት ወንድዬ ለገሰ (ዶ/ር)፤ ሀምሌ 15 ቀን 2016 ዓ.ም ሶስት ሺህ የአፕል ችግኞችና ሌሎች ፍራፍሬዎች በአጠቃላይ አራት ሺህ 500 ችግኞችን የመትከል ስራ መከናወኑን ተናግረዋል፡፡
የተቋሙ የአመራር ልማት ስራዎች ለአካባቢው ማህበረሰብ የስራ እድል እንዲፈጠርለት፣ መሰረተ ልማት እንዲገነባለት እያደረጉ በመሆናቸው አካዳሚው ይህንኑ ተግባር አጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ አመላክተዋል፡፡
የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላት በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ውስጥ አረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ።
የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላት አረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር የችግኝ ተከላ አከናውነዋል።
በመርሀ ግብሩ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላት በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የስራ አመራር ዘርፍ ምክትል ርዕሰ አካዳሚ ወንድዬ ለገሰ (ዶ/ር) ጋር በመሆን በችግኝ ተከላው ላይ ታድመዋል።
የከፍተኛ ትምህርት አመራሩን አቅም የሚገነባ የትምህርት አመራር ልማት ፕሮግራም መቅረጽ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደረገ::

ውይይቱን ያደረጉት የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ እና የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ናቸው::

በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ያለውን የአመራር አቅም ውስንነት ለመሙላትና ሁሉን አቀፍ የከፍተኛ ትምህርት የአመራር ልማት ፕሮግራም ለመቅረፅ ሁለቱ ተቋማት የተወያዩ ሲሆን በጋራ በመስራት የዘርፉን ሁለንተናዊ ዕድገት ማረጋገጥ እንደሚቻል ከስምምነት ላይ ተደርሷል::

የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ በውይይቱ ላይ እንደገለጹት በሁለቱ ተቋማት የሚቀረፀው የከፍተኛ ትምህርት የአመራር ልማት ፕሮግራም የዘርፉን አመራር አቅም በመገንባት ለትምህርት ጥራት እና ለትውልድ ግንባታ የሚኖረው ሚና ቀላል ግምት የሚሰጠው አይደለም ብለዋል::

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ በበኩላቸው የሚቀረፀው የከፍተኛ ትምህርት አመራር ልማት ፕሮግራም የዘርፉን አመራር በብቃት ለማልማት እና ስምሪት ለመስጠት ዕድል የሚፈጥር መሆኑን ጠቁመው በአውሮፓና አሜሪካ ይገኛል ተብሎ ከሚታሰበው ልምድና ስልጠና የተሻለ እንደሚሆን ያላቸውን እምነት ገልጸዋል::

የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ እና ትምህርት ሚንስቴር የከፍተኛ ትምህርት አመራር ልማት ፕሮግራም ቀርፃን የሚከውን የቴክኒክ ኮሚቴ አቋቁመው ውይይቱን አጠናቀዋል::
👍1