Ethio Job Vacancy
46.1K subscribers
23.2K photos
63 videos
157 files
19.5K links
አዳዲስ እና ወቅታዊ የሥራ ቅጥር ማስታወቂያዎችን ከተለያዩ ጋዜጦችና ድረ ገጾች ለሥራ ፈላጊዎች መረጃ መስጠት ነው።
Post New Job vacancies to Who are looking jobs.
Group discussion https://t.me/+uGe3tVg5jF4yZjk0
Download Telegram
ሐምሌ 17/2011 (24 July 2019)
Advert on Reporter
Anbessa City Bus
2 - ቦታዎች ልምድ ላላቸው
የስርቆት ወንጀል በአዲስ አበባ መዲና
ይሕ መልእክት ለሁሉም አዲስ አበቤ ነዋሪ እና የወንጀል መከላከል አካላት ይድረስልኝ።
ሥርቆትን ሙያ ብለው በየጊዜው መልክና አካሔድ በአዳዲስ መልክ ስትራቴጂ እየነደፉ በተለያዩ የአዲስ አበባ ቦታዎች በግለሰብ በቡድን በጨለማ እና በጠራራ ፀሀይ ስርቆት ሲፈፀም ማስተዋል ለአዲስ አበቤ የአደባባይ ሚስጥር ነው። ከዚህ በፊት የነበረው ስርቆት በተለያዩ ተሽከርካሪን በመታገዝ ቦርሳ መንጠቅ እንዲሁም ተሳፋሪ እና ሕዝብ በሚሰበሰብባቸው ቦታዎች በመግባት የተለያዩ የሥርቆት ወንጀሎች ሲፈፀሙ ማየት የተለመደ ነው። እንደሚታወቀው በሞተር ሳይክል የታገዘ ስርቆትን ለመከላከል ሲባል የከተማ አስተዳደሩ በወሰደው እርምጃ የዚህ አይነት ወንጀል የቀነሰበት ቢያንስ መሐል ከተማ ወንጀሉ እንዳይፈፀም የተደረገበት አግባብ ተፈጥሯል።
ነገር ግን አሁን ላይ እጅግ እጅግ አሳሳቢ እና ለአዲስ አበቤ ነዋሪዎች በሰላም ወጥተው በሰላም ለመግባት የሚሳቀቁበት ደረጃ የሚያደርስ አንድ መልኩን ቀይሮ የሚፈፀም ወንጀል አለ።
ይሕ የወንጀል ድርጊትም ሲፈፀም በየቦታው ወንጀሉን ለመፈፀም የሚጠቀሙበት ዘዴ ቢለያይም አንድ የማይቀር ጉዳይ ግን አለ፤ እርሱም ድብደባ አካል ማጉደል እና ማዋከብ ነው።
በተለይ ይሕ የስርቆት ወንጀል አፈጻጸም አንድን ገንዘብ ወይንም ጥሩ ዋጋ ሊያወጣ የሚችል ስልክ አለው ብለው የሚጠረጥሩትን ግለሰብ በመከታተል ከዘራፊ ቡድኖች መካከል አንደኛው ግለሰብ ተነጥሎ የሚዘረፈውን ግለሰብ በመከታተል ከመሬት ተነስቶ መተናኮል ይጀምራል። ዘራፊው ግለሰብ ወዲያውኑ አራስ ነብር ይሆንና አንተ ሌባ እዛ ጋ ታክሲ ውስጥ ስልኬን ልትሰርቀኝ ነበር እኔ ግን እንደሌሎች አይደለሁም ዝም ብዬ አሳለፍኩህ ሌባ ሌባ እያለ ሲያዋክበው ከቅርብ እርቀት ሆነው ሲከታተሉ የነበሩ የዘራፊው አባላት ተሯሩጠው ያን ምስኪን ግለሰብ ማዋከብ አልፎም ሌባ ሌባ እያሉ በኪሱ ያለውን መዝረፍ ሻንጣ ከያዘም ሻንጣውን መበርበር ቡጢ እና ጠረባ በየተራ መፈፀም ይጀምራሉ። የአካባቢው ሰውም ሌባ ተይዞ ነው አቅምሰው እያለ ባላየ ባልሰማ ይሔዳል። በዚያን ወቅት ተበዳዩ ቢጮህና ፖሊስ ወይንም ነግበኔ ነው ብሎ ለመገላገል የሚገባ ግለሰብ ቢኖርም እነዛ ዘራፊ ቡድኖች ሲሰርቅ እጅ ከፈንጅ ይዘነው ነው ብለው እርሱን ወንጀለኛ ብለው ይፈርጁታል። ወዲያውኑ እነዛ ዘራፊ ግለሰቦችም ከአካባቢው ይሰወራሉ።
ብቻ ምን አለፋችሁ የዚህ ወንጀል ሰለባ የሆኑ ከንብረታቸው መዘረፍ አልፎ ጥርሳቸው፣ አይናቸው፣ በአጠቃላይ አካላቸው የጎደለ ግለሰቦችን ቤት ይቁጠረው።
በመጨረሻም፦
1.ይሕን አዲስ የስርቆት ወንጀል አፈጻጸም ለመከላከል የፀጥታ አካላት በየክፍለ ከተማው ወይንም በየአካባቢው ከማህበረሰቡ ጋር የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ መስራት እና ማህበረሰቡ እንደዚህ አይነት ድርጊት ሲፈጸም ሲያዩ ለማገላገል እና ለፀጥታ አካላት ደብዳቢዎችን እና ተደብዳቢውን አሳልፎ መስጠት እንዳለባቸው ማስገንዘብ፣
2.በየአካባቢው የወረዳው የፀጥታ አስከባሪ ፖሊሶችን ማሰማራት እና በፈረቃ እንዲሰሩ ማድረግ፣
3.የዚህ ወንጀል ሰለባ የሆኑ ግለሰቦች የደረሰባቸውን የወንጀል ድርጊት በአካባቢው በሚገኝ የፖሊስ ወይንም የፀጥታ አካል ሪፖርት ማድረግ። ቢያንስ ወንጀለኞች ባይያዙም ተመሳሳይ ወንጀል እንዳይፈጸም ለፀጥታ አካላት መረጃ ይኖራቸዋል።
4. ሚዲያዎች በዚህ የወንጀል ድርጊት ሰለባ የሆኑ ግለሰቦችን በማፈላለግ ለሕብረሰቡ ማስተላለፍና ግንዛቤ መፍጠር ቢቻል፤ እንዲሁም የወንጀሉ ሰለባ የሆናችሁ ግለሰቦች ለሚዲያ አካላት መረጃ መስጠት ቢቻል መልካም ነው እላለሁ።
በዚህ አጋጣሚ ሲሰርቅም ሆነ ሌላ የወንጀል ድርጊት ፈፅሟል ተብሎ የሚጠረጠር ግለሰብ ቢገኝ ማንም ግለሰብም ይሁን የፀጥታ አካል ወንጀለኛ ተብሎ የተጠረጠረ ግለሰብ ለማምለጥ እስካልሞከረ ድረስ የአካልም ሆነ የሞራል በደል ሊፈፀምበት እንደማይችል በሕግ ተደንግጓል። ስለዚህ ሌባ ሌባ እያለ የሚደበድብ ግለሰብ ካለ ደብዳቢውም ወንጀለኛ ስለሆነ ለሕግ መቅረብ አለባቸው። ወንጀለኛን መቅጣት እና ማረም የሚችል ሥልጣን የተሰጣቸው የሕግ አካል አሉ።
ሕብረተሰበቡም ይሕን አጭር መረጃ ተመርኩዞ ወንጀለኞችን ለፀጥታ አካላት አሳልፎ በመስጠት ተመሳሳይ ወንጀል እንዳይፈፀም በመከላከል ማንኛውም ግለሰብ ያለምንም ስጋት በሰላም ወጥቶ በሰላም ያሰበውን ስራ አከናውኖ የሚኖርባት ከተማ መፍጠር እና የከተማዋን ገፅታ መጠበቅ የሁሉም ነዋሪ ኃላፊነት መሆን አለበት።
ነግበኔ ነውና
ወንጀልን በጋራ እንከላከል።
ሐምሌ 17/2011 (24 July 2019)
Advert on Reporter
Tefzer Business Center
2 - ቦታዎች ልምድ ላላቸው
ሐምሌ 17/2011 (24 July 2019)
Advert on Reporter
Humedica Ethiopia
1 - ቦታ ልምድ ላለው/ላላት
ሐምሌ 17/2011 (24 July 2019)
Advert on Reporter
Humedica Ethiopia
1 - ቦታ ልምድ ላለው/ላላት
ሐምሌ 17/2011 (24 July 2019)
Advert on Reporter
Weibo Xu Electronics Company
3 - ቦታዎች በ0አመት 15 - ቦታዎች ልምድ ላላቸው
ሐምሌ 17/2011 (24 July 2019)
Advert on Reporter
Alek Terrazzo Factory PLC
3 - ቦታዎች ልምድ ላላቸው
ሐምሌ 17/2011 (24 July 2019)
Advert on Reporter
Wegeret Construction
9 - ቦታዎች ልምድ ላላቸው
ሐምሌ 17/2011 (24 July 2019)
Advert on Reporter
Impact Printing AND Graphics
1 - ቦታ በ0አመት 6 - ቦታዎች ልምድ ላላቸው
ሐምሌ 18/2011 (25 July 2019)
Advert on The Ethiopian Herald
Ministry of Environment, Forest and Climate Change
1 - ቦታ ልምድ ላለው/ላላት