Ethio Job Vacancy
46.2K subscribers
23.2K photos
63 videos
157 files
19.6K links
አዳዲስ እና ወቅታዊ የሥራ ቅጥር ማስታወቂያዎችን ከተለያዩ ጋዜጦችና ድረ ገጾች ለሥራ ፈላጊዎች መረጃ መስጠት ነው።
Post New Job vacancies to Who are looking jobs.
Group discussion https://t.me/+uGe3tVg5jF4yZjk0
Download Telegram
«ደምቢ ዶሎ እያለሁ የትምህርት ቤት ጓደኞቼ አማራ፣ ትግሬ፣ ኦሮሞ፣ ኤርትራዊና ሌሎችም ነበሩ፡፡ቤተሰቦቼ መጀመሪያ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ነበሩ፡፡ የአባቴ የክርስትና ስም ወልደ ገብርኤል፣ የእናቴ ደግሞ ወለተ ገብርኤል ነበር፡፡ የእህቴና የእናቴ ክርስትና እናት እታፈራሁ የሚባሉ ጎንደሬ ናቸው፡፡» ብለዋል።
ዶክተር ነጋሶ ስምንተኛ ክፍል ፈተና እስከሚፈተኑ ድረስ አባታቸው በሄዱበት እየተዘዋወሩ ነው ትምህርታቸውን የተከታተሉት፡፡ ከዘጠነኛ እስከ አሥራ አንደኛ ክፍል እየሰሩ እንደተማሩም ይናገራሉ። ከዚያም አሥራ ሁለተኛ ክፍል የመግቢያ ፈተና በመፈተን በዕደ ማርያም ትምህርት ቤት መግባት ቻሉ፡፡
«የአባቴ ልጅ ነኝ፤ በእርሳቸው ነው የወጣሁት» የሚሉት ዶክተር ነጋሶ፤ ስለያዙት ስብዕና፣ ባህሪና ጥንካሬ ሲያብራሩ ከአባታቸው ከቄስ ጊዳዳ ሶለን እንዳገኙት ይገልጻሉ፡፡ ገና በአምስት ዓመታቸው ዓይነስውር በመሆን የህይወትን ከባድ ፈተና የተቀበሉት ቄስ ጊዳዳ ከልመና ወጥተው የታወቁ ቄስ ሰባኪ ለመሆን በቅተዋል፡፡ በቄስ ጊዳዳ ስብዕናና ብርታት የተደመሙ የውጭ አገር ዜጎች ታሪካቸውን ፅፈው አሳትመውላቸዋል፡፡ የዶክተር ነጋሶ አባት ቄስ ጊዳዳ ሶለን የታወቁ የፕሮቴስታንት ቄስ ነበሩ፡፡ የቤቴል ቤተክርስቲን መስራቾች ውስጥ ግንባር ቀደሙ ናቸው፡፡
የፖለቲካ ሀ ሁ …
ዶክተር ነገሶ በዕደ ማርያም ትምህርት ቤት የመግባት ዕድል ማግኘታቸው ከዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጋር የመገናኘትና የመወያየት ዕድል ፈጠረላቸው፡፡ ስለዓለም ታላላቅ አብዮቶች የተማሩትም በዚህ ትምህርት ቤት ነው፡፡ በዩኒቨርሲቲው የተለያዩ የስነ ግጥምና ሌሎች ፕሮግራሞች ላይ ይገኙ ነበር፡፡ እነዚህ ሁሉ ወጣቱ ነጋሶን ከፖለቲካ ጋር በማስተዋወቅ የላቀ ሚና ተጫውተዋል፡፡
ከፖለቲካ ሕይወት ጅማሮ ጋር በተያያዘ እዚያው በዕደማርያም ትምህርት ቤት ውስጥ አስተዳደር እና ሌላ ኃላፊነት ውስጥ የሚሰሩ ዶክተር ጥላሁን ገሞታ ፤ ጉታ ሰርኔሳ እና ሌሎች ተማሪዎች እንደነበሩ ዶክተረ ነጋሶ ስለህይወት መንገዳቸው በተጻፈው መጽሐፍ አንስተዋል፡፡
«የተማሪዎችን አልጋና ምግብ ቤት ንፅህናውን ይቆጣጠራሉ። አንድ ቀን ጉታ ሰርኔሳ ወደ ቢሮው ይጠራኛል፡፡ ጉድፍ የሚፈልግ ይመስል ፊቴ ላይ ዐይኑን ተከትሎ ‘ነገ እሁድ ነው!’ አለኝ፡፡ ‘አዎን’ አልኩት ‘ነገ አንድ ትልቅ ስብሰባ በጉለሌ ይካሄዳል፤ በዛ ስብሰባ ተማሪዎች እንዲገኙ ጋብዘናል፡፡ ሁሉም ኦሮሞዎች ናቸው፡፡ አንተስ ብትገኝ?’ አለኝ:: ሌላ ጥያቄ ሳላስከትል ‘ምናልባት እሄድ ይሆናል’ አልኩት። ከጉታ ጋር ፒያሳ ተገናኘንና አብረን ሄድን፡፡
ቦታው ጉለሌ ሙስሊም መቃብር ፊት ለፊት ነበር፡፡ የስብሰባው ቦታ ስንደርስ ግቢው በትርና እርጥብ ሳር የያዙ ሽማግሌዎች፣ ተማሪዎች፣ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ ወታደሮች… ሁሉ ነበሩ:: መግቢያው ጋር ባለች ጠረጴዛ ላይ ሰዎች ስም ይመዘግባሉ፡፡ ድንኳኑ ውስጥ በኃይል የሚያስተጋባ ድምፅ ይሰማኛል፡፡ ተናጋሪው ማና እንደሆነ አይታየኝም፡፡ ለካ ያ ስብሰባ የተዘጋጀው በሜጫና ቱለማ ማህበር ኖሯል፡፡ ተናጋሪው ጄኔራል ታደሰ ብሩ ናቸው፡፡ አንድ ብር ከፍዬ መታወቂያ ተሰጠኝና አባል ሆኜ ተመለስኩ፡፡»
የፖለቲካ ሀ ሁ ሌላኛው ትውውቅ ነው፡፡ ታዲያ በዕደማርያም ትምህርት ቤት ያላቸውን ቆይታ አጠናቀው የመግቢያ ፈተና በመውሰድ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ትምህርታቸውን በ1963 ዓ.ም አጠናቀቁ፡፡
የተማሪዎች ንቅናቄ
በ1960ዎቹ ዓ.ም ኢትዮጵያን ጨምሮ በአጠቃላይ በዓለም ላይ የተማሪዎች ንቅናቄ ተነስቶ ነበር፡፡የተማሪዎች እና የወጣቶች የለውጥ ፍላጎት የወጣበት ጊዜ ነው፡፡ የዓለም ሕዝቦች፤ የፊውዳል ስርዓት የሚጨቁኑበትና የሚበዘብዙበት ስርአት እንደሆነ በመገንዘብ «ለውጥ መምጣት አለበት፤ በጥቂት ገዥ መደቦች መጨቆንና መበዝበዝ አይገባም፤ ፍትህ ሊኖር ይገባል» የሚል ጥያቄ አንስተው ነበር፡፡ በዓለም አቀፍ ሲታይ ኢምፔሪያሊዝም የሰፈነበት ወቅት ነበር፡፡
በኢትዮጵያ ስለነበረው የተማሪዎች ንቅናቄ ዶክተር ነጋሶ በመጽሐፋቸው ሲያስታውሱ «ንቅናቄውን የሚመራው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ማህበር ምክር ቤት ነበር፡፡ ምክር ቤቱ ለመግባት ከፍተኛ ውድድር ይካሄዳል፡፡ ብቃትና ንቃት ያለው ሰው ነበር የሚመረጠው፡፡ አንዴ ጥላሁን ግዛው ተወዳድሮ ነበር፡፡አርአያ የሆነ ድንቅ ልጅ ነበር:: እርሱን የሚፎካከረው ደግሞ መኮንን ቢሻው የተባለ ልጅ ነበር፤ አሁን ዶክተር ነው:: እና ጥላሁን እንዲመረጥ ስለምንፈልግ ሳያሸንፍ ሲቀር አለቀስን፡፡ይህ ከተከናወነ ሁለት ዓመት በኋላ ጥላሁን በታኅሳስ ወር ተገደለ፡፡ እንቅስቃሴው የሚመራው በምክር ቤቱ ነበር፡፡ ትግሉን የሚመራ የፖለቲካ ፓርቲ አልነበረም፡፡ ተወካዮቹ አብዮተኛ መሆን ይጠበቅባቸዋል::»
ታዲያ ዶክተር ነጋሶም ካሉበት ፋካሊቲ ከአንድ ጓደኛቸው ጋር በመሆን የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ህብረት ማህበር ምክር ቤት አባል ሆኑ፡፡ በወቅቱ የተማሪዎች ንቅናቄ ዓላማ የነበረው ኢትዮጵያን ዴሞክራሲያዊት ሀገር ማድረግ፤ ፈጣን አብዮት ተካሂዶ ለውጡ እንዲመጣ ለጭቁኑ ህብረተሰብ መታገል ነበር::
በወቅቱ ጭቁን የሚባሉት የህብረተሰብ ክፍሎች ማለትም ላብአደሮች፣ አርሶአደሮች፣ ሴቶች፣ ጭቁን ብሔረሰቦች፣ ጭቁን ሃይማኖቶች… ሲሆኑ ዶክተር ነጋሶ እና ጓደኞቻቸው ይህንን ጭቆናን ለማስወገድና የነበሩባቸው ችግሮች እንዲፈቱላቸው ከፈለጉ ተደራጅተው መታገል አለባቸው፤ ሲሉ ነበር።
የቤተሰብ ህይወት
ዶክተር ነጋሶ ጥቅምት 1967 ዓ.ም ወደ ጀርመን ሲጓዙ ቤተሰባቸውን ይዘው ለመሄድ አስበው ነበር፡፡ሆኖም ለመውለድ አንድ ወር የቀራቸውን ባለቤታቸውን በአውሮፕላን ማሳፈር ስለማይቻል ከወለዱ በኋላ ከነልጆቻቸው ይዘው ወደ ጀርመን የሚመጡበትን ሁኔታ አመቻችተው ወደ ጀርመን አቀኑ። ባለቤታቸውም ጃለሌን እንደወለዱ በወሩ ሁለቱን ልጆቻቸውን ኢብሳንና ጀለሌን ይዘው ወደ ጀርመን ሄዱ፡ ፡ ኑሯቸውን የጀመሩት ቦሁሞ በምትባል ግዛት ነበር፤ በኋላም በ1968 ዓ.ም ወደ ፍራንክፈርት መጡ፡፡
ዶክተሩ ስለመጀመሪያ ትዳራቸው ሲናገሩ «… ከባለቤቴ ጋር መስማማት አልቻልንም:: ሁልጊዜ በትንሽ በትልቁ ሥራችን ፀብ ሆነ:: አንዴ ተጣልተን ለየብቻ መኖር ጀምረን ነበር:: በሌላኛው ጊዜም እንዲሁ እኔ ከቤት ወጥቼ የኦነግ መሪዎች ዶክተር ታደሰ ኤባና አቶ ታደሰ ዋቅጂራ አስታረቁን፡፡ ብቻ መስማማት እና በሰላም መኖር አልቻልንም፤ ጀርመን አገር ደግሞ የሴቶች መብት በጣም የሚከበርበት አገር ነው፡፡ የጀርመን ፍርድ ቤት ዳኞች ጉዳያችንን በተገቢ መንገድ ከተመለከቱት በኋላ የፍች ወረቀታችንን ሰጡን፡፡» ሲሉ ያስታውሳሉ።
ከዚያም እዚያው ጀርመን «ሦስተኛ ዓለም ቤት» የተሰኘ ድርጅት ውስጥ እየሰሩ ሳለ የአሁኗ ባለቤታቸው በሩዋናዳ በአንድ ግብረ ሰናይ ድርጅት በአዋላጅ ነርስነት ሲሰሩ ቆይተው ለትምህርት ወደ ፈራክፈርት ተመለሱ፡፡ ታዲያ ለአፍሪካ ፍቅር ያላቸው እኚህ ሴት ምንም እንኳ ጀርመን የትውልድ አገራቸው ብትሆንም ከአፍሪካውያን ጋር መስራት ውሎ ማደር ሆነ ኑሯቸው፡፡ እናም ይህ ፍቅር እና ውሎ ከዶክተር ነጋሶ ጋር እንዲገናኙ አደረጋቸው፤ተላመዱም። ከ1978 ዓ.ም ጀምሮም አብረው መኖር ጀመሩ፡፡ ተሊሌ የተባለች አንዲት ሴት ልጅም ወልደዋል፡፡
የተማሪዎች አመፅ በጀርመን
ጀርመን እንደነማርክስ ያሉ ዓለማችንን የዘወሩ ፖለቲከኞችን ያፈራች ምድር ናት፡ ፡ የሦስተኛው የዓለም አገራት አብዮተኞች መሰብሰቢያ ማዕከልም ነበረች፡፡ የ60ዎቹ ትውልድ ትንታግ ወጣቶች ሰልፈኛ የነበሩት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ፤የፖለቲካ ትኩሳት በሚንቀለቀልባት የአመፅ ትግል በሚጠነሰስባት አያሌ ርዕዮተ ዓለም ሃሳቦች በሚፋጩባት ጀርመን ሲከትሙ የአገር ቤቱ የተማሪዎች አብዮት በደርግ እየተዳፈነ ሄደ፡፡ ነጋሶ የለኮሱትን አብዮት ጥለው ባህር ማዶ የተሸገሩት ከትግሉ ሜዳ ለመሸሽ የሚመስላቸው አይጠፉም፡፡ነገር ግን ጀርመንም ቢሆን አብዮቱን እያጧጧፉት ነበር፡፡
ለነገሩ አያሌ የዘመኑ ወጣት አብዮተኞች የአገር ቤት ትግል አላዋጣ ሲላቸው በአየርም በምድርም እያሉ አሜሪካ እና አውሮፓ ሲሰደዱ ትግላቸውንም የመቀጠል ትልማቸውን በልባቸው በመሰነቅ ነበር፡፡ ዶክተር ነጋሶም በአንድ ወቅት እንዳሉት የኢትዮጵያን ምድር ለቅቄ ወደ ጀርመን ስበር በአንጎሌ ሻንጣ ውስጥ ብዙ ሃሳቦችን ጠቅጥቄ ነበር ብለዋል፡፡
ኢህአፓ ይበትናቸው የነበሩ ወረቀቶች፣ የአብዮት እንቅስቃሴ በመቋቋም ላይ የነበሩት መኢሶንና ኦነግ በሃሳብ አብረዋቸው ባህር ማዶ ተሻግረዋል፡፡ የተማሪዎች አብዮትን መነሻ በማድረግ የመንግሥት ስልጣንን የተረከበው የደርግ አስተዳደር አፍታም ሳይቆይ ወደ አምባገነንነት መለወጡ ዶክተር ነጋሶን ብቻ ሳይሆን የአገር ቤት ታጋዮችን ሳይቀር ተስፋ ማስቆረጡ አልቀረም፡፡ ይህንን ክፉ ዜና ደግሞ ከአገር ርቆ መስማት ስቃዩን እጥፍ ድርብ ያደርገዋል፡፡
በጀርመን የነበሩ የፖለቲካ ማህበራትን የዶክተር ነጋሶን ያህል አበጥሮ የሚያውቅ እምብዛም አይገኝም፡፡በጀርመን ለቁጥር የሚያዳግቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተመስርተዋል፤ ፈርሰዋልም፡፡ የፖለቲካ ድርጅቶችም ፍጭት ከባድ ነበር፡፡ ታዲያ ዶክተር ነጋሶም አንጀታቸውን የሚያርስ የፖለቲካ ፓርቲ አጡ:: ያልገቡበት ፖለቲካ ድርጅት ፣ሊያስማሙ ያልሞከሩት ማህበር የለም፡፡ በዚህ ላይ የውጭ አገር ኑሮ ሰልችቷቸዋል፡፡ አገር ቤት ወደነበረው ተጨባጭ ትግል ለመግባት ቋምጠዋል፡፡
የአገራቸውን ምድር ለመርገጥ ድልድይ የሆናቸው ታዲያ ኢህአዴግ ነበር፡፡ ዶክተር ነጋሶ አዲስ የፖለቲካ ምዕራፍ በመሻገር ከኢህአዴግ ጋር ተቀላቅለው ለአገራቸው የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ለማበርከት ተጣድፈዋል፡፡ ከዚያ በፊት ግን ጥቂት ፈተናዎችና መሰናክሎች ይጠብቃቸዋል፡፡ በአውሮፓ ሲወራ የሰሙትን «ኦህዴድ የህውሃት አሽከር ነው» የሚል አሉባልታውን ራሳቸው ፈትሸው ማረጋገጥ ነበረባቸው፡፡ የኦነግና ኦህዴድ ፍጥጫም የፖለቲካ መንገዳቸውን ቀና አያደርግላቸውም:: ወደ ፊትም የሚጠብቃቸውን የፖለቲካ ሕይወት እሾህ የበዛበት ቢሆንም ወደ ፈተናው የገቡት ግን በደስታ ነበር፡፡
በኩረ ስልጣን
በ1983 ዓ.ም የመጀመሪያ የመንግሥት ሥራቸውን በሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴርነት የጀመሩት ዶክተር ነጋሶ ለአንድ ዓመት በሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴርነት ካገለገሉ በኋላ ወደ ማስታወቂያ ሚኒስትር ተዘዋወሩ፡፡ እዚያም ቢሆን ከችግር እና ውጣ ውረድ አልዳኑም፡፡
ዶክተር ነጋሶ ነገሩን ሲያስታውሱ «በሚኒስትር መሥሪያ ቤቱ ያሉ አብዛኛው ኃላፊዎችና ሠራተኞች ታጋይ በመሆኔ ፈተናውን አክብዶውብኝ ነበር» ይላሉ፡፡ ዶክተር ነጋሶ ከሠሯቸው ሥራዎች አንዱ ህገ መንግሥት ማርቀቅ ነው፡፡ በሽግግሩ ዘመን ሕገመንግሥት ሲረቅ በአርቃቂው ኮሚሽን ውስጥ ከተካተቱ ሰዎች መካከል ዶክተር ነጋሶ አንዱ ነበሩ፡ ፡ ሕገ መንግሥት ሲረቀቅ የኃይለ ሥላሴንና የደርግን እንዲሁም የዳበረ ዴሞክራሲ ባህል አላቸው የሚባሉ አገራት ሕገ መንግሥቶች እንደተመለከቱት የሚናገሩት ዶክተር ነጋሶ፤ በሕገ መንግሥት ዙሪያ ዕውቀት ያላቸው የውጭ ባለሙያዎች ጽሑፍ ማቅረባቸውን ያስታውሳሉ፡ ፡ በፓርላማም ውይይት ክርክርም ተደርጓል፡፡
ሕይወት በቤተ መንግሥት
ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሆነው እንደተሾሙ ጨርቄን ማቄን ሳይሉ በአጀብ ወደ ቤተ መንግሥት ገቡ። ከቤተሰቦቻቸው ጋር የቤተ መንግሥት ህይወትን ገና ሀ ብለው ሲጀምሩ መኖሪያ ቤታቸው ዝናብ ሲጥል በማፍሰሱ አይጥ ወደሚንሸራሸርበት ቤት መዘዋወራቸውን የህይወት ታሪካቸው በተጻፈበት መጽሐፍ ላይ ገልጸዋል፡፡ የቤተ መንግሥቱ መኖሪያ ከአንድ የእንግሊዝ ባለሀብት መኖሪያ እንደማይበልጥ የሚናገሩት ዶክተር ነጋሶ፤ ታላቁ ቤተ መንግሥት ውስጥ አዲስ የፕሬዚዳንት መኖሪያ ቤት እንዲሰራ አዲስ ዲዛይን የወጣ ቢሆንም ሲጀምር እንደተስተጓጎለ ይገልጻሉ፡፡
ዶክተር ነጋሶ አሉ «እኔ ቤተ መንግሥት ብገባም ግቢው ሙሉ ለሙሉ የማዝበት አልነበረም፡፡»
የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሆነው ሲሠሩ የኢትዮጵያን አምባሳደሮች መሾም፣ የውጭ አገር አምባሳደሮች ሲመጡ መቀበል ፤የሥራ ጊዜያቸውን ሲያጠናቅቁ ደግሞ መሸኘት ነበር። መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ልዑካንን ማነጋገር ከአገሪቱ ጋር ጥሩ ግንኙነት እንዲመሰርቱ በማድረግ ጥረት አድርገዋል፤ ነገር ግን ብዙ ፈተናዎች ገጥሟቸዋል፡፡
ነጋሶ ስለ ሕይወታቸው በተጻፈው መጽሐፍ ራዕያቸውን ተናግረዋል፡፡ «የእኔ ራዕይ ኢትዮጵያ የነጻ ዜጎች አገር እንድትሆን ነው፡፡ የዴሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብቶች ሙሉ ለሙሉ የተከበረላቸው፣ የስልጣን ባለቤትነታቸው በምንም ዓይነት መንገድና ሁኔታ ያልተገደበ ዜጎች፣ አስተዳደራዊ፣ ህጋዊና ማህበራዊ አገልግሎቶችን በየትም ቦታ በሚገባቸው ቋንቋ የሚያገኙ ዜጎች፣ በየትምህርት ቤቱ ከአፍ መፍቻ በተጨማሪ ከሌሎች ጋር ለመግባባትና ለኑሮ ይረዱኛል የሚሉትን ቋንቋዎች ሁሉ በፍላጎታቸው የሚማሩበት ዕድል ያላቸው የነፃ ዜጎች አገር እንድትሆን ነው፡፡» እናም እኛም የእኚህን ቅንና ጀግና የአገር ባለውለታ ራዕይ የሚያሳካ ትውልድ እንዲፈጠር ምኞታችን ነው፡ ፡
ዶክተር ነጋሶ በጀርመን ሀገር ህክምና ሲከታተሉ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ከሰማን ቀናት ተቆጥረዋል። ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት ርዕስ ብሄር በመሆን በ1987 የተሾሙ ሲሆን፤ ለ7 ዓመታትም ማገልገላቸው ይታወሳል። በታሪክ ትምህርት ሦስተኛ ዲግሪያቸውን የያዙት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ፤ እንደ ምሁርነታቸው በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገራትም የተለያዩ ግልጋሎቶችን ሲሰጡ ቆይተዋል። በተማሩት ትምህርትም የኦሮሞን ባህል፣ ታሪክ እና እሴት የሚያንፀባርቁ እና የኢትዮጵያን አንድነት የሚያጠናክሩ የተለያዩ ጥናቶችን አካሂደዋል።
አዲስ ዘመን ሚያዚያ 27 ቀን 2011 ዓ.ም
በአብረሃም ተወልደ
ክፍት የሥራ ማስታወቂያ


የሥራ ቦታ ፡- ሳውዲ አረቢያ የቅጥር ቆይታ፡- 2 ዓመት ከ45 ቀን ዕድሜ፡- ከ21-45 የስልክ አቅርቦት ይመቻቻል፡፡ ኢንሹራንስና ትኬት በቀጣሪው ይሸፈናል፡፡ ኤጀንሲው ለሚሰጠው ማንኛውም አገልግሎት ምንም ዓይነት ክፍያ አያስከፍልም፡፡ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የታደሰ መታወቂያ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ በመያዝ ዘወትር በሥራ ሰዓት በኤጀንሲው ቢሮ በግንባር ቀርበው መመዝገብ ይችላሉ፡፡ አድራሻ፡- ሜክሲኮ ኬኬር ሕንፃ አጠገብ አይመን ሕንፃ ቢሮ ቁጥር 301/901 ስልክ ቁጥር፡-011-8547770/0911155596/0930406919 ሠብሊና በውጭ ሀገር ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ወኪል
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 28፣ 2011 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከጤና ባለሙያዎች ጋር ውይይት ካደረጉ በኋላ መፍትሄ ያገኙ ጉዳዮች ላይ ከጤና ሚኒስቴር የተሠጠ መግለጫ :--:

1. የሀኪሞችና የሌሎች ባለሙያዎች የስራ ምደባ በተመለከተ፦

• አሁን በስራ ላይ ያሉ ሀኪሞችንም ሆነ ሌሎች የጤና ባለሙያዎች የአለም የጤና

ድርጅት ባስቀመጠው ዝቅተኛ ስታንዳርድ (health work force density) መሰረት በሰራ ለይ ያሉት ባለሙያዎች ቁጥር ህብረተሰቡን ለማገልግል በቂ ስላልሆነ በሚቀጥሉት ኣመታት የሚመረቁ ሀኪሞችም ሆነ ሌሎች ባለሙያዎች መመደብ እንዲቻል ክልሎች በጀትና ተጨማሪ መደብ እንዲያስፈቅዱ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

• ከግንቦት ወር 2011ዓ.ም ጀምሮ በክልሎችና በዩኒቨርሲቲ ሆስፒታሎች ስፖንሰርነት 3ሺህ 800 የስፔሻላይዜሽን ትምህርት እየተከታተሉ የሚገኙ ሀኪሞች ደሞዝ፣ መደብና ጥቅማጥቅም በጤና ሚኒስቴር እንዲሸፈን በመወሰኑ ተጨማሪ 3ሺህ800 ሀኪሞችን በክልሎችና በዩኒቨርሲቲዎች ለመቅጠር ያስችላል፡፡

2. የስፔሻላይዜሽን ስልጠና በተመለከተ፦

• በግል ፈተና ወስደው መሰልጠን ለሚፈልጉ ባለሙያዎች የስፔሻላይዜሸን ትምህርት እንዲከታተሉ ተፈቅዷል፡፡

3. የሀኪሞችን የወጪ መጋራት በተመለከተ፦

• ከግንቦት ወር 2011ዓ.ም ጀምሮ ከዚህ ቀደም የትምህርት ማስረጃ ለማግኘት የሚከፈለው ብር 470ሺህ እንዲቀርና ሃኪሞችም እንደማንኛውም የመንግስት ዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎች በወጪ መጋራት ህግ መሰረት የሚስተናገዱ ይሆናል፡፡

4. ከፌደራል ተቋማት የትርፍ ሰዓት እና የጥቅማጥቅም ክፍያ ላይ የሚቆረጠውን ታክስ በተመለከተ፦

• በፌደራል ሆስፒታሎች ከዚህ በፊት ሲቆረጥ የነበረው የትርፍ ሰዓት እና የጥቅማጥቅም ክፍያ ታክስ ከግንቦት ወር 2011 ዓ.ም ጀምሮ በፌደራል መንግስት እንዲሸፈን ተወስኗል።

በተመሳሳይ እስከ አሁን ይሄንን ተግባራዊ ያላደረጉ ክልሎች በአጭር ጊዜ ጉዳዩን ወደ ክልል ካቢኔ አቅርበው እንዲያስወስኑ ስምምነት ለይ ተደርሷል።

5. የ ባለሞያ ካሪየር ስትራክቸርን በተመለከተ፦

• ከ2009 ዓ.ም ደሞዝ ጭማሪ ጋር ተያይዞ በፌደራል ሆስፒታሎች ከዚህ በፊት ወደ ጎን የነበረውን የካሪየር እድገት ከግንቦት 2011ዓ.ም ጀምሮ ወደ ላይ እንዲሆን ተወስኗል፡፡

በተመሳሳይ እስካሁን ይሄንን ተግባራዊ ያላደረጉ ክልሎች በአጭር ጊዜ ጉዳዩን ወደ ክልል ካቢኔ አቅርበው እንዲያስወስኑ ስምምነት ለይ ተደርሷል።

6. የጤና ተቋማትን ስታንዳርድ ማሻሻል በተመለከተ፦

• ከዚህ በፊት የተጋነኑ የሚመስሉ የግል ጤና ተቋም ለመክፈት ሲጠየቁ የነበሩ መስፈርቶች እንዲሻሻሉ ተደርጓል፡፤

ከግንቦት 2011ዓ.ም ጀምሮ ወደ ስራ የሚገባ ይሆናል፡፡

7. የተቀናጀ የቀዶ ህክምና ባለሙያዎችን የትምህርት እድል በተመለከተ፦

• ከመስከረም 2012 ዓ.ም ጀምሮ የተቀናጀ የቀዶ ህክምና ባለሙያዎች የትምህርት እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ካሪኩለም በመዘጋጀት ላይ ይገኛል፡፡

8. በግል የህክምና ትምህርት ቤቶች የሚማሩ የህክምና ተማሪዎችን በተመለከተ፦

• በግል የህክምና ትምህርት ቤት የሚማሩ የኢንተርን ሀኪሞች ትምህርት ቤቶቹ በሚሰጣቸው የጊዜ ገደብ የተደራጀ ሆስፒታል እስኪኖራቸው በመንግስት ሆስፒታሎች ትምህርታቸውን እንዲከታተሉና ወርሃዊ ደሞዛቸውንም የሚመደቡበት የመንግስት ጤና ተቋም እንዲከፍላቸው ተወስኗል፡፡

• ከግል የህክምና ትምህርት ቤቶች የተመረቁና የሚመረቁ ሀኪሞች እንዲሁም ሌሎች የጤና ባለሙያዎች ባሉት ክፍት መደቦች መቀጠር እንዲችሉ እድሉ ይመቻቻል።

• ከሀምሌ 2010 ዓ.ም ጀምሮ ከግል ህክምና ትምህርት ቤት የተመረቁ ሀኪሞች ከዚህ በፊት 179ሺህ ብር እንዲከፍሉ ወይም ሁለት አመት እንዲያገለግሉ ያስገደድ የነበረው መመሪያ እንዲቀር ተደርጎ የትምህርት ማስረጃቸው እንዲወስዱ ተደርጎአል።

9. የኢንተርን ሀኪሞችን ጥያቄ በሚመለከት፦

• ከላይ በተሰጡት መፍትሄዎች የተመለሱ ጥያቄዎች እንደተጠበቁ ሆነው ሌሎች በጤና ባለሞያዎች ለተነሱ ተጨማሪ ጥያቄዎች የጤና ሚኒስቴር በተዋረድ ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር፣ ከዩኒቨርሲቲዎችና ከዩኒቨረሲቲ ሆስፒታሎች ጋር በመሆን እንዲፈቱ ይደረጋል፡፡

10. በክልሎች እና በፌድራል ተቋማት እየተደረጉ የሚገኙት የተለያዩ የጤና ባለሞያ ጥቅማጥቅም ክፍያዎችን በተመለከተ፡

• በክልሎች እና በፌድራል ተቋማት እየተደረጉ የሚገኙት የተለያዩ የየጤና ባለሞያ ጥቅማጥቅም ክፍያዎች ወጥ እንዲሆኑ በ2005ዓ.ም በወጣው የጥቅማጥቅም መመሪያ መወሰኑ ይታወቃል።

ሁሉም ክልሎች ይሄ መመሪያ ተግባራዊ እንዲሆን በአጭር ጊዜ ጉዳዩን ወደ ክልል ካቢኔ አቅርበው እንዲያስወስኑ ስምምነት ላይ ተደርሷል።

በ2005ዓ.ም በወጣው የጥቅማጥቅም መመሪያ ላይ ያልተካተቱ የሙያ ዘርፎች የተጋላጭነት ክፍያን አስመልክቶ በአጭር ጊዜ እንዲካተቱ ይደረጋል፡፡

11. የጤና ፖሊሲን በተመለከተ፦

• ከህብረተሰባችን የጤና ፍላጎት እና የአለም ነባራዊ ሁኔታ ጋር የተጣጣመ የጤና ፖሊሲ እንዲኖረን ለማድረግ ነባሩ የጤና ፖሊሲያችን እንዲከለስ ተወስኖ የተለያዩ የጤና ባለሙያች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይቶች መደረጋቸው ይታወቃል፡፡

በተዋረድ በሚደረጉ ተጨማሪ ውይይቶች እንደተጠበቀ ሆኖ ማንኛውም የጤና ባለሙያ ፖሊሲው ላይ አስተያየት መስጠት እንዲችል በመከለስ ላይ የሚገኘው የፖሊሲ ሰነድ የጤና ሚኒስቴር የምረጃ መረብ (ዌብ ሳይት) ላይ ተጭኗል፡፡

12. ለጤናው ሴክተር ትኩረት ሰጥቶ ስለመስራት፦

• መንግስት ለጤናው ሴክተር የሚያሰፈልገውን ትኩረት መስጠቱን እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ለመጥቅስ ያክል የግዢ ስርዓቱን ማሻሻል አንዱና ዋነኛዉ ነው፡፡

እንደማሳያም ባለፈው አንድ አመት ውስጥ የመድሃኒትና የህክምና መሳሪያዎች ግዥ ፍጥነትና ጥራት ለማሻሻል ከተወሰዱት እርምጃዎች ውስጥ

የላቦራቶሪ መመርመሪያ መሳሪያዎች ማለትም ሄማቶሎጂ/ኬሚስትሪ/ጉሉኮሜትርና ሪኤጀንቶች/ኬሚካሎች ግዢ በፍሬምወርክ ስምምነት ከአውሮፓ እና አሜሪካ ድርጅቶች ጋር ውል ተገብቶ ዘመን አፈራሽ ማሽኖች ከድርጅቶቹ በነጻ እንዲቀርብ እና ሪኤጀንቶች/ኬሚካሎች ሳይቆራረጡ ከ3 እስከ 5 ዓመታት ማቅረብ እንዲችሉ ስምምነት ላይ ተደርሶዋል፡፡

በዚህ ስምምነት በመጀመሪያ ዙር ከተካተቱ 500 ተቋማት ውስጥ 50 ተቋማት ተጠቃሚ የሆኑ ሲሆን÷ 450 ተቋማት ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል፡፡

በቀጣይ አመት ሁሉንም ጤና ተቋማት እንዲያካትት ይደረጋል፡፡

ለ 2012 ዓ.ም የ 80 አይነት መድሃኒቶችን ግዢ በረጅም ግዜ የ ግዥ ፍሬም ወርክ ስምምነት እንዲፈጸም ተወስኗል።

• ባለፈው አንድ አመት ጊዜ ብቻ የጤና ሚኒስቴር ለጠቅላይ ሚኒስቴር ያቀረባቸው አምስት የበጀት ጭማሪ ጥያቄዎች ተፈቅደዋል፡፡ ከጸድቁት የበጀት ጭማሪ ጥያቄዎች መካከል፦

i. ለፌዴራል ሆስፒታሎች የትርፍ ሰዓትና ጥቅማጥቅም ክፍያዎች የሚቆረጠውን የስራ ግብር ለመሸፈን 70 ሚሊዮን ብር በወር

ii. ለ 3ሺህ 800 የስፔሻላይዜሽን ተማሪ ሀኪሞች ደሞዝና ጥቅማጥቅም የሚውል ግማሽ ቢሊዮን ብር፣

iii. ለ50 የማህበረሰብ ፋርማሲ መክፈቻ 50 ሚሊዮን ብር

iv. ለጥቁር አንበሳ እና ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታሎች ለመድሀኒት እንዲሁም ለህክምና መሳሪያዎች ግዢ እዳ የሚከፈል ከ ግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ እና
v. ለመድሀኒት እና ለህክምና መሳሪያዎች ግዢ የሚውል በእርዳታ ከምናገኘዉ ውጪ ቀድሞ ይመደብ ከነበረው ከ30 ሚሊዮን ዶላር ወደ የ130 ሚሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ከመንግስት በጀት በዚህ ዓመት ተፈቅዷል፡፡

• የምግብ፤መድሀኒት፤ጤና ተቋም እና የጤና አገልግሎት አስተዳደር እና ቁጥጥር ባለስልጣን (FMHACA) ተደራራቢ ሀላፊነቶች ወስዶ እየሰራ በመቆየቱ የሚፈለገውን ያክል ውጤት ማምጣት ባለመቻሉ በዚህ አመት በአዋጅ ወደ መድሀኒት እና ምግብ ቁጥጥር (FDA) እንዲቀየር ተደርጓል፡፡

13. የዩኒቨርስቲ ሆስፒታሎችን በተመለከተ፦

• እነዚህ ሆስፒታሎች በሳይንስና ከፍተኛ ሚኒስቴር ስር ባሉ ዩኒቨርሲቴዎች እንዲሚተዳደሩ ይታወቃል። በእነዚህ ሆስፒታሎች ለይ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት ከገንዘብ ሚኒስቴር፣ ከጤና ሚኒስቴርና ከሳይንስና ከፍተኛ ሚኒስቴር የተውጣጣ የባለሙያዎች ቡድን ተቋቁሞ የችግሮቹን መንስኤ እና መፍትሄ አጥንቶ በአጭር ግዚው ውስጥ የውሳኔ ሃሳብ ያቀርባል፡፡

ከእነዚህ በተጨማሪ የተነሱ ጥያቄዎችን እያየ የመፍትሄ ሃሳቦችን ለውሳኔ የሚያቀርብ ቡድን ከጠቅላይ ሚኒስቴርና ከጤና ሚኒስቴር እንዲሁም ከሌሎች የሚመለከታቸው የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ተቋቁሞ በአጭር ግዜ ውሳኔዎችን ያሳውቃል።#fbc
ሚያዝያ 27/2011 (05 May 2019) ...
Advert on Addis Zemen
Addis Ababa Water and Sewarage Authority ...
2 - ቦታዎች ልምድ ላላቸው
ሚያዝያ 27/2011 (05 May 2019) ...
Advert on The Ethiopian Herald
Addis Ababa University ..
2 - ቦታዎች ልምድ ላላቸው
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ያበደ ሰርግ:-) :-)
Crazy wedding
እንደዚህ አይነት ሰርግ ብትጠሩ ትሄዳላችሁ?
አደጋ ነው
ከጤና ሚኒስቴር የተሰጠ መግለጫ

በሚያዚያ 26 2011ዓ.ም ክቡር ጠቅላይ ሚንስትሩ ከጤና ባለሙያዎች ጋር ባደረጉት ስብሰባ ላይ ለተነሱ ጥያቄዎች መፍትሄ አግኝተዋል ካሏቸዉ መካከል የተወሰኑት ፤
.
1. የሀኪሞች እና የሌሎች ባለሙያዎች የስራ ምደባ በተመለከተ
.
- አሁን በስራ ላይ ያሉ ሀኪሞችንም ሆነ ሌሎች የጤና ባለሙያዎች የአለም የጤና ድርጅት ባስቀመጠው ዝቅተኛ ስታንዳርድ (health work force density) መሰረት በሰራ ለይ ያሉት ባለሙያዎች ቁጥር ህብረተሰቡን ለማገልግል በቂ ስላልሆነ በሚቀጥሉት ኣመታት የሚመረቁ ሀኪሞችም ሆነ ሌሎች ባለሙያዎች መመደብ እንዲቻል ክልሎች በጀት እና ተጨማሪ መደብ እንዲያስፈቅዱ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡
.
- ከግንቦት ወር 2011ዓ.ም ጀምሮ በክልሎች እና በዩኒቨርሲቲ ሆስፒታሎች ስፖንሰርነት 3800 የስፔሻላይዜሽን ትምህርት እየተከታተሉ የሚገኙ ሀኪሞች ደሞዝ፣ መደብ እና ጥቅማጥቅም በጤና ሚኒስቴር እንዲሸፈን በመወሰኑ ተጨማሪ 3800 ሀኪሞችን በክልሎች እና በዩኒቨርሲቲዎች ለመቅጠር ያስችላል፡፡
.
2. የስፔሻላይዜሽን ስልጠና በተመለከተ፡
- በግል ፈተና ወስደው መሰልጠን ለሚፈልጉ ባለሙያዎች የስፔሻላይዜሸን ትምህርት እንዲከታተሉ ተፈቅዷል፡፡
.
3. የሀኪሞችን የወጪ መጋራት በተመለከተ፡

- ከግንቦት ወር 2011ዓ.ም ጀምሮ ከዚህ ቀደም የትምህርት ማስረጃ ለማግኘት የሚከፈለው ብር 470,000.00 እንዲቀር እና ሃኪሞችም እንደማንኛውም የመንግስት ዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎች በወጪ መጋራት ህግ መሰረት የሚስተናገዱ ይሆናል፡፡
.
4. ከፌደራል ተቋማት የትርፍ ሰዓት እና የጥቅማጥቅም ክፍያ ላይ የሚቆረጠውን ታክስ በተመለከተ፡

- በፌደራል ሆስፒታሎች ከዚህ በፊት ሲቆረጥ የነበረው የትርፍ ሰዓት እና የጥቅማጥቅም ክፍያ ታክስ ከግንቦት ወር 2011 ዓ.ም. ጀምሮ በፌደራል መንግስት እንዲሸፈን ተወስኗል ። በተመሳሳይ እስከ አሁን ይሄንን ተግባራዊ ያላደረጉ ክልሎች በአጭር ጊዜ ጉዳዩን ወደ ክልል ካቢኔ አቅርበው እንዲያስወስኑ ስምምነት ለይ ተደርሷል።
.
5. የባለሞያ ካሪየር ስትራክቸርን በተመለከተ፡

- ከ2009 ዓ.ም ደሞዝ ጭማሪ ጋር ተያይዞ በፌደራል ሆስፒታሎች ከዚህ በፊት ወደ ጎን የነበረውን የካሪየር እድገት ከግንቦት 2011ዓ.ም ጀምሮ ወደ ላይ እንዲሆን ተወስኗል፡፡ በተመሳሳይ እስካሁን ይሄንን ተግባራዊ ያላደረጉ ክልሎች በአጭር ጊዜ ጉዳዩን ወደ ክልል ካቢኔ አቅርበው እንዲያስወስኑ ስምምነት ለይ ተደርሷል።
.
6. የጤና ተቋማትን ስታንዳርድ ማሻሻል በተመለከተ
ከዚህ በፊት የተጋነኑ የሚመስሉ የግል ጤና ተቋም ለመክፈት ሲጠየቁ የነበሩ መስፈርቶች እንዲሻሻሉ ተደርጓል፡፤ ከግንቦት 2011ዓ.ም ጀምሮ ወደ ስራ የሚገባ ይሆናል፡፡
.
7. የተቀናጀ የቀዶ ህክምና ባለሙያዎችን የትምህርት እድል በተመለከተ፡

- ከመስከረም 2012 ዓ.ም ጀምሮ የተቀናጀ የቀዶ ህክምና ባለሙያዎች የትምህርት እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ካሪኩለም በመዘጋጀት ላይ ይገኛል፡፡
.
8. በግል የህክምና ትምህርት ቤቶች የሚማሩ የህክምና ተማሪዎችን በተመለከተ፡

- በግል የህክምና ትምህርት ቤት የሚማሩ የኢንተርን ሀኪሞች ትምህርት ቤቶቹ በሚሰጣቸው የጊዜ ገደብ የተደራጀ ሆስፒታል እስኪኖራቸው በመንግስት ሆስፒታሎች ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ እና ወርሃዊ ደሞዛቸውንም የሚመደቡበት የመንግስት ጤና ተቋም እንዲከፍላቸው ተወስኗል፡፡
.
- ከግል የህክምና ትምህርት ቤቶች የተመረቁ እና የሚመረቁ ሀኪሞች እንዲሁም ሌሎች የጤና ባለሙያዎች ባሉት ክፍት መደቦች መቀጠር እንዲችሉ እድሉ ይመቻቻል።
.
- ከሀምሌ 2010 ዓ.ም ጀምሮ ከግል ህክምና ትምህርት ቤት የተመረቁ ሀኪሞች ከዚህ በፊት 179,000 ብር እንዲከፍሉ ወይም ሁለት አመት እንዲያገለግሉ ያስገደድ የነበረው መመሪያ እንዲቀር ተደርጎ የትምህርት ማስረጃቸው እንዲወስዱ ተደርጎአል።
.
9. የኢንተርን ሀኪሞችን ጥያቄ በሚመለከት፡

- ከላይ በተሰጡት መፍትሄዎች የተመለሱ ጥያቄዎች እንደተጠበቁ ሆነው ሌሎች በጤና ባለሞያዎች ለተነሱ ተጨማሪ ጥያቄዎች የጤና ሚኒስቴር በተዋረድ ከሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ፣ ከዩኒቨርሲቲዎች እና ከዩኒቨረሲቲ ሆስፒታሎች ጋር በመሆን እንዲፈቱ ይደረጋል፡፡
.
10. በክልሎች እና በፌድራል ተቋማት እየተደረጉ የሚገኙት የተለያዩ የጤና ባለሞያ ጥቅማጥቅም ክፍያዎችን በተመለከተ፡

- በክልሎች እና በፌድራል ተቋማት እየተደረጉ የሚገኙት የተለያዩ የየጤና ባለሞያ ጥቅማጥቅም ክፍያዎች ወጥ እንዲሆኑ በ2005 ዓ.ም በወጣው የጥቅማጥቅም መመሪያ መወሰኑ ይታወቃል። ሁሉም ክልሎች ይሄ መመሪያ ተግባራዊ እንዲሆን በአጭር ጊዜ ጉዳዩን ወደ ክልል ካቢኔ አቅርበው እንዲያስወስኑ ስምምነት ላይ ተደርሷል። በ2005ዓ.ም በወጣው የጥቅማጥቅም መመሪያ ላይ ያልተካተቱ የሙያ ዘርፎች የተጋላጭነት ክፍያን አስመልክቶ በአጭር ጊዜ እንዲካተቱ ይደረጋል፡፡
.
11. የጤና ፖሊሲን በተመለከተ፡

- ከህብረተሰባችን የጤና ፍላጎት እና የአለም ነባራዊ ሁኔታ ጋር የተጣጣመ የጤና ፖሊሲ እንዲኖረን ለማድረግ ነባሩ የጤና ፖሊሲያችን እንዲከለስ ተወስኖ የተለያዩ የጤና ባለሙያች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይቶች መደረጋቸው ይታወቃል፡፡ በተዋረድ በሚደረጉ ተጨማሪ ውይይቶች እንደተጠበቀ ሆኖ ማንኛውም የጤና ባለሙያ ፖሊሲው ላይ አስተያየት መስጠት እንዲችል በመከለስ ላይ የሚገኘው የፖሊሲ ሰነድ የጤና ሚኒስቴር የምረጃ መረብ (ዌብ ሳይት) ላይ ተጭኗል፡፡
.
12. ለጤናው ሴክተር ትኩረት ሰጥቶ ስለመስራት፡
-መንግስት ለጤናው ሴክተር የሚያሰፈልገውን ትኩረት መስጠቱን እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ለመጥቅስ ያክል የግዢ ስርዓቱን ማሻሻል አንዱና ዋነኛዉ ነዉ፡፡ እንደማሳያም ባለፈው አንድ አመት ውስጥ የመድሃኒት እና የ ህክምና መሳሪያዎች ግዥ ፍጥነት እና ጥራት ለማሻሻል ከተወሰዱት እርምጃዎች ውስጥ
.
* የላቦራቶሪ መመርመሪያ መሳሪያዎች ማለትም ሄማቶሎጂ/ኬሚስትሪ/ጉሉኮሜትር እና ሪኤጀንቶች/ኬሚካሎች ግዢ በፍሬምወርክ ስምምነት ከአውሮፓ እና አሜሪካ ድርጅቶች ጋር ውል ተገብቶ ዘመን አፈራሽ ማሽኖች ከድርጅቶቹ በነጻ እንዲቀርብ እና ሪኤጀንቶች/ኬሚካሎች ሳይቆራረጡ ከ3-5 ዓመታት ማቅረብ እንዲችሉ ስምምነት ላይ ተደርሶዋል፡፡ በዚህ ስምምነት በመጀመሪያ ዙር ከተካተቱ 500 ተቋማት ውስጥ 50 ተቋማት ተጠቃሚ የሆኑ ሲሆን 450 ተቋማት ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል፡፡ በቀጣይ አመት ሁሉንም ጤና ተቋማት እንዲያካትት ይደረጋል፡፡
* ለ2012 ዓ.ም የ 80 አይነት መድሃኒቶችን ግዢ በረጅም ግዜ የ ግዥ ፍሬም ወርክ ስምምነት እንዲፈጸም ተወስኗል።
.
- ባለፈው አንድ አመት ጊዜ ብቻ የጤና ሚኒስቴር ለጠቅላይ ሚኒስቴር ያቀረባቸው አምስት የበጀት ጭማሪ ጥያቄዎች ተፈቅደዋል፡፡ ከጸድቁት የበጀት ጭማሪ ጥያቄዎች መካከል፦
i. ለፌዴራል ሆስፒታሎች የትርፍ ሰዓት እና ጥቅማጥቅም ክፍያዎች የሚቆረጠውን የስራ ግብር ለመሸፈን 70 ሚሊዮን ብር በወር
.
ii. ለ3,800 የስፔሻላይዜሽን ተማሪ ሀኪሞች ደሞዝ እና ጥቅማጥቅም የሚውል ግማሽ ቢሊዮን ብር፣
.
iii. ለ50 የማህበረሰብ ፋርማሲ መክፈቻ 50 ሚሊዮን ብር
.
iv. ለጥቁር አንበሳ እና ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታሎች ለመድሀኒት እንዲሁም ለህክምና መሳሪያዎች ግዢ እዳ የሚከፈል ከ ግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ እና
.
V. ለመድሀኒት እና ለህክምና መሳሪያዎች ግዢ የሚውል በእርዳታ ከምናገኘዉ ውጪ ቀድሞ ይመደብ ከነበረው ከ30 ሚሊዮን ዶላር ወደ የ130 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ከመንግስት በጀት በዚህ ዓመት ተፈቅዷል፡፡
.
- የምግብ ፤ መድሀኒት ፤ ጤና ተቋም እና የጤና አገልግሎት አስተዳደር እና ቁጥጥር ባለስልጣን (FMHACA) ተደራራቢ ሀላፊነቶች ወስዶ እየሰራ በመቆየቱ የሚፈለገውን ያክል ውጤት ማምጣት ባለመቻሉ በዚህ አመት በአዋጅ ወደ መድሀኒት እና ምግብ ቁጥጥር (FDA) እንዲቀየር ተደርጓል፡፡
.
13. የዩኒቨርስቲ ሆስፒታሎችን በተመለከተ፡

- እነዚህ ሆስፒታሎች በሳይንስና ከፍተኛ ሚኒስቴር ስር ባሉ ዩኒቨርሲቴዎች እንዲሚተዳደሩ ይታወቃል። በእነዚህ ሆስፒታሎች ለይ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት ከገንዘብ ሚኒስቴር፣ ከጤና ሚኒስቴር እና ከ ሳይንስና ከፍተኛ ሚኒስቴር የተውጣጣ የባለሙያዎች ቡድን ተቋቁሞ የችግሮቹን መንስኤ እና መፍትሄ አጥንቶ በአጭር ግዚው ውስጥ የውሳኔ ሃሳብ ያቀርባል፡፡
.
**
ከእነዚህ በተጨማሪ የተነሱ ጥያቄዎችን እያየ የመፍትሄ ሃሳቦችን ለውሳኔ የሚያቀርብ ቡድን ከጠቅላይ ሚኒስቴር እና ከጤና ሚኒስቴር እንዲሁም ከሌሎች የሚመለከታቸው የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ተቋቁሞ በአጭር ግዜ ውሳኔዎችን ያሳውቃል።
ሚያዝያ 27/2011 (05 May 2019) ...
Advert on Addis Zemen
Ethiopian Parliament Office ...
3 - ቦታዎች በ0 - አመት 16 - ቦታዎች ልምድ ላላቸው
ሚያዝያ 27/2011 (05 May 2019) ...
Advert on Fortune
Addis International Bank SC ...
2 - ቦታዎች ልምድ ላላቸው