African Leadership Excellence Academy
2.34K subscribers
2.55K photos
96 videos
6 files
119 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
#አሁን
#Happening_now

#የአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ ፕሬዚደንት #ዛዲግ_አብርሃ በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በተዘጋጀው የመጀመሪያው የአፍሪካ ከተሞች ፎረም ላይ ተገኝተው The Future of Urban Leadership በሚል ርዕስ ፅሁፍ እያቀረቡ ነው::

የመጀመሪያው የአፍሪካ ከተሞች ፎረም "ዘላቂ የከተሞች ልማት ለአፍሪካ ትራንስፎርሜሽን አጀንዳ 2063" በሚል መሪ ኃሳብ ከዛሬ ጀምሮ ለሦስት ቀናት በአዲስ አበባ የአድዋ መታሰቢያ መካሄድ ጀምሯል።

በፎረሙ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ፤ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ ከ47 በላይ የአፍሪካ አገራት ተወካዮች፣ የአፍሪካ ከተሞች ከንቲባዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ ምሁራን፣ ተመራማሪዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

ለተከታታይ ሶስት ቀናት በሚካሄደው አህጉራዊ ፎረም በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዝየም እና #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ የአመራር ልማት ማዕከል ውስጥ የኢትዮጵያ ከተሞች ተሞክሯቸውን በማጋራት ከአቻ የአፍሪካ ከተሞች የልምድ ልውውጥ የሚያደርጉበት ይሆናል።
👍2👎1
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ

*******************************
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከዘርፉ የክልል አመራሮች፣ ባለድርሻ እና አጋር አካላት ጋር ለሁለት ተከታታይ ቀናት #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ ሲያደርገው የነበረው የምክክር መድረክ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል፡፡
👍3
#አሁን
#Happening_now

#የአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ እና #የከተማ_እና_መሰረተ_ልማት_ሚኒስቴር
በጋራ ያዘጋጁት የተተኪ ወጣቶች ስልጠና #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ የአመራር ልማት ማዕከል ውስጥ እየተሰጠ ነው::
#በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ የስራ አመራር ዘርፍ ምክትል ርዕሰ አካዳሚ #ወንድዬ_ለገሰ (ዶ/ር) በስልጠናው መክፈቻ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለፁት አካዳሚው የወጣቶችን አቅም ለመገንባት በርካታ ስራዎችን እየሰራ እንደሆነ ጠቅሰው ወጣቶች የወደፊት አገር ተረካቢ መሆናቸውን ተገንዝበው የመሪነት አቅማቸውን በሚያሳድጉ ተግባራት ውስጥ በንቃት መሳተፍ እንዳለባቸው ተናግረዋል::

ስልጠናው የአፍሪካን የወደፊት የከተማ አመራር ማብቃት (Future urban leaders for Africa) በሚል እየተሰጠ ሲሆን ተሳታፊዎቹም ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት: ከተለያዩ ሲቪል ማህበራት: መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት የተውጣጡ አንድ መቶ ወጣቶች እየተሳተፉ ነው::

በዘርፉ ልምድ ያላቸው ከፍተኛ አመራሮችና ሙሁራንና ስልጠናውን የሰጡ ሲሆን ያካበቱትን ልምድና የህይወት ተሞክሮ ለውጣቶቹ አካፍለዋል::

#የአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚን የሪፎርም: ማስፋትና ሽግግር ፕሮግራም #በእሸቴ_አበበ (ዶ/ር) ቀርቧል::
ጳጉሜን 1፤ 2016 - የመሻገር ቀን
“የመሻገር ጥሪቶች፤የአዲስ ብርሃን ወረቶች”
ጳጉሜን 2፤ 2016 - የሪፎርም ቀን
“ሪፎርም ለላቀ አገልግሎት”
ጳጉሜን 3፤ 2016 - የሉዓላዊነት ቀን
“ኀብር ለሁለንተናዊ ሉዓላዊነት”
👍2
የገጠር መንገድ ትስስርን ተደራሽ በማድረግ የዜጎችን የምግብ ዋስትና ማረጋገጠ አለብን ሲሉ የከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ሄለን ደበበ #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ የአመራር ልማት ማዕከል ውስጥ በተደረገው መርሀ ግብር ላይ ተናገሩ፡፡

ሚኒስትር ዲኤታዋ ይህን ያሉት ከሁሉም ክልሎች ለተውጣጡ የመንገድና ትራንሰፖርት ዘርፍ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በሚኒስቴር መ/ቤቱ አስተባባሪነትና በአለም ባንክ ድጋፍ በ407 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የገጠር ትስስርን በማጠናከር የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችለውን አዲሱን ፕሮጀክት ማስጀመሪያ መርሀ ግብር #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ ውስጥ ነው፡፡
ጳጉሜን 4፤ 2016 - የኅብር ቀን
“ኅብረት ለሰላማችን"
እንኳን አደረሳችሁ!!
መልካም አዲስ ዓመት!!
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለመላው የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ቤተሰቦች፦
አዲሱ ዓመት የሰላም፤ የጤና እና የብልጽግና እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ!!
ዛዲግ አብርሃ
ፕሬዚደንት
👍2
ጳጉሜን 5፤ 2016 - የነገ ቀን
“የዛሬ ትጋት፤ ለነገ ትሩፋት”