Ethio Job Vacancy
45.3K subscribers
23.2K photos
63 videos
157 files
19.2K links
አዳዲስ እና ወቅታዊ የሥራ ቅጥር ማስታወቂያዎችን ከተለያዩ ጋዜጦችና ድረ ገጾች ለሥራ ፈላጊዎች መረጃ መስጠት ነው።
Post New Job vacancies to Who are looking jobs.
Group discussion https://t.me/+uGe3tVg5jF4yZjk0
Download Telegram
ክፍት የሥራ መደብ ማስታወቂያ
ጥቅምት 16/2012 (27 October 2019)
Advert on Fortune
Independent News and Media PLC
1 - ቦታ ልምድ ላለው/ላላት
ክፍት የሥራ መደብ ማስታወቂያ
ክፍት የሥራ መደብ ማስታወቂያ
ክፍት የሥራ መደብ ማስታወቂያ
ኑ ለሁላችን የምትበጅ ሀገር እንገንባ!
Koottaa Biyya Hunda Keenyaa Toltu Ijaarraa!
ሰላም ለሀገራችን ኢትዮጵያ ይሁን።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር።
💚💛
🙏🙏🙏
Good morning Ethiopia.....
Public Health Officer
West Gonder- Metema
New Job Vacancy
ለወገን ደራሽ ወገን ነው!
ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ
የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር
ጠቃሚ መልእክት......

"ስራ አጥን ዱላ አሸክሞ ማዞር ቀላል ነው። ይኸኛውን ፎቅ ውሰደው፣ ያኛውን ከተማ ውረር እያሉ ያልበሰለንና ነገ ምን ሊከሰት እንደሚችል መገመት የማይችልን ጎረምሳ አቧድኖ መንዳት ይቻል ይሆናል። ምን አልባት የምትቆሰቁሰው እሳት ዛሬ ላይ የሚያቃጥለው ዘሬ አይደሉም ያልካቸውን ሠዎች ብቻ ሊሆን ይችላል። ነገ ከነገ ወዲያ ግን ዳፋውን እንደ ትኩስ ድንች መዳፍህ ላይ ታገኘዋለህ። ያኔ ከሰው ጋር ተስማምቶ እንዳይኖር መቀስቀስህ ሊቆጭህ ይችል ይሆናል። ዳሩ ግን እረፍዷልና መመለስ አትችልም። ያኔ አንተን አያድርገኝ...!

ከሰሜኑ ክፍል የመጡ የገበሬ ልጆችን ተመልከት። ቀኑን ሙሉ ፀኃይ አናታቸውን እየበሳቸው ለ15 ሳንቲም ትርፍ የብሄራዊ ሎተሪን ካዝና ሲሞሉ ይውላሉ። ማታ ላይ ተመስገን ብለው ቤታቸው ገብተው ይተኛሉ። ሲነጋ ለሌላ ዙር መንከራተት ፈጣሪያቸውን ሠላም አውለኝ ብለው ይነሳሉ። ባለ ኃብትነት የሚጀምረው እንደዚህ ካለው ሥራ ወዳድነት መሆኑን ያውቃሉና!

ወደ 22 አካባቢ ጎራ በልና ተመልከት እስቲ። መንደሪን የመሰሉ ቆነጃጅት ከጀበና ቡና እና ከሽሮ ድንፋታ ጋር ታግለው ለእለት ጉርሳቸው ለዓመት ልብሳቸው ችለው ራሳቸውን ያስተዳድራሉ። መበልጸግ እንደዚህ ካለው ስራ እንደሚጀምር ያውቃሉና እሳቱን መታገስ አይከብዳቸውም!

ከተማውን የሞሉትን ከደቡብ ኢትዮጵያ የመጡ ልጆችን ተመልከት። ግማሹ ጫማ ሲያጸዳ፣ ገሚሱ ጀብሎ ተሸክሞ ከፖሊስ ጋር ቶም እና ጀሪ ስታይል ሲጫወት፣ ገሚሱ ቡሉኬት ሲያቀብል፣ አሸዋ ሲያቦካ፣ ገሚሱ ቁጢት ቋጥሮ ሸማን ከገላ ጋር ሲያዋድድ ይውላል። በሁለትና ሶስት አመታት ካለበት ደረጃ ከፍ ብሎ ለሌላ ስራ ራሱን ሲያዘጋጅ ታገኘዋለህ። ስራ ክቡር መሆኑን ያምናሉና!

ምን አልባት ዛሬ በለው ፍለጠው እያልክ በክፍያ የምትቀሰቅሰው ወጣት ለአንተ ትዕዛዝ ሲሯሯጥ በጊዜው ሳይሰራበት ነገ ተወዳድሮ ማሸነፍ ሲያቅተው በማንነቴ ምክንያት ነው ብሎ ለሌላ ዙር ትግል ላለመዳረጉ እርግጠኛ መሆን አትችልም። ጎረምሳን ቀስቅሶ የተገነባን ነገር ማውደም ቀላሉ ሥራ ነው። ለሥራ አጦች የሥራ እድል መፍጠር ግን ከባድ ነው። ግጭትን እንደ ገቢ ምንጭ የምትቆጥር ነህና የሚጋጭህ ብታጣ እንኳን ከራስህ ጋር ትጋጫለህ። የመኖር ህላዌህ እንደ እሳት ከግጭት ጋር የተቆራኘ ነህና ግጭትን ስትሰብክ ውለህ ስትሰብክ ታድራለህ!

በመጨረሻም አደብ መግዛቱ ትርፉ የጋራ መሆኑን አሥረግጠን እንናገራለን። በለው ቁረጠው እያሉ ወጣቱን መቀስቀስ ቀላል ስለሆነ ወደ መጨረሻው ግድም እንደርስበታለን። ከዚያ በፊት መግባባት የሚያስችል ቀጭን መንገድ ካለን እሱን እናስስ!

ሰላም ለሰው ልጆች ሁሉ!"

^^^^
Via ጋሻው መርሻ