Ethio Job Vacancy
45.4K subscribers
23.2K photos
63 videos
157 files
19.2K links
አዳዲስ እና ወቅታዊ የሥራ ቅጥር ማስታወቂያዎችን ከተለያዩ ጋዜጦችና ድረ ገጾች ለሥራ ፈላጊዎች መረጃ መስጠት ነው።
Post New Job vacancies to Who are looking jobs.
Group discussion https://t.me/+uGe3tVg5jF4yZjk0
Download Telegram
EPHI - Exam Result
የቅጥር ማስታወቂያ
**************
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ከዚህ በታች በተገለፀው ክፍት የስራ መደብ ተፈላጊውን መስፈርት የምታሟሉ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት የውጭ ሰሌዳ፤ የቴሌቪዥንና ሬድዮ ቻናሎች ሁሉ እንዲሁም በኮርፖሬሽኑ ድህረገፅና ፌስ ቡክ በሚገልፁት የምዘገባ ቀናት ማለትም ከሀሙስ ጥቅምት 20 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ለአምስት የስራ ቀናት ሰው ኃይል ምልመላና መረጣ ቡድን ቢሮ ቁጥር 1020 በመቅረብ ወይም ለወካይ በመላክ መመዘገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የስራ መደቡ መጠሪያ - የሰው ሀብት ዳታ ኢንኮደር
ከፍታ ደረጃ - VI
ብዛት - አንድ
ደመወዝ - 8166.00
የስራ ቦታ - የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዋና መ/ቤት ሰው ሀብት ሥራ አመራር እና ልማት ዲቪዥን
የቅጥር ሁኔታ - በኮንትራት ሆኖ በየጊዜው የሚታደስ
የትምህርት ደረጃ እና አግባብነት ያለው የስራ ልምድ - በኮምፒውተር ሳይንስ፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በስታትስቲክ፣ ማናጅመንት ኢንፎርሜሽን ሲስተምና በተመሳሳይ ዲግሪ፣ ኮሌጅ ዲፕሎማ፣ቴክኒክ ሙያ ዲፕሎማ የተመረቀ/ች በዳታኢንኮደርነት የሰሩበት የስራ ልምድ ብቻ የሚያዝ ሆኖ
› ለመጀመሪያ ዲግሪ የ2 ዓመት የሥራ ልምድ
› ለኮሌጅ ዲፕሎማ /10+3 / ደረጃ 4 የ4 ዓመት የሥራ ልምድ
› ለቴክኒክና ሙያ ዲፕሎማ / 10+2 የ6 ዓመት የሥራ ልምድ
ማሳሰቢያ
1. ይህ ማስታወቂያ በሬድዮና በቴሌቪዥን ከተነገረበት የመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ባሉት አምስት ተከታታይ የስራ ቀናት ወስጥ የአመልካቾች ምዝገባ በዋናው መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1020 ሰው ኃይል ምልመላና መረጣ ቡድን አማካኝነት ይሆናል ::
2. ከውጭ ሀገር የተገኘ ማንኛውም የትመህርት ማስረጃ ለምዝገባ ሲቀርብ ከሚመለከተው እውቀናካለው ህጋዊ ተቋም የአቻ ገመታ ማስረጃ ማቅረብና መያያዝ ይኖርበታል::
3. የከፍተኛ የትምህርት ወጪ መጋራት የሚመለከታቸው አመልካቾች ለምዝገባ ሲቀርቡ ከተምሩበት ተቋም የተሰጣቸውን የዕዳ መግለጫና ተቀጥረው ሰርተው ከሆነ የከፈሉትን መጠን የሚያሳይ ማስረጃ ይዘው መቅረብ ይጠብቅባቸዋል::
4. ከደረጃ ሁለት እስከ ደረጃ አምስት የሚጠይቁ የትምህርት ማሰረጃዎች ለምዝገባ የሚያገለግሉት ለቀረበው ደረጃ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፈተና ተወስዶ የብቃት ሰርተፍኬት / ሲ.ኦ.ሲ/ ሲቀርብ ብቻ ነው::
5. አመልካቾች ለምዝገባ ሲቀርቡ ዋናውን የትምህርትና የስራ ልምድ ማስረጃዎቻቸውን ከማይመለስ አንዳንድ ፎቶ ኮፒ ጋር ማቅረብ አለባቸው
6. አመልካቾች ምዝገባውን ለማካሄድ በአካል መጥተው ወይም ዋናውንና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ማስረጃዎችቻቸውን በተወካይ በመላክ የተዘጋውን ፎርም መሙላት ይጠበቅባቸዋል::
7. ቀጥታ አግባብነት ካለው የትምህርት ዝግጅትና የስራልምድ ውጭ ለምዝገባ የሚቀርቡ ሌሎች ማስረጃዎች ተቀባይነት አይኖራቸውም::
8. ለምዝገባ በአመልካቾች የሚቀርቡ የስራልምድ ማስረጃዎች የሰራ ልምድ ማስረጃውች የስራልምዱ የተገኘበትን የስራ መደብ ደመወዝ ከመቼ እስከመቼ እንደሰሩና ግብር የተከፈለባቸው እነደሆኑ መግለፅ አለባቸው::
9. የፈተና ጊዜ በውስጥ ማስታወቂያ ወይም በሬዲዮና በቴሌቪዥን አማካኝነት የሚገለፅ ይሆናል ::
10. አመልካቾች ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ከፈለጉ በቢሮ ስልክ ቁጥር 0115172556 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ ::
11. ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ ::
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን