ስካርና ጤና [የእውቀት ጎራ - #ጤና]
በኢትዮጵያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከተ የመጣው የመጠጥ አይነት ብዙ የጤና እና የሥነ-ልቡና ተጽእኖ እንደሚኖረው የሕክምና እና የሥነ-አእምሮ ባለሞያዎች ይናገራሉ። ብዙ የንባብ ቦታዎች ባሌለበት ሀገር ውስጥ፥ መጠጣትና መስከር "ብሔራዊ ጊዜ ማሳለፊያ" ከሆነም ሰነባብቷል። የመጠጥ ኢንዱስትሪውን የሚቃወሙትም ሰዎች ድምጽ በብዙሃኑ የተዋጠ ይመስላል። ይህንን ዐሳብ ይዘን ስንጓዝ፥ ስካር ጋር እንመጣለን። ለመሆኑ ሰው ለምን ይሰክራል? መጠጥ በሚጠጡበትና በሚሰክሩበት ጊዜ በሰውነትዎ ውስጥ ምን እየተካሄደ እንዳለስ ያውቃሉ? የዛሬው የጤና አምዳችን ስካርን ይዳስሳል።
መጠጦችን “አስካሪ” የሚያደርጋቸው ንጥረ-ነገር በሳይንሳዊ ስሙ ኤታኖል (Ethanol) ተብሎ ይጠራል፡፡ ከሁለት ካርቦን አቶሞች፣ ስድስት ሃይድሮጂን አቶሞች እና አንድ ኦክሲጂን አቶም የተሰራ ነው፡፡ ይህ ኤታኖል የተባለ ውህድ በቀላሉ በውሃ ውስጥ መሟሟት የሚችል በመሆኑ በቀላሉ በደም ውስጥ ገብቶ ይቀላቀላል፡፡ እጅግ የሚገርመው ነገር አንድ ሰው አልኮል ሲጠጣና ኤታኖል በደም ውስጥ ገብቶ በፍጥነት መሰራጨት ሲጀምር ሰውነታችን በደማችን ውስጥ አስከፊ መርዝ እንደገባ ያህል በመቁጠር በፍጥነት መራወጥ መጀመሩን ነው፡፡ በአጭር ቋንቋ - ሰውነታችን መጠጥን የሚያየው እንደ መርዝ ነው።
አልኮል በሰውነታችን ውስጥ ሲገባ የመጀመሪያው ምላስ ሰጪ ጉበት ነው። ጉበታችን አልኮል ዲሃይድሮጂኔዝ [Alcohol Dehydrogenase] የሚባል ኢንዛይም በማመንጨት አስካሪ የሆነውን የኤታኖል ንጥረነገር አሴትአልዲሃይድ [Acetaldehyde] ወደሚባል ውህድ ቀጥሎም ደግሞ ወደ አሴቲክ አሲድ [Acetic Acid] ይለውጠዋል፡፡ ይህ እንግዲህ ጉበታችን እንዳንሰክር የሚያደርገው ጥረት ነው፡፡ ጉበታችን ከሚችለው በላይ አልኮል ወደ ደም ውስጥ ሲገባ ግን በፍጥነት በሰውነት ውስጥ መሰራጨት ይጀምራል፡፡
አልኮል ከጉበታችን የመከላከል አቅም በላይ ሆኖ በደም ውስጥ ሲሰራጭ፥ ወደ አእምሯችን ይሄዳል። በዚያም ደግሞ ከተለያዩ የአእምሯችን ክፍሎች መልእክትን የሚቀበሉ የነርቭ ክፍሎች ጋር በመሄድ ራሱን ያጣብቃል፡፡ በዚህም ጊዜ የአእምሮ ፍጥነት መቀዝቀዝ ይጀምራል፡፡ በአእምሮ ውስጥ የሚገኙ ጋባ ሪሴፕተርስ [GABA Receptors] ተብለው ከሚጠሩት ነርቮች ጋር በመሄድ ራሱን ስለሚያያይዝ የአእምሮ ፍጥነት ይበልጡኑ ይቀዘቅዛል - በንግግር ጊዜ የአንደበት መያያዝም ያስከትላል፡፡ ስካር የጀማመረው ሰው መኮላተፍ የሚጀምረው ለዚህ ነው።
በአልኮል መጠጥ ውስጥ የሚገኘው ኤታኖል የተሰኘ አስካሪ ንጥረነገር በሰውነታችን ውስጥ ዶፓሚን እና ኢንዶርፊን የሚባሉት ኬሚካሎች እንዲመነጩ ስለሚያደርግ፤ ብዙ ሰዎች መጠጥ መጣጣት በጀመሩ ከሰላሳ ደቂቃ እስከ አንድ ሰዓት ድረስ የደስታ ስሜት ይሰማቸዋል፡፡ "ሞቅታ" እና "ጨዋታ" የሚጀምረው በዚህ ጊዜ ነው። የበለጠ እየጠጡ በሄዱ ቁጥር ግን የእይታ ብዥታ፣ የአስተሳሰብ ፍጥነት መቀዝቀዝ እና መወዛገብ ያጋጥማል፡፡
ሰዎች በብዛት አልኮል በጠጡ ቁጥር ወዲያው ወዲያው ወደ መጸዳጃ ቤት ሲሮጡ ይስተዋላሉ፡፡ የዚህ ምክንያት ጉበት በተቻለ መጠን በደም ውስጥ ያለውን አልኮል ለማስወጣት ሲሞክር ነው፡፡ በመጠጥ ውስጥ የሚገኘው ኤታኖል የተባለው አስካሪ ንጥረነገር፤ ኩላሊት በምን አይነት መንገድ ፈሳሽን መቆጣጠር እንዳለበት የሚነግረውን ቫሶፕሬሲን [Vasopresin] የተባለው ውሕድ ጥቅም ላይ እንዳይውል ያደርገዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ኩላሊት ፈሳሾችን ቶሎ ቶሎ ስለሚያመነጭ የሚጠጣ ሰው ቶሎ ቶሎ ወደ መጸዳጃ ቤት ይሯሯጣል፡፡
እዚህ ጋር አንድ ነጥብ መነሳት አለበት። ሰውነታችን አልኮል ሲገባበት እንደመርዝ አይቶ ለማስወጣት መረባረቡ በራሱ ስለ መጠጥ ጎጂነት ሊያስተምረን አይገባም ነበር? በአንድ ሀገርኛ ብሒል ልሰናበታችሁ፡፡
“ሰካራም ቤት አይሰራም፤ ቢሰራም አያድርበትም፣ ቢያድርበትም አይኖርበትም፣ ቢኖርበትም አያምርበትም”
ምንጭ፦ Wikipedia የመረጃ ቋት፥ Harvard health ጦማር፥ Drink aware ድረገጽ