Ethio Job Vacancy
45.3K subscribers
23.2K photos
63 videos
157 files
19.2K links
አዳዲስ እና ወቅታዊ የሥራ ቅጥር ማስታወቂያዎችን ከተለያዩ ጋዜጦችና ድረ ገጾች ለሥራ ፈላጊዎች መረጃ መስጠት ነው።
Post New Job vacancies to Who are looking jobs.
Group discussion https://t.me/+uGe3tVg5jF4yZjk0
Download Telegram
57 የምግብ ምርት አይነቶችን ህብረተሰቡ እንዳይጠቀም ተባለ።
የኢትዮጵያ የምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን 57 የምግብ አይነቶችን ህብረተሰቡ እንዳይጠቀም አስታውቋል፡፡
ባለስልጣኑ በአዲስ አበባ አደረኩት ባለው የገበያ ጥናት 57 ምርቶች የአምራች ድርጅት ስም፣የተመሰረተበት ቦታ/ሃገር የሌላቸው፣ የመጠቀሚያ ማብቂያ ጊዜያቸው የማይታወቁ ፣የንጥረ ነገር ይዘት የሌላቸውና ባጠቃላይ የአምራች ድርጅቶቻቸው የማይታወቁ እንደሆኑ ገልጧል፡፡
57 ቱ ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው የተከለከሉት ምርት አይነቶች የከረሜላ፣የገበታ ጨው፣የለውዝ ቅቤ፣የማር፣የምግብ ዘይት፣የህፃናት ምግቦች ፣የቪምቶ እንዲሁም የአቼቶ ምርቶች ናቸው ተብሏል፡፡
ባለስልጣኑ በአጥፊዎች ላይ ተገቢውን የእርምት እርምጃ እየወሰድኩ ነው ያለ ሲሆን ህብረተሰቡም የትኛውንም የምግብ ምርት ከገበያ ሲገዛ የተመረተበትና የመጠቀሚያ የአገልግሎት ጊዜውን ትክክለኛነት፣ያለተፋቀና ያልተሰረዘ መሆኑን፣ የአምራች ድርጅቱ ስምና ሙሉ አድራሻ፣የምርት መለያ ቁጥር ያለውና የብሔራዊ የደረጃ ምልክት የለጠፈ መሆኑን ማረጋገጥ እንደሚገባው ባለስልጣኑ ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ አሳውቋል፡፡
የክልል ተቆጣጣሪዎችና በየደረጃው የሚገኙ የቁጥጥር አካላት ምርቶቹን ከገበያ ላይ በአፋጣኝ የመሰብሰብ ስራውን እንዲሰሩ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጥሪውን ያስተላለፈ ሲሆን ህብረተሰቡም መሰል ምርቶችን በገበያ ላይ ካገኘ በአቅራቢያው ለሚገኝ የጤና ተቆጣጣሪ፣ ለፖሊስ አካላትና ወይም በፌደራል ደረጃ ለባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በነፃ የሥልክ መስመር 8482 በመጠቆም እንዲያሳውቅ ባለስልጣኑ ጠይቋል፡፡
የታገዱትን ምርቶች ከስር እንደሚከተለው ተቀምጠዋል።
ምንጭ; ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8
Follow me
ባለስልጣኑ 57 የምግብ ምርት አይነቶችን ህብረተሰቡ እንዳይጠቀም አሳሰበ
አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 3 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ምግብ መድሃኒትና ጤና ክብካቤ
አስተዳደር ቁጥጥር ባለስልጣን 57 የምግብ ምርት አይነቶችን ህብረተሰቡ እንዳይጠቀም
አሳሰበ።
ባለስልጣኑ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ በምግቦቹ ጥራትና ደህንነት
ላይ ባደረገው የገበያ ጥናት የምግብ ምርቶቹ መሰረታዊ የገላጭ የፅሁፍ ክፍተት ያለባቸው፣
የሚመረቱበት ቦታ የማይታወቅ፣ የንጥረ ነገር ይዘት የሌላቸው፣ አምራች ድርጅቶቹ
የማይታወቁ፣ የምርት መለያ ቁጥር፣ የተመረቱበት ጊዜ እና የምርቱ ማብቂያ ጊዜ ገላጽ ፅሁፍ
የሌላቸው ናቸው ብሏል።
ከዚህ ጋር ተያይዞም ምርቶቹን ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸውና ተቆጣጣሪ አካላት ምርቶቹን
በአፋጣኝ ከገበያ ላይ እንዲሰበስቡም ጥሪውን አቅርቧል።
በባለስልጣኑ ህብተረሰቡ እንዳይጠቀማቸው የተከለከሉ የምግብ አይነት ዝርዝሮች፤
የከረሚላ ምርቶች፤ ጆሊ ሎሊፖፕ፣ አናናስ ከረሚላ፣ ኮላስ ከረሚላ፣ ኦሊ ፖፕ፣ ቤስት
ከረሚላ፣ የስ ከረሚላ (ኮፊ ከረሚላ)፣ ማሚ ሎሊ ፖፕ፣ ሳራ ከረሚላ፣ ጃር ሎሊ ፖፕ፣ ጸሃይ
ሎሊ ፖፕ፣ ዩኒክ ሎሊ ፖፕ፣ እንጆሪ ከረሚላ፣ ብርቱካን ከረሚላ፣ ይናቱ ሎሊ ፖፕ እና ሃላዋ
ከረሚላ፤
የማር ምርቶች፤ አፍያ የተፈጥሮ ማር፣ ሪትም ማር እና በላይ ማር፣
የገበታ ጨው፤ ዊዲ፣ ሱላ፣ ናይ፣ ሃያት፣ አቤት፣ በእምነት፣ እናት፣ አባይ፣ አባት፣ ሴፍ እና
ጣዕም የገበታ ጨው
የለውዝ ቅቤ፤ ደስታ፣ አስነብ፣ ኑኑ፣ አቢሲኒያ፣ ብስራት፣ ፈሌ፣ ሳባ፣ አዳ እና አደይ የለውዝ
ቅቤ
የኑግ ዘይት፤ አደይ አበባ እና ቀመር የኑግ ዘይት
አልሚ የህጻናት ምግቦች፤ ምሳሌ የህጻናት ምግብ፣ ኤልሞ የልጆች ምግብ፣ ሂሩት የህጻናት
አጃ፣ ዘይነብ የህጻናት አጥሚት፣ ተወዳጅ ገንቢ የህጻናት አጥሚት፣ ተወዳጅ የህጻናት ሽሮ
እና ፋሚሊ ሃይል ሰጭና ገንቢ የህጻናት ሽሮ፣
ቪንቶ፤ ዴኮ፣ እስፔሻል፣ ዳና፣ ቃና፣ ላራ፣ ዛጎል አቼቶ፣ ናይስ አቼቶ፣ አምቴሳ አቼቶ፣ ማይ አቼቶ፣
መስ አቼቶ እና ቫይኪንግ አቼቶ ምርቶች ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው ታግደዋል።
©FBC
ሐምሌ 03/2011 (10 July 2019)
Advert on Reporter
Et Inclusive Finance Technology Share Company
1 - ቦታ ልምድ ላለው/ላላት
ሐምሌ 03/2011 (10 July 2019)
Advert on Reporter
Chilalo Food Complex
1 ቦታ ልምድ ላለው/ላላት
ሐምሌ 03/2011 (10 July 2019)
Advert on Reporter
Gezund Health Center
2 - ቦታዎች በ0አመት 2 - ቦታዎች ልምድ ላላቸው
ሐምሌ 03/2011 (10 July 2019)
Advert on Reporter
Aarti Steel Plc
21 - ቦታዎች በ0አመት 17 - ቦታዎች ልምድ ላላቸው
ሐምሌ 03/2011 (10 July 2019)
Advert on Reporter
Ethiopian Cathollc Church
3 - ቦታዎች ልምድ ላላቸው