ይቺን ቅጠል ብቻ እየመረጠ አንበጣው ቢያጠቃ እጅግ ጥሩ ነበር ከኢትዮጵያ ምድር እስከሚጠፋ ቢወረው ጥሩ ነበር ሌላ ሳይነካ የትውልድ ፀር
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እንዲህ ያለ ትግል ነው የገጠመን 😂
ትምህርት ለዚች ሃገር የፈየደላት አንዳች ነገር የለም።‼️⬇️
በሃገራዊ ማንነት ያልተቃኘው ሁሉን ሰልቃጭ (የባዕድ) የትምህርት ስርዓታችን የነቀዘ ቲወሪና ንድፈሃሳብ እያግበሰበሰ ከመሸጥ ያለፈ ረብ ያለው ምሁርን መፍጠር አልተቻለውም። ይልቁንም ኤሌክትሪካል ምህንድስና ተምሮ ገመድ መቀጠል የማይችል መሀንዲስ፣ እጽዋት ሳይንስ ተምሮ ስንዴ ለይቶ የማያውቅ ታክሶኖሚስት፣ ጅኦግራፊ ተምሮ ስንት አህጉር እንዳለ እንኳን በቅጡ የማያውቅ ጅኦግራፈር ብቻ ምን አለፋችሁ በየዘርፉ እልፍ አዕላፍ ሸክሞችን እየፈጠረ ነው።
እስካሁን ድረስ ሃገሪቱ የምትመራው በገበሬ እውቀት ብቻ ነው። ምሁር ነን ባዩ የገበሬ እውቀትን ከዚያም ከዚያም ቀራርሞና አዳቅሎ ገበሬው እንዳያውቅበት በእንግሊዝኛ አትቶ ለራሱ የተመራማሪነትን ካባ ይደርብበታል።
ገበሬው "ሐይቄን እምቦጭ ወረረብኝ ምን ላድርግ?" ሲለው የምሁሩ መልስ "እንቦጩን በእጅህ መንቀል የተሻለ አማራጭ ነው" ከማለት የዘለለ አይደለም።ከጤፍ ማሳ እስከ ስንዴ መሬት ከበቆሎ ማሳ እስከ ገብስ መሬት ድረስ እድሜ ልኩን አረም በመንቀል ለኖረ ለፍቶ አደር ገበሬ እንቦጭን በእጅህ ንቀል የሚል ምሁር አቤት እግዚኦ።
"ብሔራዊ ፓርኩ ተቃጠለ ምን እናድርግ?" ሲላቸው ጥርሱን ነቅሎ ያደገበትን "በቅጠልና በአፈር አጥፋው" በማለት ወገቡን ይቆርጡታል።
"ሰብሌን አንበጣ በላብኝ ምን ላድርግ?" ሲላቸው "ጅራፍ አጩህበት" በማለት ፍርደ ገምድልነታቸውን ያናፉበታል።
ሰሜን ብሔራዊ ፓርክ ከነ ብርቅየ ብዝኀ ሕይወታዊ ሃብቱ በእሳት ሲቃጠል፣ ጣና ሐይቅ ከነ ሙሉ ታሪኩና ከነገዳማቱ በእንቦጭ ሲወረር፣ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ዓይናችን እያየ ሲፈራርሱ፣ ሰሞኑንም ቃፍታ ሁመራ ብሔራዊ ፓርክ ከነ ዝሆን ሃብቱ በእሳት ሲጋይ እንዲሁም ቆላማው ሰሜን ምስራቃዊ ኢትዮጵያ በአንበጣ መንጋ ሲወረር ምሁሩ ምን ፈየደ?
ምንም።
ዛሬ ሁሉ ነገር ሲወድም ዝም ብለው የተመለከቱ ምሁራንና ተቋማት ነገ ላይ ግን ሊቅ አክለው ምሁር መስለው ማስታወሻቸውን በቆዳ ቦርሳ ወሽቀው ለኪሳራ ግመታ የተፈጠሩ ይመስል
"Assessment of 2019 Locust invasion crisis in case of North east Ethiopia" የሚል የምርምር እንቶ ፈንቶ ደርተው በታዋቂ ዓለማቀፍ ጆርናሎች ያሳትማሉ።
ለእኛ ሃገር ምሁርነት ከዚህ ያለፈ አይደለም።
በዚች ሃገር ላይ ሰርቶ የሚበላ አርሶ አደር ብቻ ነው ሌላው አውርቶ አደርና ቀምቶ አደር ብቻ ነው።በማስመሰል አድጎ በማስመሰል አርጅቶ በማስመሰል ያልፋል።
ከ80 ፐርሰንት በላይ ለሃገሪቱ የውጭ ምንዛሬ ምክንያት የሆነ ገበሬ ስኳር ምን እንደሚመስል አያውቅም በመብራት ብርሃን ታጅቦ መኖር ምን ምን እንደሚል ለማወቅ አልታደለም።
ለመሬት ጠል ለሰማይ ደመና እግዜር አይነሳም ብሎ በእምነት ዘርቶ በተስፋ እየኖረ በነፃ የሚመግብ ይህ ደግ ገበሬ ሰብሉ በአንበጣ መንጋ ተበልቶበት ተስፋው ሲሟጠጥ ማየት እንደምን ይጨንቃል።
ተፈጥሮ በድሏት ጠጠር ላይ ከበቀለች እድሜዋ ከአንድ ጎረምሳ እድሜ የምትስተካከለው እስራኤል ጭንጫ መሬት ላይ በዘመናዊ ግብርና ከመራቀቅ ተሻግራ ሰው ሰራሽ ደመና ወደ መስራት ጥበብ እያኮበኮበች ነው። እኛ ግን የዛሬ 3000 ዓመት በታረሰበት ማረሻ አሁንም እያረስን ነው።
እናም የሞተው የትምህርት ስርዓታችን ከተቀበረበት ተነስቶ ወደ ቀደመ ማንነታችን ካልተመለስን ዓይናችን እያየ አንበጣ ይበላናል።
ፍትሕ ደንታቢስና ስሜት የለሽ ምሁራንን አዝሎ ጀርባው ለጎበጠው የሃገሬ ገበሬ።
©አፄ እንደልቡ