NESIHA TV | ነሲሓ ቲቪ
28.5K subscribers
646 photos
214 videos
7 files
885 links
የነሲሓ ቲቪ ኦፊሺያል ቻነል http://t.me/nesihatv

ኢስላማዊ እውቀት ለሁሉም!!
Download Telegram
October 2, 2022
October 5, 2022
የተከበራቹ የነሲሓ ቤተሰቦች:-

አሰላሙ አላይኩም ወራህመቱላህ

ነሲሓ ቲቪ በሁለቱም ሳተላይቶች ስርጭቱን ሲያስተላልፍ መቆየቱ ይታወሳል። ሆኖም በቅርቡ ከኢትዮ ሳት [NSS-12] ለመውጣት ተገደናል። ይህንን ተከትሎ ጉዳዩ ያሳሰባቸው ወዳጆቻችን ነሲሓን ወደ ኢትዮሳት የማስመለስ ቅስቀሳ መጀመራቸውን አስተውለናል።
አላህ ኸይር ጀዛ ይክፈላቸው።

የነሲሓ ቲቪ አስተዳደር ይህንን ውሳኔ ሲወስን፤ በተለያዩ ምክንያቶች ከጣቢያው ቤተሰቦች የሚሰበሰበው እርዳታ በማሽቆልቆሉና ከምንዛሬ መናር እና ጋር በተያያዘ የሳተላይት ክፍያው አቅምን በከፍተኛ ደረጃ የፈተነ ሲሆን በሁለቱም ሳተላይቶች ላይ መቀጠሉ አዳጋች ሆኗል። ስለሆነም አማራጮችን በመገምገም በናይል ሳት ላይ ብቻ መቀጠሉ የተሻለ ሆኖ አግኝተነዋል።
ከሀገር ውጭ ያሉ ተመልካቾች እንዲያገኙን ማስቻሉ በናይልሳት ብቻ እንድንቀጥል ካደረጉን ምክንያቶች አንዱ ሲሆን፤ የተሻለ የሳተላይት ክፍያ መገኘቱም ሌላኛው ምክንያት ነው። የሐረመይን ቻነሎችን ጨምሮ በርካታ ጠቃሚ ዲናዊ ቻነሎች በናይልሳት መገኘታቸውም ለውሳኔው ተጠቃሽ ምክንያት ነው። ስለሆነም የነሲሓ ቤተሰቦች የዲሻቸውን ሰሀን ወደ ናይል ሳት በማዞር ነሲሓ ቲቪን እንዲከታተሉ እንጋብዛለን።

ሆኖም በናይል ሳት የሚተላለፈውን ስርጭት ቀጣይነት ለማረጋገጥና የፕሮግራሙን ጥራት ለማስጠበቅ በነሲሓ ወዳጆች የተጀመረው የድጋፍ እንቅስቃሴ ወሳኝ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠሉ በእጅጉ አስፈላጊ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን።

ወሰላሙ አለይኩም

ኢሊያስ አወል
ሥ/አስኪያጅ

T.me/nesihatv
October 13, 2022
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
October 15, 2022
October 21, 2022
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
November 3, 2022