Ethiojobs pages.com
5.54K subscribers
3.63K photos
14 files
3.49K links
📑የተለያዩ የስራ ማስታወቂያዎች እና የስራ መረጃዎችን  ስንለቅ በፍጥነት እንዲደርሶ ቻናሉን ይቀላቀሉ
Abroad
NGO
DEGREE
DIPLOMA
LEVELS
PRIVATE
GOVERNMENT
A place where you found day to day new job opportunitie in Ethiopia and abroad in any field of study starting from #0_year experience
Download Telegram
ማስታወቂያ
..................//.................
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ግንቦት 28 ቀን 2012 ዓ.ም በጀማሪ ኤሌክትሪካልና ሜካኒካል መሃንዲስ የስራ መደቦች ላይ አወዳድሮ ለመቅጠር ማስታወቂያ ማውጣቱ እና አመልካቾችም በተቀመጠው መስፈርት መሰረት በኦን ላይን መመዝገባቸው ይታወቃል፡፡

ስለሆነም በተጠየቀው መስፈርት መሰረት ከዚህ በፊት በኦን ላይን የተመዘገባችሁ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአንድ ሳምንት ውስጥ የድግሪያችሁን ኮፒ ብቻ በኢሜይል አድራሻችን hr.hiring@eep.com.et እድትልኩልን እናሳውቃለን፡፡

ማሳሰቢያ፡-
****//****
አመልካቾች ኢሜይል በምታደርጉበት ወቅት በጉዳዩ (Subject) ላይ የተወዳደራችሁበት የትምህርት ዘርፍ (Field) ጠቅሳችሁ እንድትልኩልን እናሳስባለን፡፡

ነሐሴ 19/2012 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል
መረጃውን ሸር በማድረግ ለሚመለከታቸው እናካፍል።

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2013 ዓ.ም ለድህረ ምረቃ ትምህርት በቀን መርሃ ግብር ለሁለተኛ እና ለሶስተኛ ዲግሪ እንዲሁም በማታ መርሃ ግብር ለሁለተኛ ዲግሪ ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡

⚡️የትምህርት አሰጣጡ የኮቪድ-19 በሽታ ወረርሽኝ እስከሚሻሻል ድረስ በቨርቹዋል እና በኢለርኒግ የመማር ማስተማር መንገድ በተጨማሪም እንደ አስፈላጊነቱ በገጽ ለገጽ የሚካሄድ መሆኑን እያሳወቀ የሚከተሉትን በማሟላት ማመልከት እንደምትችሉ ያሳስባል፡፡

1. የማመልከቻ ፎርሙን በዩኒቨርስቲው ድረገጽ (portal.aau.edu.et) መሙላት

2. ከማመልከቻው ፎርም የሚያገኙትን የማመልከቻ ቁጥር (Application Number) በመያዝ ብር 200 /ሁለት መቶ/ ለመመዝገቢያ ብር 600 /ስድስት መቶ/ የመግቢያ ፈተና ለመውሰድ በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ በሞባይል CBE ብር ወይም በወኪሎች ወይም በቅርንጫፍ አማካኝነት ክፍያ መፈጸም ያስፈልጋል (ክፍያ የሚፈጸምበትን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 2 አጭር ኮዶች ምዝገባው ከመጀመሩ በፊት በዩኒቨርሰቲው ድረ ገጽ እና በፌስቡክ እናሳውቃለን)፡፡

3. ክፍያዎትን ካጠናቀቁ በኋላ ወደ ማመልከቻ ፎርሙ በመመለስ ፒዲኤፍ (PDF) ፎርማት የተለወጠ የትምህርት ማስረጃዎትን፣ የወጪ መጋራት ሰነድዎትን$፣ እንዲሁም ለቀን መርሃ ግብር የትምህርት ወጪዎን /Sponsorship/ የሚሸፍንልዎት የመንግስት መስሪያ ቤት ከሆነ የተፈረመበትና ማህተም የተደረገበት ፎርም አስገብተው እና ሌሎች መረጃዎችን በማከል ምዝገባዎትን ማጠናቀቅ ይኖርብዎታል፡፡

4. የSponsorship ከዩኒቨርስቲው ድረ ገጽ (portal.aau.edu.et/ aau.edu.et) ማግኘት ይችላሉ፡፡

5. ለPhD አመልካቾች የ BA/BSc ዲግሪ/ጊዜያዊ ዲግሪ እና CGPA ያለው ትራንስክሪፕት እና የMA/MSC ዲግሪና ትራንስክሪፕት ማያያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡

6. በተጨማሪም ለPhD አመልካቾች ትምህርት ክፍሉ የሚጠይቀውን ማያያዝ ይኖርብዎታል፡፡

7. ለMA/MSC አመልካቾች የ yBA/BSc ዲግሪ/ጊዜያዊ ዲግሪ እና CGPA ያለው ትራንስክሪፕት ማያያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡

#ማሳሰቢያ
• ምዝገባው የሚከናወነው portal.aau.edu.et ብቻ ሲሆን ምንም አይነት ማስረጃ በአካል ይዞ በመቅረብ ማስገባት አይቻልም፡፡

• የወጪ መጋራት ያጠናቀቃችሁበትን ማስረጃ ዋናውን በተጠየቃችሁ ግዜ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡

• ኦፊሻል ትራንስክሪፕት ለአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሬጅስትራር ቢሮ ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1176 ያላስላከ አመልካች ቀጣይ የምዝገባ ሂደቶች እንደማይከናወኑለት እናሳስባለን፡፡

• የፈተና ግዜውን በተመለከተ ከትምህርት ክፍሉ ማስታወቂያ ሰሌዳ እንዲሁም ከዩኒቨርስቲው ድረ ገፅ (portal.aau.edu.et/aau.edu.et) መከታተል የምትችሉ ያሳውቃል፡፡

• ጤና ላይ ለሚያመለክቱት አመልካቾች ዲግሪያቸዉን ሲጨርሱ ከጤና ጥበቃ ወይም ከተማሩበት ዩኒቨርስቲ የሚሰጣቸዉን ደብዳቤ ወይም በየሴምስተሩ የሚሰጣቸዉን Grade report ማያያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡

• የተማሪዎች ቁጥር ከመቀበል አቅም በታች (ዝቅተኛ) ከሆነ የትምህርት ፕሮግራሞች የማይከፈቱ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

🗓የመመዝገቢያ ቀን ከነሐሴ 06 እስከ ነሐሴ 21 2012 ዓ.ም

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ከመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በቀን /መደበኛ/ ፕሮግራም ከ2005 እስከ 2012 ዓ.ም ተምረዉ ለተመረቁ አካል ጉዳተኛና ሴት ተማሪዎች የነፃ ትምህርት ዕድል (Scholarship) አዘጋጅቷል፡፡
የትምህረት አሰጣጡ የኮቪድ-19 በሽታ ወረርሽኝ እስከሚሻሻል ድረስ በቨርቹዋል እና በኢለርኒግ የመማር ማስተማር መንገድ በተጨማሪም እንደ አስፈላጊነቱ በገጽ ለገጽ የሚካሄድ መሆኑን እያሳወቀ የሚከተሉትን በማሟላት ማመልከት እንደምትችሉ ያሳስባል፡፡
1. ከመንግስት ዩኒቨርስቲ በቀን /መደበኛ /ፕሮግራም የተመረቀ/ች
2. የመጨረሻ የትምህርት ዉጤት (CGPA) 2.75 እና በላይ ያላቸዉ
3. ያለባቸዉን የወጪ መጋራት ክፍያ ከፍለዉ የጨረሱ እና ኦፊሻል ትራንስክሪፕት ከተማሩበት ዩኒቨርስቲ ማስላክ የሚችሉ
4. በገንዘብ ድጎማ (የኪስ ገንዘብ እየተከፈላቸዉ) ለሚወዳደሩ ከፍለዉ መማር እንደማይችሉ ከሚኖሩበት ወረዳ የተመሰከረ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
5. ለአካል ጉዳተኞች ከሚኖሩበት ወረዳ የተመሰከረ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
6. ትምህርት ክፍሉ የሚያወጣዉን የመግቢያ መስፈርት የሚያሟሉ መሆን ሲኖርባቸው
አመልካቾች
1. የማመልከቻ ፎርሙን በዩኒቨርስቲው ድረገጽ (portal.aau.edu.et) መሙላት
2. ከማመልከቻው ፎርም የሚያገኙትን የማመልከቻ ቁጥር (Application Number) በመያዝ ብር 200 /ሁለት መቶ/ ለመመዝገቢያ ብር 600 /ስድስት መቶ/ የመግቢያ ፈተና ለመውሰድ በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ በሞባይል CBE ብር ወይም በወኪሎች ወይም  በቅርንጫፍ  አማካኝነት ክፍያ መፈጸም ያስፈልጋል (ክፍያ የሚፈጸምበትን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 2 አጭር ኮዶች ምዝገባው ከመጀመሩ በፊት በዩኒቨርሰቲው ድረ ገጽ እና በፌስቡክ እናሳውቃለን) 
3. ክፍያዎትን ካጠናቀቁ በኋላ ወደ ማመልከቻ ፎርሙ በመመለስ ፒዲኤፍ (PDF) ፎርማት የተለወጠ የትምህርት ማስረጃዎትን፣ የወጪ መጋራት ሰነድዎትን እና ሌሎች መረጃዎችን አስገብተው ምዝገባዎትን ማጠናቀቅ$ 
4. የBA/BSc ዲግሪ/ጊዜያዊ ዲግሪ እና ያለው CGPA ትራንስክሪፕት ማያያዝ ይጠበቅብዎታል፡፡
ማሳሰቢያ
• ምዝገባው የሚከናወነው portal.aau.edu.et ብቻ ሲሆን ምንም አይነት ማስረጃ በአካል ይዞ በመቅረብ ማስገባት አይቻልም፡፡
• የወጪ መጋራት ያጠናቀቃችሁበትን ማስረጃ ዋናውን በተጠየቃችሁ ግዜ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡
• ኦፊሻል ትራንስክሪፕት ለአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሬጅስትራር ቢሮ ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1176 ያላስላከ አመልካች ቀጣይ የምዝገባ ሂደቶች እንደማይከናወኑለት እናሳስባለን፡፡
• የፈተና ግዜውን በተመለከተ ከትምህርት ክፍሉ ማስታወቂያ ሰሌዳ እንዲሁም ከዩኒቨርስቲው ድረ ገፅ (portal.aau.edu.et/aau.edu.et) መከታተል የምትችሉ ያሳውቃል፡፡
• ጤና ላይ ለሚያመለክቱት አመልካቾች ዲግሪያቸዉን ሲጨርሱ ከጤና ጥበቃ ወይም ከተማሩበት ዩኒቨርስቲ የሚሰጣቸዉን ደብዳቤ ወይም በየሴምስተሩ የሚሰጣቸዉን  Grade report ማያያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡ 
• የተማሪዎች ቁጥር ከመቀበል አቅም በታች (ዝቅተኛ) ከሆነ የትምህርት ፕሮግራሞች የማይከ
ክፍት የስራ መደብ ማስታወቂያ
.............................................
ዲላ ዩኒቨርሲቲ በጤና እና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ አጠቃላይ ሆስፒታል ከዚህ በታች በተጠቀሱት ክፍት የስራ መደቦች ላይ አመልካቾችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።
                 ፤
#አንደኛ፦ የስራ መደቡ መጠሪያ፦ አንስቴዥዮሎጂ ፕሮፌሽናል I
• ደረጃ፦ XII
• ብዛት፦ 4
• የመ.መ.ቁ.8.37/ዲዩ/ሆካ፦ 1701-1704
• ደመወዝ፦ 7071
• ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ፦ በሙያው የመጀመሪያ ዲግሪ
• ተፈላጊ የትምህርት አይነት፦ በአንስቴዮሎጂ ፕሮፌሽናል ሙያ የተመረቀ/ች
• የስራ ልምድ፦ አይጠይቅም
• የቅጥር ሁኔታ፦ በቋሚነት

#ሁለተኛ፦ የስራ መደቡ መጠሪያ፦ አንስቴዥዮሎጂ ፕሮፌሽናል I
• ደረጃ፦ XII
• ብዛት፦ 4
• የመ.መ.ቁ.8.37/ዲዩ/ሆካ፦ —
• ደመወዝ፦ 7071
• ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ፦ በሙያው የመጀመሪያ ዲግሪ
• ተፈላጊ የትምህርት አይነት፦ በአንስቴዮሎጂ ፕሮፌሽናል ሙያ የተመረቀ/ች
• የስራ ልምድ፦ አይጠይቅም
• የቅጥር ሁኔታ፦ በኮንትራት

#ማሳሰቢያ
ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዋናውን የትምህርት ማስረጃ ከማይመለስ አንድ ኮፒ ጋር በማያያዝ አዲስ አበባ ቦሌ ሩዋንዳ ኤምባሲ ፊት ለፊት በሚገኘው የዲላ ዩኒቨርሲቲ ጉዳይ አስፈፀሚ ጽ/ቤት ወይም ዲላ ዩኒቨርሲቲ  የሰው ሃ/ልማ/ሥ/አስ/ዳይሬክቶሬት (ዋናው ግቢ) መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን የፈተና ቀን በውስጥ ማስታወቂያ የሚገለፅ መሆኑን እናሳውቃለን።

ዲላ ዩኒቨርሲቲ
የሰው ሃ/ልማ/ሥ/አስ/ አመራር ዳይሬክቶሬት
Dilla University