Ethio Job Vacancy
46.1K subscribers
23.2K photos
63 videos
157 files
19.5K links
አዳዲስ እና ወቅታዊ የሥራ ቅጥር ማስታወቂያዎችን ከተለያዩ ጋዜጦችና ድረ ገጾች ለሥራ ፈላጊዎች መረጃ መስጠት ነው።
Post New Job vacancies to Who are looking jobs.
Group discussion https://t.me/+uGe3tVg5jF4yZjk0
Download Telegram
ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ
ነሐሴ 28/2011 (03 September 2019)
Advert on Addis Zemen
Hawassa University
89 - ቦታዎች በ0አመት 2 - ቦታዎች ልምድ ላላቸው

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ለሁለተኛ ጊዜ ከዚህ በታች በተጠቀሰው የሥራ መደብ ላይ መምህራንን ለመቅጠር ይፈልጋል፡፡
ማሳሰቢያ መመዝገቢያ ቀናት፣
1. በሌክቸረር የሥራ መደብ ላይ የምትመዘገቡ አመልካቾች የሁለተኛ ዲግሪ ነጥባችሁ ለወንዶች 3.50 እና ከዚያ በላይ እንዲሁም በመጀመሪያ ዲግሪ ውጤታችሁ 3.00 እና ከዚያ በላይ መሆን ይጠበቅባችኋል፡፡ ለሴቶች የሁለተኛ ዲግሪ 3.35 እና ከዚያ በላይ እንዲሁም በመጀመሪያ ዲግሪ ውጤታችሁ 2.75 እና ከዚያ በላይ መሆን ይጠበቅባችኋል፡፡
• ለአካል ጉዳተኞች የሁለተኛ ዲግሪ 3.15 እና ከዚያ በላይ እንዲሁም በመጀመሪያ ዲግሪ ውጤታቸው 2.50 እና ከዚያ በላይ መሆን ይጠበቅባችኋል፡፡
• ለታዳጊ ክልልና አርብቶ አደር አካባቢ ነባር ብሄረሰብ ተወላጅ ተማሪዎች የሁለተኛ ዲግሪ 3.15 እና ከዚያ በላይ እንዲሁም በመጀመሪያ ዲግሪ ውጤታችው 2:50 እና ከዚያ በላይ መሆን ይጠበቅባችኋል፡፡
• ለረዳት ምሩቃን አመልካቾች ለወንዶች 3.25 እና ከዚያ በላይ መሆን ይጠበቅባችኋል፡፡ ለሴቶች 3.00 እና ከዚያ በላይ እንዲሁም ለአካል ጉዳተኞች 2.75 እና ከዚያ በላይ መሆን ይጠበቅባችኋል፡፡ ለታዳጊ ክልልና አርብቶ አደር አካባቢ ነባር ብሄረሰብ ተወላጅ ተማሪዎች 2.75 እና ከዚያ በላይ ለሁሉም የህክምና ዲግሪ (የሰውና የእንስሳ) 3.00 እና ከዚያ በላይ መሆን ይጠበቅባችኋል፡፡
2. ለሥራ መደቡ የተቀመጠውን መስፈርት የምታሟሉ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 (ሰባት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ አዲስ አበባ አሜሪካን ኤምባሲ ፊት ለፊት ባለው በፌዴራል ትምህር ትሚኒስቴር የስርዓተ ትምህርት ቢሮ ቁጥር 352 ወይም ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በዋናው ግቢ የሰው ሀብት ሥራ አመራር ዳይሬክቶሬት ባለው በአካል በመገኘት ወይም በተወካይ ወይም በፋክስ Fax No. 0462205187) መመዝገብ ይቻላል፡፡
3. ለመምህራን የቤት አበል እንደየ ደረጃው የሚከፈል ይሆናል፡፡
4. ደመወዝ በከፍተኛ ትምህርት ተቋም የደመወዝ ስኬል መሠረት ነው፡፡
5. ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ፡፡
6. የሥራ መደቡ የሚገኘው ሀዋሳ ከተማ
7. ዝርዝር አፈጻጸሙ ከትምህርት ሜኒስቴር የአገር ውስጥ -መምህራን ምልመላና ቅጥር ልማት ስርዓት ለመደንገግ በወጣው መመሪያ መሠረት ይከናወናል፡፡
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
Bedigame post yetederege new, lemayitayachihu,
ክፍት የሥራ መደብ ማስታወቂያ
ነሐሴ 28/2011 (03 September 2019)
Advert on Addis Zemen
1 - ቦታ በ0አመት 6 - ቦታዎች ልምድ ላላቸው
በኢትዮጵያ የአካባቢና የደን ምርምር ኢንስቲትዩት የእንጨት ቴክኖሎጂ ምርምር ማዕከል ቀጥሎ በተጠቀሱት የሥራ መደቦች ላይ የሥራ ልምድ ያላቸው/የሌላቸውን ሥራ ፈላጊዎችን አወዳድሮ በቋሚነት ለመቅጠር ይፈልጋል፡፡
ማሳሰቢያ፤
1. የምዝገባ ጊዜ፤ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ብቻ ይሆናል፡፡
2. የምዝገባ ቦታ፡- ሳሪስ ሆራይዞን ጎማ ፋብሪካ /ቆዳ ፋብሪካ አካባቢ በሚገኘው በማዕከሉ የሰው ሀብት አስተዳደር ቢሮ ስ.ቁ. 0118898772 ነው፡፡
3. አመልካቾች ለመወዳደር መያዝ ያለባቸው ፤የማመልከቻ ፎርም የተዘጋጀ ሲሆን ፣ካልኩሌም ቬት(CV)፣የተሟላ የትምህርትና የሥራ ልምድ ማስረጃ ዋናውን ከማይመለስ ፎቶ ኮፒ ጋር በማቅረብ በግንባር በመቅረብና በወኪልና በፖስታ ሳ.ቁ. 2322 መመዝገብ ይችላሉ፡፡
4. የግል ተቋማት የተሰጠ የሥራ ልምድ ማስረጃ የሥራ ግብር የተከፈለ መሆኑን መግለጽ አለበት፡፡
5. አመልካቾች በቂ የስልክ አድራሻ ፤የሥራ መደብ፤ደረጃ፤የማዕከል ስም በተዘጋጀው የማመልከቻ ፎርም ላይ መሙላት ይኖርባቸዋል።
6. ትምህርታቸውን ከደረጃ 1-5 ለተከታተሉ የብቃት ማረጋገጫ ሲ.ኦ.ሲ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
7. በተጠቀሱ የሥራ መደቦች ላይ ተወዳድረው ፈተናውን ያለፉ በአዲስ የሥራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን (JEG) በተፈቀዱ መደቦች ትይዩ ይመደባሉ፡፡
8. የፈተና ቀን በውስጥ ማስታወቂያ ይገለጻል፡፡
9. ሴት ተወዳዳሪዎች እንዲያመለክቱ ይበረታታሉ፡፡
በኢትዮጵያ የአካባቢና የደን ምርምር ኢንስቲትዩት የእንጨት ቴክኖሎጂ ምርምር ማዕከል
ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ
ነሐሴ 28/2011 (03 September 2019)
Advert on Addis Zemen
Adama Science and Technology University
89 - ቦታዎች በ0አመት 86 - ቦታዎች ልምድ ላላቸው