የ12ኛ ክፍል ውጤትን የተመለከተ መግለጫ!‼️
የ12ኛ ክፍል ውጤትን በተመለከተ በትምህርት ሚኒስትሩ ሚኒስቴር ዶክተር ጥላዬ ጌቴ፣ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ገ/እግዚአብሔር ምክትል ዳይሬክተሮች ዶ/ር ዘሪሁን ዱሬሳ እና አቶ መሳይ ደምሴ፣ እንዲሁም የየክልሎች የትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች የሆኑት ዶክተር ጌታሁን ጋረደው የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ፣ ዶ/ር ቶላ ባሪሶ የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ እንዲሁም ዶክተር ይልቃል የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች በተከታታይ ውጤቱን በተመለከተ በጋራበተላለፈው ውሳኔ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።
በዚሁም መሰረት በዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ፈተና ያጋጠመ ችግር መኖሩን በተለይ በደንብ ጥሰት ዙሪያ በማረጋገጫ የተያዘባቸው ተማሪዎች ውጤት መሰረዙ እና በደንብ ጥሰቱ ተሳታፊ የሆኑ አካላት በየደረጃው ተጠያቂ የሆኑበት ሁኔታን እንዳለ ሆኖ፤ ፈተናዎቹ ከሰጡባቸው ቀናት ሀሙስና አርብ ማለትም በ6 እና 7/10/2011ዓ.ም ከተሰጡት ፈተና ውጤቶች በተለየ ከቅዳሜና እሁድ በኋላ ሰኞ እና ማክሰኞ ማለትም በ10 እና 11 10/2011ዓ.ም በተሰጡት ፈተናዎች በግልጽ የታየ የውጤት ግሽበት መኖሩ በመረጋገጡ የዩንቨርስቲ መግቢያ መቁረጫ ነጥቡ በአራቱ የትምህርት ዓይነቶች ላይ መሰረት ያደረገ እንደሚሆን መወሰኑን ገልጸዋል፡፡
እነዚህም እንግሊዝኛ፣ ሒሳብ፣ አፕቲቲዩድና ፊዚክስ ለተፈጥሮ ሳይንስ ሲሆኑ እንግሊዝኛ፣ ሒሳብ፣ አፕቲቲዩድና ጂኦግራፊ ለማህበራዊ ሳይንስ ይሆናሉ፡፡ ይህም ሲሆን ተማሪዎች እንዲሁም የተማሪ ወላጆች ሊገነዘቡ የሚገባቸው ተማሪዎቹ ያስመዘገቡት ውጤት በመምህርነት ሙያ ለመማር ከመረጡ ተማሪዎች ውጪ ለዩንቨርስቲ መግቢያ ብቻ የሚያገለግልና የተፈጥሮና የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ተብለው ዩንቨርስቲ እንደሚገቡና ከአንድ ዓመት የፍሬሽማን ኮርሶች በኋላም በሚያስመዘግቡት ውጤት መሰረት የፈለጉትን የትምህርት ፊልድ መርጠው መማር የሚችሉ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
የተከሰተውን ግሽበት በተመለከተም የማጣራት ሂደቱን የሚያካሂድ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስቴሩ የሆነ ኮሚቴ መቋቋሙን የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ጌታሁን ጋረደው ያሳወቁ ሲሆን ተጠያቂው አካል አስተማሪና የማያዳግም እርምጃ የሚወሰድበት መሆኑን አሳውቀዋል፡፡ በመግለጫው ማጠቃለያም የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትሩ ዶ/ር ጥላዬ ጌቴ እንደገለጹት የመቁረጫ ነጥቡን በተመለከተ ከጸጥታ ጋር በተያያዘ ችግር የነበረባቸው አካባቢዎች የተፈተኑ ተማሪዎች በልዩ ሁኔታ የሚታይላቸው መሆኑንና በጥቂት ቀናት ውስጥ በኤጀንሲው የሚገለጽ መሆኑን እንዲሁም በታየው የውጤት ግሽበት ምክንያት የተያዙት የተማሪዎች ውጤቶች እንደሚለቀቅ ጨምረው አሳውቀዋል።
@የጉድ ገንፎ እያደረ ይፋጃል

ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ
ነሐሴ 29/2011 E.C (04 September 2019) G.C
Advert on Addis Zemen magazine
Madawelabu University
288 - ቦታዎች በ0አመት 50 - ቦታዎች ልምድ ላላቸው
ባሌ ሮቤ ከተማ የሚገኘው መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ መምህራን እና ቴክኒካል ረዳቶችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡ ለሁሉም አመልካቾች የመጀመሪያም ሆነ ሁለተኛ ዲግሪ ከታወቀ ተቋም የተመረቃችሁ ሆኖ ምዝገባው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከተለቀቀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት አዲስ አበባ (መገናኛ - ለም ሆቴል አካባቢ ከሚገኘው የአዲስ አበባ መሬት ልማት አስተዳደር ህንፃ ጀርባ) ባለው የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ጉዳይ ማስፈፀሚያ ቢሮ፣ ባሌ ሮቤ መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የሰው /ሀ/አ/ል/ዳይሬክቶሬት (ዋና ጊቢ አዲሱ ህንፃ G+3)፣ ጎባ ሪፈራል ሆስፒታል እና ሻሸመኔ ኩየራ ካምፓስ ሲሆን የሚመለስ ኦርጂናል ዶክመንት እና የማይመለስ ከሲቪ (CV) ጋር የተጣጣመ አንድ ፎቶ ኮፒ የተሟላ ማስረጃ በመያዝ በአካል ቀርቦ መመዝገብ ወይም ማስመዝገብ ይቻላል፡፡
በጨረሻው ገፅ ከ1-14 የተመለከቱትን ማሳሰቢያዎች በሚገባ ይመልከቱ፡፡
ማሳሰቢያ
1. ለሁለተኛ ዲግሪ/ Lecturer /አመልካቾች ውጤት ለወንዶች 3.50 እና ከዚያ በላይ፣ ለሴቶች 3.35 እና ከዚያ በላይ፤እንዲሁም የመጀመሪያ ዲግሪ ውጤታቸው ለወንድ 3.00 እና ከዚያ በላይ፣ ለሴቶች 2.75 እና ከዚያ በላይ ያለው/ላት፡፡ ለአካልጉዳተኞች 3.15 እና ከዚያ በላይ እንዲሁም የመጀመሪያ ዲግሪ ውጤታቸው 2.50፣ ለታዳጊ ክልልና አርብቶአደር አካባቢ 3.15 እና ከዚያ በላይ፤ እንዲሁም የመጀመሪያ ዲግሪ ውጤታቸው 2.50 እና ከዚያ በላይ፤ለሁሉም አመልካቾች የመመረቂያ ጽሑፍ B+ (Very Good) እና ከዚያ በላይ መሆን ይገባዋል፡፡
2. ለሁሉም ህክምና ዲግሪ /የሰውና የእንስሳ / 3.00 እና ከዚያ በላይ ሆኖ፤ ቢበዛ ከሁለት Fx የበለጠ ያለው አይስተናገድም፡፡
3. ለመጀመሪያ ዲግሪ/ Graduate Assistant or Assistant Lecturer/ አመልካቾች ውጤት ለወንድ 3.25 እና ከዚያ በላይ፣ ለሴት 3.00 እና ከዚያ በላይ፣ ለአካል ጉዳተኞች 2.75 እና ከዚያ በላይ፣ለታዳጊ ክልልና አርብቶአደር አካባቢ 2.75 እና ከዚያ በላይ፡፡
4. ለቴክኒካል ረዳት አመልካቾች ውጤት ለመጀመሪያ ዲግሪ 2.00 እና ከዚያ በላይ፣ በደረጃ III እና IV ለሚወዳደሩ የብቃት መረጋገጫ (COC) ሰርተፍኬት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ 5. የትምህርት ማስረጃቸው ከሃገር ውስጥ ትምህርት ተቋማት ከሆነ ኦፊሻል ትራንስክሪፕት ማስላክ የሚችሉና በውጭ አገራት ትምህርታቸውን የተከታተሉ ተወዳዳሪዎች የትምህርት ደረጃ አቻ ግመታ እና ሰነድ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡ 6. ከረዳት ፕሮፌሰር በላይ ማስታወቂያ በወጣባቸው መደቦች አመልካቾች መደቡ ክፍት ሆኖ ባለበት በማንኛውም ጊዜ ማመልከት ይችላሉ፡፡
7. ለሁለተኛ ዲግሪ አመልካቾች ዕድሜ ከ 45 ዓመት መብለጥ የለበትም፣ ፆታ አይለይም፡፡
8. ለአንደኛ ዲግሪ አመልካቾች ዕድሜ ከ 35 ዓመት መብለጥ የለበትም፣ ፆታ አይለይም፡፡
9. ደሞወዝ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ስኬል መሰረት ይሆናል ፡፡
10. የምዝገባ ቦታ፡- አዲስ አበባ (መገናኛ - ለም ሆቴል አካባቢ ከሚገኘው የአዲስ አበባ መሬት ልማት አስተዳደር ህንፃ ጀርባ) ባለው የመደወላቡ ዩኒቨርሲቲ ጉዳይ ማስፈፀሚያ ቢሮ፣ ባሌ ሮቤ መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ የሰው /ሀ/አ/ል/ዳይሬክቶሬት (ዋና ግቢ አዲሱ ህንፃ G+3)፣ ጎባ ሪፈራል ሆስፒታል እና ሻሸመኔ ኩየራ ካምፓስ በአካል በመቅረብ መመዝገብም ሆነ ማስመዝገብ ይቻላል ፡፡
11. የምዝገባ ቀን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ አንስቶ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ይሆናል፡፡
12. አመልካቾች ተገቢውን መስፈርት አሟልተው ማለፋቸውን ሲያረጋግጡ ከሚሰሩበት መስሪያ ቤት በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
13. የፈተና ቀን በውስጥ ማስታወቂያ እና በዩኒቨርሲቲው ዌብ ሳይት ይገለፃል፡፡
14. የስራ ቦታ ከተራ ቁጥር 1-97 ሮቤ ካምፓስ 98-147 ጎባ ካምፓስ እና 148-178 ሻሸመኔ ካምፓስ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0228902116/ 0116181964 ወይም የዩኒቨርሲቲ ዌብ ሳይት WWW.mwu.edu.et ይመልከቱ ፡፡
መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ባሌ-ሮቤ