Ethio Job Vacancy
46K subscribers
23.2K photos
63 videos
157 files
19.5K links
አዳዲስ እና ወቅታዊ የሥራ ቅጥር ማስታወቂያዎችን ከተለያዩ ጋዜጦችና ድረ ገጾች ለሥራ ፈላጊዎች መረጃ መስጠት ነው።
Post New Job vacancies to Who are looking jobs.
Group discussion https://t.me/+uGe3tVg5jF4yZjk0
Download Telegram
#የትርጉም #መናፍስት
እንደ ሰው ስጠይቅ በብሔር አታዳምጡኝ
የራስ አስቀምጣችሁ የዘር ጆሮ አትስጡኝ
የዘር መልስ አትስጡኝ

እንደ ሰው ሲያወራ በጎጥ ጆሮ ሰምተን
"#መገዳደፍ" ጀመርን "#መደጋገፍ" ትተን
* * *
#እንግዳ #ሲመጣ
ትልቅ ሀገር ሽጠን መንደር ስለገዛን
"#ማሳቁን" ትተነው "#ማሳቀቅ" አበዛን
ሰውነትን ጥሎ ዘረኝነት ሲያልፈው
"#ተቀባይ" "#ተበቃይ" ሆነውና አረፈው
ዜግነት ሞቶ ብሄር ጀገነ
"#መቀበል" ማለት "#መበቀል" ሆነ
* * *
#አዲስ #ሞያ #ሆኖ
አፍ በጆሮ ማረድ ንግግር መበለት
"#እንቆረጥ" ሆኗል "#እንቆጠር" ማለት
#አትራፊ #ተብሎ
ፍቺ ሊቸረቸር ከሱቅ የወጣ ‘ለት
"#እንዝጋ" ይልሀል "#እንግዛ" ለማለት
* * *
ተርጓሚ ሲበዛ በየጥጋጥጉ
"#መተራረድ" ሆነ "#መረዳዳት" ወጉ

"#የማብላት" ትርጉሙ "#መብላት" የሆነ ‘ለት
"#መገናነዝ" ሆኗል "#መዘጋገን" ማለት

"#ሊቁን" ጠፍንገን "#ቂሉን" ስንፈታ
"#ወንጀል" ገነነ "#በወንጌል" ፋንታ
ትርጉም አለቀ ፍቺ ተዛባ
"#ልጅ" ስንጣራ "#ጅል" ዘሎ ገባ
========||=======