Ethiojobs pages.com
5.03K subscribers
2.98K photos
14 files
3.09K links
📑የተለያዩ የስራ ማስታወቂያዎች እና የስራ መረጃዎችን  ስንለቅ በፍጥነት እንዲደርሶ ቻናሉን ይቀላቀሉ
Abroad
NGO
DEGREE
DIPLOMA
LEVELS
PRIVATE
GOVERNMENT
A place where you found day to day new job opportunitie in Ethiopia and abroad in any field of study starting from #0_year experience
Download Telegram
Ĥæíłű ŧ:
🔰ተመርቃቹ ሥራ በማፈላለግ ላይ ለምትገኙ ስለ
ተደጋጋሚ የሥራ ቃለመጠይቆች / ከጠቃሚ ማብራሪያ ጋር እንሆ ⬇️
=====================
@shegerjobs

1⃣ኛ. ራስዎን ያስተዋውቁን? (Please introduce yoursef to know who you are?)
@shegerjobs
ይህ ጥያቄ ቀላል ይመስላል እንጂ ብዙዎች ገና ከጅምሩ ስህተት የሚሰሩበት እንደሆነ ይስተዋላል። ብዙዎች የህይወት ታሪካቸውን ያወራሉ። የጥያቄው አይን ግን በሥራ (በትምህርት) ህይወት ላይ ስለቆዩበት ማንነትዎ፣ የት/ት ደረጃዎ፣ የስራ ልምድ ካለዎት ስለልምድዎ፣ ስላስመዘገቡትና ስለሠሩባቸው ጥሩ ሥራዎች፣ ጀማሪ ተቀጣሪ ከሆኑ በዩኒቨርሲቲ ቆይታዎ ስለነበረዎት መልካም እንቅስቃሴዎች ወይም ስለሠሯቸው የመመረቂያ ጥናቶች (Research) ወይም ፕሮጀክቶች በመዘርዘር እራስዎን ቢያስተዋውቁ የተሻለ ነው። በንግግርዎ ወቅት ለጠያቂው የመጀመሪያ ምርጫው እንዲሆኑ ጠቃሚ ነገሮችዎ ላይ ትኩረት ያድርጉ። የዘር ሀረግ እየቆጠሩ፣ የትውልድ ቦታ እየከለሉ ጥያቄውን እንዳይወድቁ ይጠንቀቁ።

2⃣ኛ. ስለዚህ የሥራ ማስታወቂያ እንዴት መረጃ አገኙ? (How did you got an information about this vacancy?)
@shegerjobs
ይኸም በተደጋጋሚ ይጠየቃል። የዚህ ጥያቄ ዓላማው ድርጅቱን ምን ያክል እንደሚወዱትና እንደሚፈልጉት ለማወቅም ጭምር ነው። በመሆኑም መልስዎ "የድርጅቱን ድህረ ገጽ እከታተል ስለነበር ከድህረ ገጹ ላይ"፣ በጋዜጣ የወጣ ከሆነ "ከጋዜጣ ላይ"፣ "ከማስታወቂያ ቦርድ" በኦንላይን : በማለት በትክክል ያገኙበትን መልስ ይመልሱ። ለመልስ ውበት ብለው ያልተለቀቀበትን መረብ ከጠቀሱ ውሸታም እንደሚባሉ ይወቁ።
3⃣ኛ. ስለመስሪያ ቤታችን ምን ያውቃሉ? (Have any knowhow about this organization?)
... @shegerjobs
ለቃለመጠይቅ ፈተና ከመቅረብዎ በፊት ስለ መስሪያቤቱ፦ የምስረታ ዘመን፣ ተልዕኮውን (Mission)፣ አላማውን እና ስፋቱን (scope and objective)፣ ራዕዩን (vision)፣ የምርት ውጤት (Final output) አስቀድመው ለማወቅ እና እርሰዎ ለአላማው መሳካት የሚያደርጉትነ አስተዋጽኦ ለማካተት ይሞክሩ። ይህንን መረጃ ከድኅረ ገጽ እና ከተለጠፉ ታፔላዎች ማግኘት ይችላሉ። ለዚህ ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ መስጠት ለሥራው የሰጡትን ትኩረት ያመለክታል።
4⃣ኛ. ለምን እዚህ መቀጠር ፈለጉ? (Why did you want to be employee in this company?)
@shegerjobs
ጥሩ ልህቀት የሆነውን ሰው ነውና ራስዎን ያዘጋጁ። በምንም ምክንያት "ሥራ ዕድል ስለፈጠረልኝ፣ ደመወዝተኛ ለመሆን፣ ሥራ ላለማጣት" የሚልበሚሠራባቸው ነገር እንዳይመልሱ።
. "መስሪያ ቤት ዘርፎች ላይ ብሳተፍ ትልቅ አስተዋፅኦ እንደማበረክት ስላመንኩኝ"
. "መስሪያ ቤቱ የላቀ እንቅስቃሴዎችን እያስመዘገበ በመሆኑ እኔም የዚህ አካል በመሆን ሀገሬንና መስሪያ ቤቱን ማሳደግ ስለምፈልግ፡፡"
(መስሪያ ቤት የሚሰጠውን አገልግሎት በመጥቀስ) "እንደዚህ ያለ አገልግሎት የሚሰጡ ቦታዎች ላይ መሆን ታላቅ እርካታን ስለሚሰጠኝ።" ብለው ይመልሱ።
5⃣ኛ. ለመስሪያ ቤቱ ምን አይነት አስተዋጽኦ አደርጋለሁ ብለው ያምናሉ (If you will employed, what role do you believe that you may pay for company?
. @shegerjobs
በመስሪያ ቤቱ የሥራ ቤተሰብ ከሆንኩ፦ በቡድን እንቅስቃሴ ውስጥ የቡድኑን አንድነት በማጠናከር (Team work)፣ልምድ የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠናዎችን በማመቻቸት (Skill building tranings)፣ የሥራ ልውውጥ በማድረግ (Experience sharing)፣ አዳዲስ ጥናቶችን ከመደበኛ ሥራዬ ጎን ለጎን በመስራት (Researchs and projects)፣ ደንበኞችን በአክብሮትና በተገቢው ሆኔታ በማስተናገድ (Respect and legality for customers)... ለመስሪያቤቱ እድገት ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱ ይናገሩ፡፡
6⃣ኛ. ጠንካራ ጎኖችዎ ምንድናቸው? (What are your strength?)
@shegerjobs
እውነተኛ ጥንካሬዎትን ይመስክሩ። (የሚፈልጉትን ምኞት ሳይሆን ያለዎት ነገር)። ከሚወዳደሩበት የሥራ መደብ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ሙያዊ ጥንካሬዎችዎን ቢያስቀድሙ የተሻለ ነው ፡፡
7⃣ኛ. የዚህን ድርጅት ራዕይ እና ተልእኮ ያውቃሉ? [what are vision and missions of this organization?]
@shegerjobs
ይህን ጥያቄ ለመመለስ አስቀድሞ መዘጋጀት ይጠበቅብዎታል። እየተወዳደሩበት ያለውን ድርግት ራዕይ፣ ዓላማ እና ተልእኮ አስቀድመው በሚገባ ማወቅ አለብዎ። ይህንን መረጃ በድርጅቱ ድኅረ ገጽ፣ በተሰቀሉ ባነሮች ላይ፣ በታተሙ በራሪ ወረቀቶች ላይ፣ በድርጅቱ የውስጥ ግድግዳዎች ላይ ስለሚያገኟቸው ፈጽሞ ሳያውቁ እንዳይገቡ ይመከራሉ። ምንም መረጃ ባያገኙ እንኳን ገና ራዕይ እና ተልዕኮ ያልረቀቀላቸው ሊሆኑ ስለሚችሉ በራስዎ ከመመለስ ይልቅ የቅርብ ሰዎችን አፈላልጎ መጠየቅ ተገቢ ነው።
8⃣ኛ. ስለድርጅቱ ምን ምን ያውቃሉ? [what knowhows do you have about this organization?]
@shegerjobs
እያንዳንዱ ድርጅት የራሱ የሆነ ታሪክ አለው። ይህም ጥያቄ ድርጅቱን ለማወቅ እና የድርግጁ ሰራተኛ ለመሆን ካለዎት ጉጉት አንጻር ምን ያክል እንደተጓዙ ያመለክታልና ሰፋ ያለ መረጃዎችን በማሰባሰብ ምላሽ መስጠት ተገቢ ነው። ለዚህ መልስ ለመስጠት ቢያንስ መቼ እንደተመሰረተ፣ ማን እንደመሰረተው [ባለቤቱ ማን እንደሆነ]፣ የት እና በምን ያክል መነሻ ገንዘብ [Capital] እንደተመሰረተ፣ ስንት ቅርንጫፎች እንዳሉት፣ ዋና መስሪያ ቤቱ የት እንደሆነ፣ ምን ምን አይነት አገልግሎቶች እንደሚሰጥ፣ ምን ያክል የገንዘብ ሃብት እንዳለው፣ ምን ያክል ሰራተኞች እንዳሉት፣ ምን አይነት የእድገት ፍጥነት እንዳለው... የመሳሰሉትን ማወቅ ይኖርበዎታል። እነዚህን ካወቁ የድርጅቱን ማንነት መግለጽ ይችላሉ ማለት ነው
9⃣ኛ. በአንድ መስሪያ ቤት ውስጥ ሊኖሩ የሚገባቸው መርሆችና እሴቶች ምን ምን ናቸው? [What are values and principles expected from one organization?]
@shegerjobs
እነዚህ ነገሮች በአብዛኛውአገልግሎት ለሁሉም ድርጅቶች ተቀራራቢ የሆነ ይዘት ቢኖራቸውም እንደ ድርጅቱ ባህርይና ይዘት ሊለያዩ ስለሚችሉ በራሱ በድርጅቱ ውስጥ ያሉትን እሴቶችና መርሆች አፈላልጎ ማወቅ ተገቢ ነው። ከእነዚህም ውስጥ ሃቀኝነት [integrity]፣ የደንበኞች እርካታ [customer satisfaction]፣ የሰራተኞች እርካታ [employees satisfaction]፣ ታማኝነት [honesty]፣ የቡድን ወይም የኅብረት ሥራ [team work]፣ የህዝብን አደራ መወጣት [public trust]፣ ትህትና [humility]፣ ቀላል አገልግሎት [simplicity]፣ አንድነት [unity]፣ ደስተኛነት [happiness]፣ ነጻነት [freedom]፣ ግልጸኝነት [Transparency]፣ ፍቅር ዋና ዋናዎቹ ናቸው ::

መልካም ዕድል !

🛑 #like & #ሼር በማረግ ሌሎችም ተጠቃሚ እንዲሆኑ የራስዎን አስተዋጽኦ ያበርክቱ ! ⬇️

@ethiojobs90