Ethio Job Vacancy
46K subscribers
23.2K photos
63 videos
157 files
19.5K links
አዳዲስ እና ወቅታዊ የሥራ ቅጥር ማስታወቂያዎችን ከተለያዩ ጋዜጦችና ድረ ገጾች ለሥራ ፈላጊዎች መረጃ መስጠት ነው።
Post New Job vacancies to Who are looking jobs.
Group discussion https://t.me/+uGe3tVg5jF4yZjk0
Download Telegram
Mettu University
አዲሱ የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 እና አንዳንድ ጉዳዮች
ከዚህ ቀደም በሀገራችን ኢትዮጵያ የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይን የሚገዙ ሕጎች እንደነበሩ የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ፡፡ ከነዚህም ውስጥ በ1955 ዓ.ም የወጣው የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 210/1955፣ በ1968 ዓ.ም የወጣው የሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 64/1968፣ የሠራተኛ ጉዳይ ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 85/1968፣ ስለአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ የወጣው አዋጅ ቁጥር 42/1985 እና አዋጅ ቁጥር 377/1996 የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
ከየካቲት 18 ቀን 1996 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ በግሉ ዘርፍ ያለውን የአሠሪና ሠራተኛ ግንኙነትና መስተጋብር እንደ ዋነኛ ምሰሶ በመሆን ሲያስተዳድር የነበረው ሕግ አዋጅ ቁጥር 377/1996 እና የዚህ አዋጅ ማሻሻያ ሕጎቹ አዋጅ ቁጥር 466/1997 እና አዋጅ ቁጥር 494/1998 ነበሩ፡፡ እነዚህ ሕጎች ከ14 አመታት በላይ በሥራ ላይ የዋሉ በመሆናቸው አሁን ካለው የማህበረሰብ እድገት ጋር የተጣጣሙ ባለመሆናቸው የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቀን ሰኔ 27 ቀን 2011 ዓ.ም ባደረገው 4ኛ አመት የሥራ ዘመን 48ኛ መደበኛ ስብሰባው የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ረቅቅ አዋጅን መርምሮ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡
ይህም ሕግ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 ዓ.ም ሆኖ ነሐሴ 30 ቀን 2011 ዓ.ም በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ በሥራ ላይ ውሏል፡፡ ይህ አዲሱ የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ምን ምን ሀሳቦችን አካቶ ነው የተሻሻለው? ለሠራተኛው ምን ዓይነት ሕጋዊ ጥቅምና መብቶችን አካቷል? እንዲሁም የአሠሪ ግዴታና መብት ምን ይመስላል? የሚሉትን ጉዳዮች እና አዲሱን አዋጅ ከተሻረው የአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 በማነፃፀር በወፍ በረር (Bird’s Eye View) እንደሚከተለው እንመለከታለን፡፡
አዲሱ የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 ከዚህ ቀደም የነበረውን አዋጅ ከነ ማሻሻያዎቹ በመሻር እና የግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጄንሲ አዋጅ ቁጥር 632/2001ን በአዲሱ አዋጅ ውስጥ በማካተት ነው በሥራ ላይ የዋለው፡፡
ይህ አዲሱ አዋጅ የተለያዩ አዳዲስ ሀሳቦችን አካቶ ብቅ ብሏል፡፡ ከዚህ ቀደም በነበረው በተሻረው ሕግ መሠረት በቅጥር ምልመላ ሂደት (Recruitment Process) ላይ አዋጁ ተፈጻሚ እንዲሆን አልተደረገም ነበር፡፡ በአዲሱ አዋጅ የአዋጁን የተፈጻሚነት ወሰን በአሠሪና ሠራተኛ በቅጥር ላይ በተመሰረተ ግንኙነትና በቅጥር ምልመላ ሂደት ላይ እንዲሆን ተደርጓል፡፡ ይህም ማለት በአዲሱ አዋጅ አንድ ቅጥርን የሚፈጽም አካል (አሠሪ) ምልመላ ሂደቱ ግልጽና ተጠያቂነት ባለው መንገድ እንዲያካሂድና ከማንኛውም ዓይነት አድሎ (Discrimination) በፀዳ መልኩ እንዲያከናውን የሚያስገደድ ነው፡፡ ቅጥሩን የሚፈፅመው አካል ይህንን የቅጥር ሂደት ግልጽ ባልሆነና አድሎን በሚፈጥር መልኩ ምልመላውን ካከናወነና ሠራተኛው ላይ ቅሬታን ከፈጠረ ሠራተኛው (የወደፊት ተቀጣሪው) ቅሬታውን የሥራ ክርክር ጉዳይን አይቶ ለመወሰን ስልጣን ላለው ፍርድ ቤት አቤቱታውን እንዲያቀርብና መፍትሄ እንዲያገኝ የሚፈቅድ ድንጋጌ ነው፡፡ ይህ የአዋጁ የተፈፃሚነት ወሰን ድንጋጌ ለአሠሪው ግዴታን የሚጥል ለሠራተኛው ደግሞ መብትን የሚያጎናፅፍ ነው፡፡ ይህ ድንጋጌ በአግባቡ ከተተገበረ አሁን በአገራችን ኢትዮጵያ ላይ እየታየ ላላው የሠራተኛ ቅጥር ሂደት ቅጥ ያጣ ነፃነትን ወደ ስርአት የሚያስገባ እና ለዜጎች እኩል ሥራ የመወዳደር እና የመቀጠር ዕድል መብትን (The Right of equal opportunity of jobs) የሚያረጋግጥ ይሆናል፡፡

አዋጁ ለአሠሪውም ሆነ ለሠራተኛው እንዳያደርጉ የከለከላቸው ህገ-ወጥ ተግባራትን ዝርዝሯል፡፡ ከነዚህም ውስጥ የተከለከሉ ድርጊት በሚለው በአንቀፅ 14 ስር ለህብረት ድርድር አስፈላጊ የሆነ መረጃ ባለማቅረብ የድርድር ጊዜ እንዲራዘም ማድረግ ወይም ሌሎች ከቅን ልቦና ውጭ የሆኑ ተግባራትን መፈፀም፣ በሥራ ቦታ ወሲባዊ ትንኮሳ ወይም ጥፋት መፈፀም፣ በሥራ ቦታ አካላዊ ጥቃት መፈፀም እና ሠራተኛን በሀይል አስገድዶ ማንኛውንም ሥራ እንዲሰራ ወይም ግዴታን እንዲያሟላ ማድረግ በአሠሪ ወይም በሥራ መሪ ከተፈፀሙ የአሠሪ ህገ-ወጥ ተግባራት ተደርገው ተቆጥረዋል፡፡ በተመሳሳይ አንቀፅ ስር በሀሰተኛ ሰነድ መገልገል ወይም ለመገልገል መሞከር፣ በህብረት ስምምነት ከተፈቀደው ውጭ ወይም አሠሪው ሳይፈቅድ በሥራ ሰዓት ስብሰባ ማካሄድ፣ በሥራ ቦታ ወሲባዊ ትንኮሳ ወይም ጥቃት መፈፀም እና በሥራ ቦታ አካላዊ ጥቃት መፈፀም ለሠራተኛው የተከለከሉ ድርጊቶች ናቸው በሚል እንደ አዲስ የተካተቱ ሀሳቦች ናቸው፡፡

የሥራ ስንብት ክፍያን በተመለከተ የተሻረው አዋጅና ማሻሻያ ድንጋጌዎቹ ላይ የሰፈሩት ምክንያቶች ሲሟሉ ክፍያ የሚፈፀም የነበረ ሲሆን በአዲሱ አዋጅ አንቀፅ 39 (1) (መ) ስር አዲስ ሀሳብ አካቷል፡፡ ይህም ሀሳብ በአሠሪ ወይም በሥራ መሪ ወሲባዊ ጥቃት ወይም ትንኮሳ የተፈፀመበት እንደሆነ ወይም ድርጊቱ በሌላ ሠራተኛ እንደተፈፀመ ሪፖርት ተደርጎለት አሠሪው ተገቢውን እርምጃ ባለመውሰዱ ሠራተኛው የሥራ ውሉን ያቋረጠ እንደሆነ ከአሠሪው የሥራ ስንብት ክፍያ የማግኘት መብት እንዳለው የሚደነግግ ነው፡፡ የሥራ ስንብት ክፍያ ዋነኛው ዓላማ አንድ ሠራተኛ ከሥራ ሲሠናበት ችግር ላይ እንዳይወድቅ ራሱን እንዲያቋቁም ለመርዳት ወይም በሥራ ላይ የቆየ ሠራተኛ አዲስ ሥራ ፍለጋ ላይ እያለ ሊደርስበት የሚችለውን ኢኮኖሚያዊ ችግር በመጠኑም ቢሆን ለመቀነስ ነው፡፡ ይህ የክፍያ ዓይነት በተለምዶ የሥራ ማፈላለጊያ በመባል ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ወሲባዊ ጥቃት ወይም ትንኮሳ የደረሰበት ሠራተኛ በሥራ ላይ የሚደርስበትን አካላዊም ሆነ ሞራላዊ በደል ችሎ የሚሰራበት ጊዜ እንዲያበቃ የሕግ ከለላ በሀገሪቱ እንዳለ ማሳያ ድንጋጌ ነው፡፡
ሌላኛው የዚህ አዋጅ ማሻሻያ የሙከራ ጊዜ ቅጥርን የሚመለከት ጉዳይ ነው፡፡ የሙከራ ጊዜ ቅጥር ማለት አንድ ሰው በሥራ ውሉ መሠረት ሊመደብበት ለታቀደው ቦታ ተስማሚ መሆኑን ለመመዘን በተዋዋዮቹ ወገኖች (በአሠሪው እና በሠራተኛው) ስምምነት በፅሁፍ የሚደረግ የቅጥር ዓይነት ሲሆን ይህ የሙከራ ጊዜ በተሻረው አዋጅ ከአርባ አምስት (45) ተከታታይ ቀናት ለማይበልጥ ጊዜ የሚደረግ የነበረ ቢሆንም በዚህ በአዲሱ አዋጅ ግን የሙከራ ጊዜው ሠራተኛው ሥራ ከጀመረበት ቀን አንስቶ ከ60 (ስልሳ) የሥራ ቀናት (ከሁለት ወራት) ሊበልጥ አይችልም በማለት የሙከራ ጊዜ ቀናቱ ከፍ እንዲል ተደርጓል፡፡ ይህ የህጉ ድንጋጌ ለአሠሪው ሰፋ ያለ መብት የሰጠና አሠሪው ሠራተኛውን ሊመድብበት ላቀደበት የሥራ መደብ ብቁ መሆኑን በቂ ጊዜ በመስጠት እንዲመዝነው የሚረዳው ነው፡፡ በሌላ በኩል ሠራተኛው ቋሚ ከመሆን እና የሥራ ዋስትናን ቶሎ ከማረጋገጥ ጉጉት አንጻር ሲታይ ይህ ድንጋጌ ሠራተኛው ላይ ቅሬታ ያስነሳል የሚል እምነት አለኝ ፡፡ ይህ ቢሆንም ሠራተኛው ለተጠቀሰው ጊዜ ቋሚ አለመሆኑን አውቆ ሥራውን አክብሮ በትጋት እንዲሰራ እና የሥራ ባህሉን (Work Habit) እንዲያዳብር ይረዳል የሚል ሀሳብ አለኝ፡፡
በአጠቃላይ አዲሱ የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 ለሠራተኛው አንዳንድ መብቶችን ያስከበረ፣ ለአሠሪው ደግሞ የሥራ ውልን ለማቋረጥ ሰፊ መብትን ያጎናፀፈ ነው ለማለት ይቻላል፡፡ በአሠሪና ሠራተኛ መካከልም የኢንዱስትሪ ሰላምን ለማስፈን ታስቦ የወጣ አዋጅ ስለመሆኑ ከአዋጁ መግቢያ (Preamble) ላይ በግልፅ መረዳት ይቻላል፡፡ አዋጁን በማስፈፀም ሂደት ላይ ወደፊት ለሚፈጠሩ ችግሮች በሶስትዬሽ መድረክ ማለትም በሠራተኛው፣ በአሠሪውና በመንግስት በኩል በሚደረግ ቅርብ ውይይት ይፈታሉ የሚል እምነት አለኝ፡፡ በተጨማሪም ይህንን ሕግ ለመተርጎም ህገ-መንግስታዊ ስልጣን የተሰጣቸው ፍ/ቤቶችም ህጉ የወጣበትን ዓላማና ሊደርስበት ላሰበው ግብ ህጉን በአግባቡ በመተርጎም ለሠራተኛው ቅሬታ አፋጣኝ መፍትሄ በመስጠት ለእውነትና ለፍትህ ይቆማሉ የሚል ተስፋ አለኝ፡፡ መልካም የሥራ ዘመን ይሁንልን!!!
Written by አብዱሰላም ሳዲቅ ሙክታር
ምንጭ፡ abyssinialaw
አንድ ሠራተኛ የሥራ ውል ስምምነት ከፈፀመና ሥራውን መሥራት ከጀመረ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ የተለያዩ ፈቃዶችን የማግኘት ህገ መንግስታዊ መብት አለው፡፡ ይህም መብቱ በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 ተረጋግጧል፡፡ ከእነዚህ የፍቃድ አይነቶች ውስጥ ለዚህ ፅሁፍ ሲባል ሁለቱን ብቻ እናያለን፡፡ አንደኛው የአመት ፈቃድን የሚመለከት ሲሆን ለመጀመሪው የአንድ አመት አገልግሎት የሚሰጠው የፈቃድ መጠን አሥራ ስድስት (16) የሥራ ቀናት እንዲሆን ተደርጓል፡፡ ይህም በተሻረው የአሠሪ እና ሠራተኛ አዋጅ ላይ ከነበረው ለተመሳሳይ አንድ አመት አገልግሎት ይሰጥ ከነበረው የአሥራ አራት (14) የሥራ ቀናት የዓመት እረፍት የሁለት (2) ተጨማሪ የሥራ ቀናት ዕድገት እንዲያሳይ ተደርጓል፡፡ ከአንድ አመት በላይ ለሆነ አገልግሎት በአሥራ ስድስት ቀናት ላይ ለእያንዳንዱ ተጨማሪ ሁለት የአገልግሎት ዓመት አንድ የሥራ ቀን እንዲሆን ተደርጓል፡፡ በጠቅላላው ሲታይ ለሠራተኛው የሚሰጥ አመት ፈቃድ መጠን አንፃራዊ መሻሻል አሳይቷል ለማለት ይቻላል፡፡

ሁለተኛው የፈቃድ ዓይነት ልዩ ፍቃድ ሆኖ ለቤተሰብ ጉዳይ የሚሰጥ ፈቃድ ሲሆን ከዚህ ቀደም ያልነበረው በዚህ በአዲሱ አዋጅ የተካተተው ባል የሆነ ሠራተኛ (Married Employee) የትዳር ጓደኛ ስትወልድ ለሶስት ተከታታይ ቀናት ከክፍያ ጋር ፈቃድ እንዲያገኝ ሆኗል፡፡ ይህም ድንጋጌ የባል ሰራተኞችን ጥያቄ የመለሰ ነው ለማለት ይቻላል፡፡ ይህ (Paternity Leave) በሌላው አለም በበለፀጉትና በተለይ በስካንዲኒቪያን (Scandinivian) ሀገሮች የተለመደ አሰራር ሲሆን በሀገራችንም ይህ የፈቃድ ዓይነት ማህበራዊ ጠቀሜታው የጎላ ነው፡፡ ነፍሰጡር የሆነች ሠራተኛ ለቅድመ ወሊድ የአንድ ወር እንዲሁም ለድህረ ወሊድ የሶስት ወር በጠቅላላው የአራት ወር የወሊድ ፈቃድ ዕረፍት የማግኘት መብትን አረጋግጦላታል፡፡ በዚህ አግባብ ከተሻረው አዋጅ ጋር ሲነፃፀር የአንድ ወር የወሊድ ፈቃድ ዕረፍት ጭማሪ እንዲኖረው ተደርጓ ተሻሽሏል፡፡ ይህም ድንጋጌ የሴት ሰራተኞችን ጤና ለመጠበቅ ከፍተኛ የሆነ አስተዋፅኦ ይኖረዋል፡፡

በአሠሪና ሠራተኛ የሥራ ውል ግንኙነት ላይ አለመግባባት የሚፈጥረው ዋናው ጉዳይ አሠሪው የሠራተኛውን የሥራ ውል ያለማስጠንቀቂያ የሚያቋርጥበት ጉዳይ ነው፡፡ መደበኛ ፍ/ቤቶችም በአብዛኛው የሥራ ክርክር ጉዳዩችን በሥራ ክርክር ችሎቶች ሲያዩ እንደጭብጥነት የሚይዙት ጉዳይ አሠሪው የሠራተኛውን ውል ያቋረጠው በሕጋዊ መንገድ ነው ወይስ አይደለም የሚል ነው ፡፡ ለዚህ ጭብጥ ደግሞ መፍትሄ ለመስጠት ፍ/ቤቶች የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎችን ይሰማሉ፡፡

አሠሪው የሠራተኛውን የሥራ ውል ያለማስጠንቀቂያ ለማቋረጥ በአዋጅ ቁጥር 377/76 አንቀፅ 27(1) ላይ በተመለከቱት ምክንያቶች እና በህብረት ስምምነት ላይ በተገለፁት የሥራ ውል ለማቋረጥ ያስችላሉ ተብለው የተወሰኑ ጥፋቶችን ሠራተኛው ፈፅሞ ሲገኝ ብቻ ነው፡፡ ከነዚህም ጥፋቶች ውስጥ በአንቀፅ 27 (1) (ሀ) እና (ለ) የተጠቀሱት፡- ሀ) ያለበቂ ምክንያት እና ማስጠንቀቂያ እየተሰጠው (warning) በመደጋገም የሥራ ሰዓት አለመክበር፣ እና ለ) በመደዳው ለአምስት የሥራ ቀናት ወይም በአንድ ወር ውስጥ በጠቅላላው ለ10 የሥራ ቀናት ወይም በአንድ አመት ውስጥ በጠቅላላው ለ30 የሥራ ቀናት ያለ በቂ ምክንያት ከሥራ መቅረት የሚሉት ይገኙበታል፤ እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ጥፋቶች በአዲሱ አሠሪ እና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ እንደሚከተለው ተሻሽለዋል፡፡

አዲሱ የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ አንቀፅ 27 (1) (ሀ) ላይ የተመለከተው አንደኛው ያለማስጠንቀቂያ የሥራ ውል ማቋረጫ መንገድ ሠራተኛው የሥራ ሰዓት ለማክበር የማይችልባቸው ሁኔታዎች ተብለው በህብረት ስምምት፣ በሥራ ደንብ ወይም በሥራ ውሉ ከተዘረዘሩት ምክንያቶች ውጭ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ እየተሰጠው በስድስት ወር ውስጥ በጠቅላላው ለስምንት ጊዜ የሥራ ሰዓት አለማክበር ነው፡፡ ይህ የሕግ ድንጋጌ ከአዋጅ 377/96 አንፃር ሲታይ ሠራተኛው የሥራ ሰዓት ባለማክበሩ የሚሰጠው ማስጠንቀቂያ በፅሁፍ እንዲሆን የተደረገ ሲሆን በመደጋገም የሥራ ሰዓት አለማክበር የሚለው ደግሞ በስድስት ወር ውስጥ በጠቅላላው ለስምንት ጊዜ የሥራ ሰዓት አለማክበር በሚል ግልፅ በሆነ መልኩ የጊዜ ገደብ እንዲበጅለት ተደርጓል፡፡
ይህ ድንጋጌ ለአሠሪው በህብረት ስምምነት፣ በሥራ ደንብ ወይም በሥራ ውሉ ከሚዘረዘሩት ወይም ከተዘረዘሩት የሥራ ሰዓት አለማክበር ምክንያቶች ውጭ ሠራተኛው ወደ ሥራ ገበታው አርፍዶ ቢገባ ወይም ከተቀመጠው የሥራ ሰዓት ቀድሞ ቢወጣ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ እየተሰጠው በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ለስምንት ጊዜ የሥራ ሰዓቱን ካላከበረ አሠሪው የሥራ ውሉን ያለማስጠንቀቂያ እንዲያቋርጥ ይፈቅድለታል፡፡ ድንጋጌው አሠሪዎች አሁን በሀገራችን ያለውን የትራንስፖርት ችግር ከግምት ውስጥ አስገብተው በሀላፊነት መንፈስ ሠራተኛውን ካላስተዳደሩና ካልመሩ በሠራተኛው በኩል እንደ የሥራ ሰዓት አለማክበሪያ ምክንያት ተደጋግሞ ሊጠቀስ የሚችል የትራንስፖርት ችግር በመሆኑ የጊዜ ገደብ መቀመጡ በሠራተኛው ላይ የሥራ ዋስትና (Job Security) አደጋ ውስጥ የሚጥል ነው፡፡
በአንቀፅ 27 (1) (ለ) ስር የተደነገገው ሌላኛው ያለማስጠንቀቂያ የሥራ ውልን ማቋረጫ ምክንያት በዚህ አዋጅ ከተመለከቱት እረፍቶች እና ልዩ ልዩ ፈቃዶች ውጭ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ እየተሰጠው በስድስት ወር ውስጥ ለአምስት ቀናት ከሥራ መቅረት ነው፡፡ ይህ አንቀፅ ከበፊቱ አዋጅ አንፃር ሲቃኝ አሠሪው በቀላሉ የሠራተኛን የሥራ ውል እንዲያቋርጥ የሚያስችል ነው፡፡ መሰረታዊው ጥያቄ “ከሥራ መቅረት” ማለት ምን ማለት ነው የሚለው ጥያቄ ሲሆን ይህም ማለት አንድ ሠራተኛ ሊሰራ በተስማማውና በአሠሪው በተመደበበት የሥራ ቦታ ላይ በተቀመጠው መደበኛ የሥራ ሰዓት እና ጊዜ አለመገኘት ማለት ነው፡፡ ነገር ግን አንዳንድ አሠሪዎች (ድርጅቶች) የሥራ ሰዓቱን ያላከበረ ( ያረፈደ ወይም ቀድሞ የወጣን) ሠራተኛን ከሥራ እንደቀረ (Absent) እንደሆነ አድርገው የሚቆጥሩና የሚተገብሩ በመሆናቸው አንድ ሠራተኛ ከሥራ ለቀረባቸው ጊዜያት ደሞዙን ከመቁረጥ አልያም ሌላ ቀላል አስተዳደራዊ እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ የመጨረሻውንና ከባድ የሚባለውን አስተዳደራዊ እርምጃ ማለትም የሥራ ውልን እንዲያቋርጡ የሚያደርግ ነው፡፡ ይህ ደግሞ የሠራተኛውን የሥራ ዋስትና (Job Security) አደጋ ላይ የሚጥልና በአሠሪና ሠራተኛ መካከል የኢንዱስትሪ ሰላምን ለማምጣት አዳጋች የሚያደርግና በዚህ ድንጋጌ ምክንያት ሊፈጠር በሚችለው አለመግባባት ፍ/ቤቶች ላይ ከፍተኛ የሆነ የሥራ ጫና ይፈጥራል የሚል እምነት አለኝ፡፡ በሌላ በኩል ሥራው ላይ የሚያለምጥ፣ የሚለግም ወይም የሚያሾፍ በጠቅላላው ሥራውን የማያከብር ሠራተኛን አሠሪው የመሸከም ግዴታ እንደሌለበት የሚያሳይ ድንጋጌ ነው፡፡
It's for your information
New Job Vacancy
ጥቅምት 03/2012 (14 October 2019)
Advert on Addis Zemen magazine
TBO Printing and Publishing S.C
10 - ቦታዎች በ0አመት 3 - ቦታዎች ልምድ ላላቸው
ጥቅምት 02/2012 (13 October 2019)
Advert on Addis Zemen magazine
Alefa Transprt Plc
91 - ቦታዎች ልምድ ላላቸው
ጥቅምት 02/2012 (13 October 2019)
Advert on Addis Zemen magazine
Sheraton Addis Hotel
2 - ቦታዎች ልምድ ላላቸው
Good Night All Ethiopians
Good morning Ethiopia

ማስታወቂያ
ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ
ለ 2ዐ12 የ Weekend MPH ተመዝጋቢዎች፡፡

በኅብረተሰብ ጤና ትምሕርት ክፍል በቅዳሜ እና እሑድ ትምህርት ኘሮግራም ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማሠልጠን በወጣው ማስታወቂያ ያመለከታችሁ ተወዳዳሪዎች የመግቢያ የጽሑፍ ፈተናው ቅዳሜ ጥቅምት 15/ 2ዐ12 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 በመድኃኒያለም አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ይሰጣል፡፡ ስለዚህ በሰዓቱ ተገኝታችሁ ፈተናውን እንድትወስዱ እያሳወቅን ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ ይዛችሁ እንድትመጡ በጥብቅ እናሳውቃለን፡፡

SPHMMC
አስደሳች ዜና ለከፍተኛ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

የመቱ ዩኒቨርሲቲ ተከታታይና ርቀት ትምህርት እንኳን ለ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሠላም አደረሳችሁ እያለ በማታውና በዕረፍት ቀን የትምህርት መረሃ-ግብር በመጀመሪያ ዲግሪ በተለያዩ የሥልጠና ዘርፎች አመልካቾችን ተቀብሎ ማሠልጠን ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የመማር ፍላጎት ያላችሁና የትምህርት ሚኒስቴርን የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ መሥፈርት ማሟላት የምትችሉ አመልካቾች ከጥቅምት 05-15/2012 ዓ.ም ድረስ በመቱ ዩኒቨርሲቲ ተከታታይና ርቀት ትምህርት ዳይሬክቶሬት እና በበደሌ ማዕከል በለምለም ካርል 1ኛ ደረጃ ት/ት ቤት ዘወትር በሥራ ሰዓት ቅዳሜን ጨምሮ በግንባር በመቅረብ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ሥልጠናው የሚሰጥባቸው የት/ት ዘርፎች

 BSc in Civil Engineering
 BSc in Electrical Engineering
 BSc in Mechanical Engineering
 BSc in Const. Technology & Management
 BSc in Chemical Engineering
 BSc in Computer Science
 BSc in Information Technology
 BSc in Mathematics
 BSc in Statistics
 BSc in Biology
 BSc in Chemistry
 BSc in Physics
 BSc in Sport Science
 BA in Civics and Ethical Studies
 BA in English Language and Literature
 BA in Afan Oromo and Literature
 BA in Oromo Folklore
 BA in Geography and Env’t Studies
 BA in Sociology
 BA in Law
 BA in Management
 BA in Management Information System
 BA in Accounting
 BA in Economics
 BA in Marketing
 BA in Adult Education & Community Development
 BA in Educational Technology
 BA in Special need Education
 BA in Psychology
 BA in Early Child Care
 BSc in Agro-Economics
 BSc in Forestry
 BSc in Plant Science
 BSc in Animal Science
 BSc in Agribusiness & Value Chain Mgt
 BSc in Ecotourism & Biodiversity Conservation
 BSC in Horticulture

የማመልከቻ መሥፈርቶች
 12ኛ ክፍል ያጠናቀቁ እና ት/ት ሚኒስቴር ለከፍተኛ ት/ት ተቋም መግቢያ በየዓመቱ የሚያወጣውን ዝቅተኛ የመቁረጫ ነጥብ ማሟላት የሚችሉ፡፡
 ህጋዊ እውቅና ካለው የት/ት ተቋም 12+2 ወይም 10+3 ተመርቀው ዲፕሎማ ያላቸው፡፡
 ለቴክኒክና ሙያ ተቋማት ሠልጣኞች በሰለጠኑበት የሙያ መስክ የደረጃ 4 ሰርተፍኬት (COC) ያላቸው
ማሳሰቢያ
• በምዝገባ ወቅት ሁሉም አመልካቾች አንድ ክላሴር፣ ፋስትነር፣ ዋናውን የትምህርት ማስረጃ ከማይመለስ ሁለት ኮፒ እና ሁለት ጉርድ ፎቶ ጋር ይዘው መቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
• የማታ ትምህርትን በተመለከተ የግብርና ት/ት መስኮች በበደሌ ግብርና ኮሌጅ ሌሎች የት/ት መስኮች የሚሰጡት በመቱ ማዕከል ይሆናል፡፡
ቀን፡ 04/02/2012 ዓ.ም

ክፍት የኃላፊነት ቦታ ማስታወቂያ
-------------------------------
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር ‘’በመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአመራሮችና አስተዳዳሪዎችን ምርጫ፣ ሹመት/ምደባ ለመደንገግ ባወጣው መመሪያ 002/2009 መሰረት ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ‘’የመካከለኛ አመራር ምርጫ፣ ሹመት/ምደባ መመሪያ ቁጥር 002/2010’’ በዩኒቨርሰቲው ሴኔት አጸድቆ ተግባራዊ እያደረገ ነው፡፡ በዚህም መሰረት ከዚህ ቀጥሎ በተዘረዘሩት አካዳሚክ ክፍሎች በሃላፊነት ላይ የቆዩት ምክትል ዲኖች የሀላፊነት ጊዜያቸውን ስላጠናቀቁ በምትካቸው በመመሪያው በወጣው መስፈርት መሰረት ብቁ አመልካቾችን አወዳድሮ መሾም ይፈልጋል፡፡

ክፍት የኃላፊነት ቦታ፡ አካዳሚክ ዲን - ለግብርናና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ

የማወዳደሪያ መስፈርት
1ኛ. የትምህርት ደረጃ፡ ሌክቸረርና ከዚያ በላይ ያለው/ያላት

2ኛ. በከፍተኛ ትምህርት ተቋም፣ በኢንዱስትሪ፣ በምርምር ተቋማት ወይም መሰል ተልዕኮ ባላቸው ተቋማት በልዩ ልዩ ኃላፊነት ዕርከን ያገለገለ/ችና ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረከተ/ች፤

3ኛ. በሚያመለክቱበት አካዳሚክ ክፍልና ዘርፍ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ የከፍተኛ ትምህርት ተደራሽነት፣ ፍትኃዊነት፣ ጥራት፣ ተገቢነትና ዓለምአቀፋዊነትን ለማሳካት፣ አካዳሚክ ክፍሉን የልህቀት ማዕከል ለማድረግ፣ ተጨማሪ ሀብት ለማስገኘት፣ እንዲሁም ዓለማቀፋዊና አገራዊ ጉድኝቶችን ለመፍጠርና ለማስፋት በሚደረገው ሂደት አስተዋጽኦ ለማበርከት የሚያስችል ስትራቴጂያዊ ዕቅድ ማዘጋጀትና ማብራሪ መስጠት የሚችል/ምትችል፤

4ኛ. የአካዳሚክ ክፍሉ ማህበረሰብ፣ የአካዳሚክ ኮሚሽኑ አባላት እንዲሁም የሚመለከታቸው ተጋብዘው በሚገኙበት መድረክ በአጀንዳዎች ላይ በአካል ተገኝቶ/ታ ማብራሪያና ገለጻ መስጠት የሚችል/ምትችል፤

አመልካቾች፡- ይህ ማስታወቂያ በዩኒቨርሰቲው ድህረ-ገጽ፣ ፌስቡክና ማስታወቂያ ሰሌዳዎች ከተገለጸበት ጥቅምት 4/2011 ዓ/ም ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የትምህርትና የስራ ልምዳቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ያዘጋጁትን ከአምስት ገጽ ያልበለጠ ስትራቴጂያዊ ዕቅድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ባሕር ዳር ዩኒቨርሰቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ወይም አዲስ አበባ በሚገኘው የዩኒቨርሰቲው ግንኙነት ጽ/ቤት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

ለበለጠ መረጃ፡ በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች 0923 297333 ወይም 0918353494 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል፡፡
ኢንፎርሜሽንና ስትራቴጂክ ኮሚኒኬሽን ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ
"ተስፋ ካለህ ፈረሱ ክንፍ ያበቅላል"

በድሮ ጊዜ አንድ የፐርሺያ ንጉስ ፤ በሶስት ሰዎች ላይ የሞት ፍርድ ፈርዶባቸው የስቅላት ስነስርአቱ ከመፈፀሙ በፊት ለመጨረሻ ጊዜ የሚሉት ነገር ካለ እንዲናገሩ ለእያንዳንዳቸው እድል ሰጣቸው ። የመጀመሪያዎቹ ሁለቱ ሰዎች ተስፋ በቆረጠ ስሜት ውስጥ ሆነው እያለቀሱ ቤተሰቦቻቸውን ተሰናበቱ ። የሶስተኛው ሰውዬ ተራ ሲደርስ ግን ሰውዬው ንጉሱን አንድ ጥያቄ መጠየቅ እንደሚፈልግ ተናገረ ። ንጉሱም "በል ተናገር" ብለው ፈቀዱለት ። ሰውዬው ንጉሱን "የስምንት ወር እድል ከሰጡኝ የሚወዱትን ፈረሶን አሰልጥኜ ክንፍ አብቅሎ እንዲበር ማድረግ እችላለው!" ሲል ለንጉሱ ተናገሩ ። ንጉሱም ደስ እያላቸው" ስምንት ወር ይበዛል ባይሆን ሁለት ወር ልሰጥህ እችላለው "። ነገር ግን ፈረሴ በሁለት ወር ውስጥ ክንፍ አብቅሎ መብረር ካልቻለ ተሰቃይተህ እንድትገደል አደርግሃለው! "አሉት ። ሰውየው በዚህ ተስማማ ።
ይህን የሰሙት አብረው ስቅላት የተፈረደባቸው ሰዎች " አንተ ሰውዬ መቼስ ፈረስ ክንፍ አውጥቶ እንደማይበር ታውቃለህ ። ታዲያ ይሄን እያወክ ተሰቃይተህ ለመሞት እንዴት ትስማማለህ...ቆይ ምን አስበህ ነው ?" ብለው ጮሁበት ።
ሰውየውም እንዲ ሲል መለሰላቸው "አስቡት እስኪ...በዚህ ሁለት ወር ውስጥ አራት አማራጮች አሉኝ፦
አንደኛ ማንም ሳይገለኝ በተፈጥሮ ሞት ልሞት እችላለው ። ሁለተኛ ፈረሱ እራሱ ሊሞት ይችላል ። ሶስተኛ ንጉሱም ሊሞት ይችላል ። አራተኛው ደግሞ ማን ያውቃል ፈረሱ እራሱ ክንፍ አውጥቶ መብረር ቢችልስ ? አላቸው ።
ብዙ ጊዜ አንድ ችግር ሲደርስብን ልባችን ይሰበራል ፤ ሌላ አማራጭና መንገድ ያለ አይመስለንም ፤ የኔ ነገር አበቃለት ፣ እድሌ ነው ምንም ማድረግ አልችልም ፣ ከዚ በኋላ ተስፋ የለኝም እያልን በችግሩ መቆዘም ይቀናናል ፤ እንዴት ይህን ችግር አልፋለው የተሻለውን የመፍትሄ ሀሳብ ለማምጣት ምን ማድረግ አለብኝ ከማለት ይልቅ ተስፋ ወደ መቁረጥ እንሄዳለን ። ይህ ደሞ ብዙ ጊዜ ዋጋ ያስከፍለናል ። ከዚህ ታሪክ ብዙ እንማራለን ።
ተስፋ ባለመቁረጡ አንገቱ ላይ የጠለቀችውን ገመድ በጥሶ ህይወቱን ለማርዘም በቅቷል ። አበቃለት በተባለበት ሰዓት እሱ ግን በተሰጠችው ሽርፍራፊ ደቂቃ ተስፋ ሳይቆርጥ የመፍትሄ ሀሳብ ማመንጨት በመቻሉ ይህወቱን ለማትረፍ ችሏል ። አስቸጋሪ በተባለ ሁኔታ ውስጥ ብንሆን እንኳ እይታችን የተስተካከለና ወደ ኋላ ከሚጎትተን አሉታዊ ሀሳቦች ከራቅን አማራጭ መንገድ ሁሌም በየትም ቦታ አለ። የጥዋት ፀሐይን ለመሞቅ ድቅድቁን ጨለማ ማለፍ ግድ እንደሆነ ሁሉ ፤ አብቅቶለታል የተባለው ነገር ለአዲስ የህይወት ጅማሮ መማሪያና መንደርደሪያ ሊሆን እንደሚችል ማመን ትርፋማ ያደርጋል ።
"አልማዝ ሳይሞረድ እንደማያንፀባርቅ ሁሉ ስብዕናም ያለመከራ ቦግ አይልም"
ሰላም፣ ፍቅር፣ ተስፋ ለሁላችን።