NESIHA TV | ነሲሓ ቲቪ
28.6K subscribers
673 photos
227 videos
7 files
907 links
የነሲሓ ቲቪ ኦፊሺያል ቻነል http://t.me/nesihatv

ኢስላማዊ እውቀት ለሁሉም!!
Download Telegram
የምርጫ ምዝገባ ጊዜ ተራዝሟል !!

የኢ/እ/ጉ/ጠ/ጉባኤ የምርጫ ቦርድ በ 2017 ለሚያካሄደው የመጅሊስ ምርጫ ከዚህ በታች ባሉ ምክንያቶች ለተጨማሪ ሁለት ሣምንት ጊዜ እንዲራዘም ወስኗል፡፡
1. የህዝቡ የምርጫ ምዝገባ ግንዛቤ በበቂ ደረጃ ተደራሽ አለመሆን፣
2. የምርጫ ቁሳቁስ ለሁሉም የሀገሪቱ ክፍል በእኩል ደረጃ ባለማዳረሱ፣
3. ወቅቱ የሀገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበት ወቅት በመሆኑ በአስመራጭ ቦርድ አባልነት የተመረጡ አባላቶች በዚሁ ሥራ ላይ በመሆናቸው፣
4. ህዝቡ የምርጫ ምዝገባ ሲስተም (Online registration) ሥርዓት የተለመደ አለመሆንና ገና በመነቃቃት ላይ በመሆኑ፣
5. ከሁሉም አካባቢዎች የሚገኙ ሙስሊም ህብረተሰብ እየቀረበ ያለው የምዝገባ ጊዜ መራዘም ጥያቄዎች መበራከታቸው፣
በአጠቃላይ ቦርዱ ከላይ የቀረቡትን ጉዳዮች በጥልቀት በመገምገምና በማገናዘብ በመላ ሀገሪቱ የሚካሄደው የመጅሊስ የ 2017 ምርጫ በ 2 ሳምንት የተጨማሪ ጊዜ በመጨመር ማለትም እስከ ሐምሌ 13 ቀን 2017 ድረስ የምዝገባ ቀን እንዲራዘም ወስኗል፡፡
ስለዚህ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል የሚገኙ ምስሊም ማህበረሰብ በቀሩት ቀናት በነቂስ ወጥቶ እንዲመዘገብና የመሪ ተቋም መሪዎችን ለመምረጥ እንዲመዘገቡ ዳግም ጥሪ እናቀርባለን፡፡»

#ምርጫ_ለፅኑ_ተቋም
የኢ/እ/ጉ/ጠ/ጉ/የምርጫ ቦርድ

@nesihatv
👍47👏3