የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ተቋማት በአደጋ ስጋት ስራ አመራር ፖሊሲና ሰብዓዊ ድጋፍ በራስ አቅም ንቅናቄ ጉዳዮች ላይዛሬ ነሀሴ 4 ቀን 2016 ዓ.ም #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ እየመከሩ ነው፡፡
የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ጉዳይ የብሄራዊ ደህንነት፣ ማህበራዊ ፍትህ፣ የዘላቂ ልማትና ሁለንተናዊ ምላሽ የሚጠይቅ መሆኑን የኢ.አ.ስ.ሥ.አ.ኮ. ኮሚሽነር አምባሳደር ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማሪያም የምክክር መድረኩን ሲከፍቱ ተናግረዋል፡፡
በዚህም የሚዲያን የኮሙኒኬሽን አካላት የተዋናይነት ሚና እንዳላቸው የተገለጸ ሲሆን፣ ሙያዊና አገራዊ ግዴታቸውን ለመወጣትም የአደጋ ስጋር ሥራ አመራር ፖሊሲ ጉዳዮችን አውቀው የማህበረሰቡን ግንዛቤ የማሳደግ ሃላፊነት እንዳለባቸው ተመላክቷል፡፡
ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም መሽፈን የአገራችንን ሉዓላዊነት ሙሉ በማድረግ በኩል ሰፊ ሚና መኖሩም ተገልጿል፡፡ ምክክሩም ለሁለት ቀናት #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ የሚቆይ ይሆናል፡፡

ከተረጅነት አስተሳሰብ መውጣት የብሔራዊ ደህንነት፣ የማህበራዊ ፍትሕና የዘላቂ ልማት አጀንዳዎችን የማሳካት ጉዳይ ነው
መገናኛ ብዙኃን ከተረጅነት አስተሳሰብ መውጣትን የብሔራዊ ደህንነት፣ የማህበራዊ ፍትሕና የዘላቂ ልማት አጀንዳዎች መሆናቸውን ታሳቢ አድርገው መሥራት እንዳለባቸው የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ገለጸ፡፡
የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ከመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ጋር በመተባበር #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ የአመራር ልማት ማዕከል ውስጥ ያዘጋጀው የመገናኛ ብዙኃን እና ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች ሥልጠና ተጠናቋል፡፡
የኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር)፤ የተረጅነት አስተሳሰብ የዜጎችን ነፃነትና የሀገርን ሉዓላዊነት የሚሸረሽር መሆኑን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ የዘለቀ የተረጅነት አስተሳሰብና ሥነ ልቦና በብዙዎች ዘንድ በራስ አቅም የመለወጥ ተስፋ እንዳይኖር አድርጓል ብለዋል፡፡
በመሆኑም ኢትዮጵያ ያላትን እምቅ የተፈጥሮ ሀብትና የሰው ሃይል ተጠቅማ ከተረጅነት የምትላቀቅበት "የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ፖሊሲ ባሳለፍነው የካቲት ወር ተሻሽሎ እንዲጸድቅ መደረጉን አስታውሰዋል።
በኢትዮጵያ እስከ 2030 ዓ.ም ለአደጋ ስጋት የማይበገር ማህበረሰብ ለመገንባት ፖሊሲው የሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ አደጋሮች በራስ አቅም ምላሽ መስጠት ያስችላል ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ ለም አፈር፣ ሁሉን አብቃይ የሆነ መልክዓ ምድርና የአየር ጸባይ እንዲሁም አምራች የሰው ሃይል ያላት በመሆኑ ከተረጅነት አስተሳሰብ በመላቀቅ ሰርቶ መለወጥ የሚገባ መሆኑን አንስተዋል።
የተረጅነት አስተሳሰብ የብሔራዊ ደህንነትና የሀገር ሉዓላዊነት ሥጋት በመሆኑ ሰርቶ ማደግና ችግርን በራስ አቅም መፍታት የሚያስችል ግንዛቤ መፍጠር ይገባል ብለዋል፡፡

የመረዳዳት ባህልን በሥርዓት በማስተዳደር ዜጎች በራሳቸው ጸጋ ለአደጋ ምላሽ እንዲሰጡ የመገናኛ ብዙኃንና ኮሙኒኬሽን ሰፊ ግንዛቤ መፍጠር አለባቸው ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያ በተረጅነት አስተሳሰብ ላይ የጋራ መረዳት ከተፈጠረ ለመጠባበቂያ እና እለት ደራሽ ክምችት የሚያስፈለገውን 2 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን ሰብዓዊ እርዳታ በራስ አቅም መሸፈን የሚያስችል ሀገራዊ አቅም እንዳለ ገልጸዋል፡፡
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ፤ #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ ውስጥ ተገኝተው የዜጎችን ሁሉን አቀፍ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ የመገናኛ ብዙኃንና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ ሚናው የላቀ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ፖሊሲ ክብረ ነክ ከሆነ የተረጅነት እሳቤ የመውጫ መንገድ መሆኑን መረዳትም ይገባል ብለዋል፡፡
ከተረጅነት አስተሳሰብ በመላቀቅ አደጋዎችን በራስ አቅም ምላሽ መስጠት የሚችለበት አቅም መኖሩን ለህብረተሰቡ ማስገንዘብ ተገቢ መሆኑንም አንስተዋል።
የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት የሥራ ኃላፊዎችም፤ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ፖሊሲውን ገቢራዊ በማድረግ ከተረጅነት አስተሳሰብ ለመውጣት በሚደረገው ጥረት ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ዘገጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሰይፈ ደርቤ፤ በኢትዮጵያ ሴፍትኔት ልምድ ተረጅነት ባህል ሆኖ መቆየቱን ገልጸዋል፡፡
በመሆኑም ችግሩ ዘመናትን የተሻገረና ስር የሰደደ በመሆኑ ተከታታይ የአስተሳሰብና የግንዛቤ ፈጠራ ስራ ማከናወን ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
የፋና ብርድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ሥራ አስፈፃሚ አቤል አዳሙ፤ የተረጅነት እሳቤ በብዙዎች ዘንድ የጠባቂነት አስተሳሰብ አሳድሯል ሲሉ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ሥራ አስፈፃሚ አብዱራህማን ሩቤ፤ ከተረጅነት አስተሳሰብ ለመውጣት አደጋ ከመድረሱ በፊት መስራት እንደሚገባ አንስተዋል።
መገናኛ ብዙኃን ሀገራዊ አጀንዳ በመቅረፅ የማህበረሰቡን አረዳድ በመቀየር ዜጎችን ከተረጅነት አስተሳሰብ ለማላቀቅ ሚናቸውን በሚገባ መወጣት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

"ያለማሰለስ መሥራት ለስኬት ቁልፍ ነው" ይባላል። የኢትዮጵያ የደን ሽፋን የ#አረንጓዴዓሻራ ንቅናቄ ከተጀመረበት በ2011 ከነበረበት 17.2 በመቶ ወደ 23.6 በመቶ ማደግ የቻለው ባላሰለሰ ጽኑ ጥረት ነው።
በክረምቱ የችግኝ ሥራ መሪዎን ይከተሉ። አሻራዎን ይትከሉ።
ከ2011 እስከ 2016 ዓ.ም ምስሎች።
They say “consistency is the key to success." Did you know that Ethiopia's forest cover increased from 17.2% at the inception of the #GreenLegacy initiative in 2019 to 23.6% by 2023 through sheer consistency?
Follow the leader this rainy season and #PlantYourPrint.
Images from 2019 to 2024.
#GreenLegacy
#አረንጓዴዓሻራ
#PMOEthiopia