NESIHA TV | ነሲሓ ቲቪ
28.5K subscribers
646 photos
215 videos
7 files
886 links
የነሲሓ ቲቪ ኦፊሺያል ቻነል http://t.me/nesihatv

ኢስላማዊ እውቀት ለሁሉም!!
Download Telegram
የተማሪዎች ምርቃት በኢብኒ አባስ መርከዝ 01 || NesihaTv

https://youtu.be/YB53AVmIkP8

ነሲሓ ቲቪ...
ኢስላማዊ እውቀት ለሁሉም!!

@nesihatv
ውድ የነሲሓ ቲቪ ቤተሰቦች ፕሮግራሞቻችንን በ Nilesat ሙሉ ለሙሉ ያዞርን ስለሆነ ከታች በተጠቀሰው አድራሻ መከታተል የምትችሉ መሆኑን እናሳዉቃለን:-

Nilesat
Frequency: 11555 or 11554
Polarization: Vertical
Symbol Rate: 27500
Fec. 5/6

ነሲሓ ቲቪ "ኢስላማዊ እውቀት ለሁሉም!
የተከበራቹ የነሲሓ ቤተሰቦች:-

አሰላሙ አላይኩም ወራህመቱላህ

ነሲሓ ቲቪ በሁለቱም ሳተላይቶች ስርጭቱን ሲያስተላልፍ መቆየቱ ይታወሳል። ሆኖም በቅርቡ ከኢትዮ ሳት [NSS-12] ለመውጣት ተገደናል። ይህንን ተከትሎ ጉዳዩ ያሳሰባቸው ወዳጆቻችን ነሲሓን ወደ ኢትዮሳት የማስመለስ ቅስቀሳ መጀመራቸውን አስተውለናል።
አላህ ኸይር ጀዛ ይክፈላቸው።

የነሲሓ ቲቪ አስተዳደር ይህንን ውሳኔ ሲወስን፤ በተለያዩ ምክንያቶች ከጣቢያው ቤተሰቦች የሚሰበሰበው እርዳታ በማሽቆልቆሉና ከምንዛሬ መናር እና ጋር በተያያዘ የሳተላይት ክፍያው አቅምን በከፍተኛ ደረጃ የፈተነ ሲሆን በሁለቱም ሳተላይቶች ላይ መቀጠሉ አዳጋች ሆኗል። ስለሆነም አማራጮችን በመገምገም በናይል ሳት ላይ ብቻ መቀጠሉ የተሻለ ሆኖ አግኝተነዋል።
ከሀገር ውጭ ያሉ ተመልካቾች እንዲያገኙን ማስቻሉ በናይልሳት ብቻ እንድንቀጥል ካደረጉን ምክንያቶች አንዱ ሲሆን፤ የተሻለ የሳተላይት ክፍያ መገኘቱም ሌላኛው ምክንያት ነው። የሐረመይን ቻነሎችን ጨምሮ በርካታ ጠቃሚ ዲናዊ ቻነሎች በናይልሳት መገኘታቸውም ለውሳኔው ተጠቃሽ ምክንያት ነው። ስለሆነም የነሲሓ ቤተሰቦች የዲሻቸውን ሰሀን ወደ ናይል ሳት በማዞር ነሲሓ ቲቪን እንዲከታተሉ እንጋብዛለን።

ሆኖም በናይል ሳት የሚተላለፈውን ስርጭት ቀጣይነት ለማረጋገጥና የፕሮግራሙን ጥራት ለማስጠበቅ በነሲሓ ወዳጆች የተጀመረው የድጋፍ እንቅስቃሴ ወሳኝ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠሉ በእጅጉ አስፈላጊ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን።

ወሰላሙ አለይኩም

ኢሊያስ አወል
ሥ/አስኪያጅ

T.me/nesihatv
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ልዩ የሙሃደራ ፕሮግራም ባህርዳር ከተማ

🎤 በሸይኽ ኢልያስ አህመድ
🎤 በሸይኽ ሙሀመድ ኢድሪስ
🎤 በኡስታዝ መሃመድ ሃሠን ማሜ

አድራሻ፦ ቀበሌ 16 ከኖክ ማደያ ፊት ለፊት ተውፊቀል ኸይራት መስጂድ እሁድ ጥቅምት 06 ከዓሱር ሶላት በኋላ


ነሲሓ ቲቪ...
ኢስላማዊ እውቀት ለሁሉም!!

@nesihatv
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር በዳሩል ሀዲስ የሸሪዓ ትምህርት እና የአረበኛ ቋንቋ ኢንስቲትዩት ሲያስተምራቸው የቆዩ 231ተማሪዎቹን በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል።

እሁድ ከቀኑ 08፡30 ጀምሮ

በድጋሚ እሁድ ምሽት 2፡30 ላይ በነሲሓ ቲቪ እንድትከታተሉ እንጋብዛለን ::

ነሲሓ ቲቪ...
ኢስላማዊ እውቀት ለሁሉም!!

@nesihatv