Ethio Job Vacancy
46.1K subscribers
23.2K photos
63 videos
157 files
19.5K links
አዳዲስ እና ወቅታዊ የሥራ ቅጥር ማስታወቂያዎችን ከተለያዩ ጋዜጦችና ድረ ገጾች ለሥራ ፈላጊዎች መረጃ መስጠት ነው።
Post New Job vacancies to Who are looking jobs.
Group discussion https://t.me/+uGe3tVg5jF4yZjk0
Download Telegram
ዕለተ ሰንበት አዲስ ዘመን መስከረም 18 ቀን 2012 ዓ.ም

External Vacancy Announcement

Addis Ababa University Invites Committed Experienced &Competent Applicants for the following Position.
Interested Applicants.

• Should submit their letter of application stating the position they are apply, original and one copy of their credentials including transcripts and degrees.

• Registration date: with in 7 working days after the date of this advertisement.

• Place of registration; Addis Ababa University, main campus Human Resource & Development Director Office number one.

• Work place: Addis Ababa University, Aklilu lemma pathobiology

• For more information Tel. 0111- 22-59- 55

Addis Ababa University
ዲስ ዘመን ቅዳሜ መስከረም 17 ቀን 2012 ዓ.ም

ክፍት የስራ መደብ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከታች በተገለፁት የስራ መደቦች መስፈርቱን የሚያሟሉ አመልካቾችን አወዳድሮ በቋሚነት
ለመቅጠር ይፈልጋል፡፡

ማሳሰቢያ ፡-
1. የቅጥር ሁኔታ:- በቋሚነት
2. ደመወዝ: በድርጅቱ ስኬል መሰረት
3. መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች ብሔራዊ ቲያትር ወይም አዋሽ ባንክ ዋናው መ/ቤት ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋናው
መ/ቤት 1ኛ ፎቅ ሰራተኛ ምደባ ቢሮ ዋናውን እና የማይመለስ ኮፒ የትምህርት እና የስራ ልምድ ማስረጃ ይዛችሁ በመቅረብ ይህ
ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል
ጤናማ ለምኖ አዳሪዎች Vs ጎዳና አዳሪዎች - [ገመና ]

#ETHIOPIA | • በልመና የሚተዳደሩ ሰዎች ሦስተኛ ዲግሪ ካላቸው መምህራን እኩል ገቢ ያገኛሉ
• በአዲስ አበባ ልመና የሚተዳደሩ ሰዎች በቀን እስከ 700 ብር ገቢ ያገኛሉ

• መምህር - አብዱሰላም ከማል Vs አቶ ጥላዬ ዘላለም

በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ የስነልቦና መምህርና በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በማህበራዊ ስነልቦና የሦስተኛ ዲግሪ የመመረቂያ ጽሁፋቸውን በአዲስ አበባ በአስሩ ክፍለ ከተሞች “በጤናማ ለምኖ አዳሪዎች” ላይ እየሰሩ ያሉት አቶ አብዱሰላም ከማል፤ ስለለማኞች የገቢ መጠን ባደረጉት ጥናት ከዩኒቨርሲቲ መምህራን ዶክተሮችና ሚኒስቴሮች እኩል ወርሃዊ ገቢ እደሚያገኙ ተገንዝበዋል።

አንድ ጤነኛ ለማኝ ምንም ስራ አልሰራም ከተባለ በቀን ከ100 እስከ 200 ብር ያገኛል። ይህም አንድ ለማኝ በወር ምንም አልሰራም ከተባለ ዝቅተኛ ገቢው 3ሺ ብር መሆኑን ያሳያል። ጤነኛ ለማኞች የሚያገኙት ዝቅተኛ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ ካለው የመንግስት ተቋም ጀማሪ ባለሙያ ይበልጣል።

ለማኞቹ ጥሩ ሰሩ ሲባል በቀን ከ600 እስከ 700 ብር ያገኛሉ። በወር ውስጥ ከፍተኛ የሚባል ገቢያቸው 12ሺ ብር ይደርሳል ማለት ነው።

መምህሩ “እኔ ሁለተኛ ዲግሪ ያለኝ የዩኒቨርሲቲ መምህር ነኝ። ተቆራርጦ የሚደርሰኝ ወርሃዊ ደመወዝ 8ሺ ብር አካባቢ ነው። በጥናት እንዳረጋገጥኩት በርካታ ለማኞች በደመወዝ እኔን ይበልጡኛል። ከፍተኛ ገቢ የሚያገኙ ለማኞች ሦስተኛ ዲግሪ ካላቸው የዩኒቨርሲቲ መምህራን የተጣራ ወርሃዊ ገቢ ጋር የሚስተካከል ደመወዝ ያገኛሉ” ማለት ነው። ይህን ሁኔታ ማስተካካያ ካልተደረገበት በርካታ ለማኞችን ወደ ጎዳና ይጠራል ሲሉም አስጠንቅቀዋል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሶሻል አንትሮፖሎጂ ሁለተኛ ዲግሪ መመረቂያ ጽሁፋቸውን “በጎዳና አዳሪዎች” ላይ መሰረት በማድረግ እየሰሩ ያሉት ተመራማሪ አቶ ጥላዬ ዘላለም ‹‹ ጎዳና አዳሪነት በዓለም ላይ የኑሮ ዘይቤ ሆኖ መጥቷል ፡፡ ጎዳና ተዳዳሪዎች የእራሳቸው ባህልና ወግ እየያዙ መኖር ጀምረዋል። የህይወትን ፈተናና የሚያልፉበትና የዕለት ጎርሳቸውን የሚያገኙበት ሆኗል።
እንደምን አደርሽ እማማ ኢትዮጵያ?
ሰላም ላንቺ ይሁን
💚💛
🙏🙏🙏
Fake News Alert

የከፍተኛ ትምሕርት ተቋማት የአካዳሚክ ሠራተኞች የዕድገት መሠላልና የደሞዝ ስኬል ማሻሻያ ተደረገ በሚል በማኅበራዊ "ሚዲያ" የሚሠራጨው መረጃ ሐሰት መሆኑን የሣይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።
ለሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ነባርና አዲስ ገቢ ተማሪዎች፦

ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ በቅድሚያ ለመላው ተማሪዎቹ እንኳን ለ2012 ዓ/ም የትምህርት ዘመን በሰላምና በጤና አደረሳችሁ! አደረሰን እያለ ተማሪዎቹን የመግቢያ ጊዜ ሰሌዳ እንደሚከተለው ያሳውቃል፡፡

1ኛ/ ለዋናው ወይም የሚዛን ግቢ ተማሪዎች የነባር ተማሪዎች መግቢያ ጊዜ መስከረም 26 እና 27/2012 ሲሆን ለአዲስ ገቢ /ፍሬሽ/ የሚዛን ግቢ ተማሪዎች መግቢያ በተመለከተ ደግሞ መስከረም 30 እና ጥቅምት 1 ቀን 2012ዓ/ም መሆኑን ይገልጻል፡፡

2ኛ/ ለቴፒ ግቢ ነባር ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ በሚመለከት ነባር ተማሪዎች መስከረም 30 እና ጥቅምት 1 ቀን 2012 ዓ/ም ሲሆን የቴፒ ግቢ አዲስ ገቢ /ፍሬሽ ተማሪዎች ደግሞ ጥቅምት 3 እና 4 ቀን 2012 ዓ/ም መሆኑን እያሳወቅን ከዚህ ጊዜ ውጭ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የሚተላለፍትን መግለጫዎች በማየት ትክክለኛው የመግቢያ ጊዜ ባለመለየት ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ በመምጣት ከሚደርስባችሁ መጉላላት ራሳችሁን እንድትጠብቁ እናሳስባለን፡፡

በመጨረሻም ዩኒቨርሲቲው ከመላው የአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመሆን ሊቀበላችሁ ዝግጅቱን ሁሉ አጠናቆ የእናንተን መምጣት በጉጉትና በናፍቆት እየጠበቀ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

መልካም የትምህርት ጊዜ!
የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ
• ቂም ስንይዝ ሕዋሳት ይከፋቸዋል!
• ጥላቻ ሲኖረን እያንዳንዱ ሕዋሶቻችን ተጎጂ ናቸው!

"አስተሳሰባችን ሕይወታችን ነው። አስተሳሰባችን ሥሜታችንን ይፈጥራል። ሥሜታችን ደግሞ ወደ ድርጊት ይለወጣል። እንግዲህ ድርጊታችን ነው ሕይወታችን። ልቤ ውስጥ ቂም ከያዝኩ፤ ሕሊናዬ ውስጥ ጥላቻ ከነገሠ ሕይወቴን ያቆሽሸዋል። የእኔ ሕይወት ደግሞ የአንተን ሕይወት ስለሚነካ የእኔ መቆሸሽ ለአንተም ይተርፋል። ስለዚህ የልቤና አዕምሮዬ መቆሸሽ የሚያሳፍረኝ ጊዜ ይመጣል ብዬ አስባለሁ።"
ዶ/ር ሠላም አክሊሉ (በጤና ይስጥልን!)
የዋሽንግተን ፖስት ዘገባ እንደሚያሳየው አትሌቶች ቢዋሀዱም ተፎካካሪ ደጋፊዎች ግን የኢትዮጵያን መከፋፈል አሳይተዋል ይላል።‼️
ያሳዝናል
ኢትዮጵያዊነት ይለምልም
ዘረኝነት ይውደም
ቅር ያለው ቅራሪ ይጠጣ
#የመከነ_ትውልድ
ቀነኒሳ በቀለ ስለ ኢትዮጵያ..

"እናት ሀገር ኢትዮጵያ
እናት ሀገር ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ....... የኛ መመኪያ።"
የጎንደር ከተማ ውሀ ተመርዟል?‼️

የከተማው ውሀ እና ፍሳሽ አገልግሎት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሀይማኖት በለጠ ከደቂቃዎች በፊት በስልክ የነገሩኝ:

"በሶሻል ሚድያ የሚናፈሰውን ይህን ወሬ ሰምተነዋል። ነገር ግን ወሬው የሀሰት እና ህዝብን ለመረበሽ የተሰራጨ ነው። ይህን እያሰራጨ ያለው የተደራጀ ሀይል ነው። ሁሌ ግርግር ሲፈጠር እንዲህ አይነት የሀሰት ወሬ እየተለመደ ነው። ውሃው እንደሁሌው የተደራጀ የ24 ሰአት ጥበቃ እየተደረገለት ነው። ምንም አይነት የተፈጠረ ችግር የለም፣ በላቦራቶሪ ተጣርቶም ችግር እንደሌለበት ተረጋግጧል። በአካባቢው ሚድያ ዛሬ ጠዋት መልእክት እናስተላልፋለን።"

©Eliyas Meseret
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ሠልጣኝ ኦፊሰርነት ተወዳደራችሁ ያለፋችሁ ስም ዝርዝር