Ethio Job Vacancy
46.1K subscribers
23.2K photos
63 videos
157 files
19.5K links
አዳዲስ እና ወቅታዊ የሥራ ቅጥር ማስታወቂያዎችን ከተለያዩ ጋዜጦችና ድረ ገጾች ለሥራ ፈላጊዎች መረጃ መስጠት ነው።
Post New Job vacancies to Who are looking jobs.
Group discussion https://t.me/+uGe3tVg5jF4yZjk0
Download Telegram
#ቤተ #ወለድ
የደሀ ገፅሽን በስላቅ ሊገልጡ
ሀገሬ ከብርሽ ባንኮችሽ በለጡ
የባንኮችሽ ቁጥር ከገንዘብሽ ናረ
የአምናው አበዳሪ ዛሬ ተበደረ
* * *
የፎቅ አብቃይ ልጅሽን ግንባር እያወዙ
"ስራቸው" ሳይታይ ቅርንጫፎች በዙ
#ለነገሩ #ተይው
ድከም ሲለኝ እንጂ በከንቱ ‘ምለፋው
ነብይ ሲበዛ ነው በረከት የጠፋው
#ልክ #እንደ #ይሁዳ
የዘመንሽ ነብያት ለየት ሚያደርጋቸው
አምላክሽን ሸጠው መሬት መግዛታቸው
#ቁጥራቸውስ #ብትይ
ለመጎናፀፊያው ዕጣ ሲጣጣሉ
በቅዱሱ መጽሐፍ ካሉት ይበልጣሉ
* * *
#እና #ምን #ልልሽ #ነው
ባለ ባንክ ልጆችሽ
ከሌለው ሰብስበው ላለው ሲያበድሩ
ሰጪና ተቀባይ
ባለ ሁለት ትርጉም ቅኔ ሆነው አደሩ
* * *
ቅኔያዊ ባንኮችሽ ባይላሉም ባይጠብቁም
ተዘርፈው ተዘርፈው ተዘርፈው አያልቁም
* * *
#ለባንኮችሽ #ቅኔ
ለቅኔው ህብረቃል ዜማ ወጣላቸው
" ቆጥቡ ይሸለሙ " ይላል ዘፈናቸው
* * *
ተበዳሪ ወስዶ
ቅንጦቱን ሲገዛ ቅንጦቱን ሲያዋዛ
ለቀለጠው ብሩ
ፍሪጅ ይሸለማል ቆጣቢ እንደዋዛ
* * *
#የዋህ #ቆጣቢዮች
የህብረ ቃሉን ትርጉም ሊፈቱ ቢመኙም
ሰማቸውን እንጂ ወርቁን አላገኙም
====||====
sewa.A