Ethio Job Vacancy
46.1K subscribers
23.2K photos
63 videos
157 files
19.5K links
አዳዲስ እና ወቅታዊ የሥራ ቅጥር ማስታወቂያዎችን ከተለያዩ ጋዜጦችና ድረ ገጾች ለሥራ ፈላጊዎች መረጃ መስጠት ነው።
Post New Job vacancies to Who are looking jobs.
Group discussion https://t.me/+uGe3tVg5jF4yZjk0
Download Telegram
መስከረም 09/2012 (20 September 2019)
Advert on Addis Zemen
Addis Ababa Science and Technology University (AASTU)
128 - ቦታዎች በ0አመት 27 - ቦታዎች ልምድ ላላቸው
የተከበራችሁ የ Ethio Job Vacancy የሥራ ማስታወቂያ ቴሌግራም ቻናል ተከታታዮች
በዚህ ሳምንት በተለያዬ ምክንያት ማስታወቂያዎችን ፖስት ማድረግ ስላልቻለኩ እስከ መስከረም 19/2012 ድረስ በአማራጭነት ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ በመጫን የፌስቡክ ፔጁን መከታተል ትችላላችሁ።
Invite your friends to follow and look new Job vacancies via Facebook page….

Join here: [https://www.facebook.com/groups/2085932031709757/](https://www.facebook.com/groups/2085932031709757/)
ዛሬ ተመልሻለሁ
በተቻለኝ አቅም ያለፉትን እና አዳዲስ የወጡ የሥራ ማስታወቂያ ፖስት አደርጋለሁ
🙏🙏🙏
አዲስ ዘመን ሐሙስ መስከረም 15 ቀን 2012 ዓ.ም
አዲስ ዘመን ረቡዕ መስከረም 14 ቀን 2012 ዓ.ም

Vacancy Announcement

Woldia University Faculty Social Science And Humanites
አመልካቾች የሚያሟሏቸው መስፈርቶች

1. ከታወቀና ተቀባይነት ካለው የትምህርት ተቋም የተመረቁበትን የትምህርት ማስረጃ ዋናውን እና የማይመለስ
ኮፒ፤

2. የመጀመሪያ ዲግሪ አመልካቾች እድሜ 35 (ሰላሳ አምስት) አመት በታች የመመረቂያ ነጥብ ለሴቶች 3.00
እና በላይ ለወንዶች 3.25 እና በላይ እንዲሁም ለአካል ጉዳተኞች 2.75 ከዚያ በላይ ለታዳጊ ክልልና አርብቶ
አደር አካባቢ ነባር ብሔረሰብ ተወላጅ ተማሪዎች 2.75ና ከዚያ በላይ ከአንድ በላይ የበጎ ልዩነት (Affirmative
Action) ተጠቃሚዎች 2.50ና ከዚያ በላይ ለሁሉም የህክምና ዲግሪ (የሰውና የእንስሳ) 3.00 እና ከዚያ በላይ
መሆን ይኖርበታል፡፡

3. የሁለተኛ ዲግሪ እና በላይ አመልካቾች እድሜ 45 (አርባ አምስት) አመት በታች የመጀመሪያ ዲግሪ የመመረቂያ
ነጥብ ለሴቶች 2.75 ለወንዶች 3.00 ለአካል ጉዳተኞች 2.50 እና በላይ፣ የሁለተኛ ዲግሪ የመመረቂያ ነጥብ
ለሴቶች 3.35 ለወንዶች 3.50 ለአካል ጉዳተኞች 3.15ና በመጀመሪያ ዲግሪ ውጤታቸው 2.50ና ከዚያ በላይ
ለታዳጊ ክልልና አርብቶ አደር አካባቢ ነባር ብሔረሰብ ተወላጅ ተማሪዎች 3.15ና ከዚያ በላይ የነበራቸው፣
ከአንድ በላይ የበጎ ልዩነት (Affirmative Action) ተጠቃሚዎች 3.10ና ከዚያ በላይ እንደዚሁም በመጀመሪያ
ዲግሪ ውጤታቸው 2.50ና ከዚያ በላይ የነበራቸው እንዲሁም የመመረቂያ ጽሁፍ ውጤት (B+ ወይም
VeryGood) እና በላይ መሆን ይኖርበታል፤

4. ለቤተ-ሙከራ ቴክኒካል አሲስታንት ለሚቀጠሩ ዲፕሎማ ያላቸው በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት የተመረቁ የብቃት ማረጋገጫ “CoC” ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

5. አመልካቾች የሚወዳደሩበትን የትምህርት መስክ እና አካዳሚክ ማዕረግ በማመልከቻ እና እንዲሁም የተሟላ “CV” አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፤

6. የስራ ልምድ ለሚጠይቁ የትምህርት መስኮች ላይ የሚቀርበው የሥራ ልምድ ማስተማር የስራ ልምድ መሆን

7. አመልካቾች የስራ ልምዳቸውን፣ የትምህርት ማስረጃቸውንና አስፈላጊ ዶክመንቶቻቸውን በመያዝ በአካል በመቅረብ ወይም በወኪል መመዝገብ ይቻላል ወይም ከታች በተገለፀው የፖስታ አድራሻ በመላክ መመዝገብ ይቻላል፣

8. ለመጀመሪያ ዲግሪ አመልካቾች የማጣሪያ የጽሁፍ ፈተና ይሰጣል፡፡

9. ለሁሉም አመልካቾች ማስተማር የሚያስችላቸውን ብቃት በመረጡት ርዕስ ላይ የክፍል ውስጥ የማስተማር ሙከራ ያደርጋሉ፤ ለቃለ-መጠይቅም ይቀርባሉ፤

10. ከላይ በተዘረዘሩት ሁሉም የትምህርት መስኮች የተሻለ የትምህርት ደረጃ ያለው አመልካች ቢገኝ ቅድሚያ ይሰጠዋል፡፡

11. በውድድሩ የሚያሸንፉ አመልካቾች ለቅጥር በሚቀርቡበት ወቅት ከ8ኛ ክፍል ጀምሮ ያለውን የትምህርት ማስረጃ እና ሥራ ላይ ከሆኑ ከሚሰሩበት መ/ቤት መልቀቂያ እና የስራ ልምድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

12. የመመዝገቢያ ጊዜ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ቀጥሎ ባሉት ተከታታይ 10 (አስር) የስራ ቀናት ብቻ ይሆናል፤

13. የመመዝገቢያ ቦታ ወልድያ ዩኒቨርሲቲ ጀነቶ በሚገኘው ዋናው ጊቢ የሠው ሀብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ህንፃ ቁጥር AD-6 ቢሮ ቁጥር 04

14. ምዝገባው እንደተጠናቀቀ ምልመላ ተካሂዶ የፈተና ፕሮግራምና የተፈታኝ ስም ዝርዝር በዩኒቨርሲቲው ድህረገፅ ይገለፃል፡፡

ማሳሰቢያ፡- አመልካቾች ለምዝገባ በምትቀርቡበት ወቅት የ8ኛ ክፍል ካርድ መያዝ የሚጠበቅባችሁ መሆኑን እናሳስባለን፡፡

ስልክ ቁጥር፡- 0335400840/ 0334310871 ፖ.ሳ.ቁጥር፡- 400

የወልድያ ዩኒቨርሲቲ
አዲስ ዘመን ሐሙስ መስከረም 15 ቀን 2012 ዓ.ም
አዲስ ዘመን ሐሙስ መስከረም 15 ቀን 2012 ዓ.ም
ለሌሎችም Share ማድረግ አትርሱ
NEW JOB VACANCY
ADVERT ON
THE ETHIOPIAN HERALD THURSDAY 26 SEPTEMBER 2019