Ethio Job Vacancy
45.7K subscribers
23.2K photos
63 videos
157 files
19.2K links
አዳዲስ እና ወቅታዊ የሥራ ቅጥር ማስታወቂያዎችን ከተለያዩ ጋዜጦችና ድረ ገጾች ለሥራ ፈላጊዎች መረጃ መስጠት ነው።
Post New Job vacancies to Who are looking jobs.
Group discussion https://t.me/+uGe3tVg5jF4yZjk0
Download Telegram
የጀርባ ሕመም
የጀርባ ሕመም እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለውን የኅብረተሰባችን ክፍል እያጠቃ የሚገኝ የሕመም ዓይነት ነው፡፡ በአብዛኛው ይህ ሕመም በዕድሜ የገፉ ሰዎች ላይ የተለመደ የነበረ ቢሆንም በአሁኑ ጊዜ ግን በወጣትነት የዕድሜ ክልል ባሉ ሰዎች ላይም እየተበራከተ ይገኛል፡፡
► የጀርባ ሕመም ለምን ይከሰታል?
የጀርባ ሕመም ከማንኛቸውም የሰው ጀርባን ከሚሰሩ የሰውንት ክፍሎች ሊነሳ ይችላል፡፡
እነዚህም፤
✔️ የጀርባ ጡንቻዎች መሳሳብ (መሸማቀቅ)
✔️ ከባድ ዕቃን ያለአግባብ ለማንሳት መሞከር
✔️ ድንገተኛ የሆነ ከፍተኛ እንቅስቃሴ
✔️ የዲስክ መንሸራተት
✔️ የመገጣጠሚያ ላይ ኢንፌክሽን
✔️ የአጥንት መሳሳት
► የጀርባ ሕመም ከዕለት ተዕለት የኑሮ ሁኔታችን ጋር ይያያዛል፡፡
✔️ ከባድ ዕቃን በመግፋት ወይንም በመጎተት
✔️ ከባድ ዕቃን በመሸከም ወይም በማንሳት
✔️ ለብዙ ሰዓት በመቆም
✔️ ለብዙ ሰዓታት አጎንብሶ መቀመጥ
✔️ ያለ ዕረፍት ለብዙ ሰዓታት መኪና ማሽከርከር
► የጀርባ ሕመምን እንዴት መከላከል ይቻላል?
✔️ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ፡- ኤሮቢክስ የሚባለውን የስፖርት ዓይነት መሥራት የሰውነታችንን አቅም ከመጨመር ባለፈ ክብደታችንን በመቀነስ የጀርባ ሕመም ይከላከላል፡፡
✔️ ሲጋራ ማጤስን ማቆም፡- ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ ሲጋራን የሚያጤሱ ሰዎች በከፍተኛ ሁኔታ ለጀርባ ሕመም ተጋላጭ ናቸው፡፡
✔️ የሰውንት ክብደት መቀነስ፡- የሰውነት ክብደታቸው የጨመረ ሰዎች የጀርባ ሕመም ይኖርባቸዋል፡፡
✔️ የተስተካከለ አቀማመጥ፡- በምንቀመጥበት ጊዜ ጀርባችንን የሚደግፍ እና እጃችንን የምናሳርፍበት ቀጥ ያለ አቀማመጥ መያዝ፡፡
✔️ የተስተካከለ አቋቋም፡- በምንቆምበት ጊዜ የሰውነት ክብደታችን በሁለቱም እግሮቻችን በእኩል መጠን እንዲያርፍ ማድርግ እና ቀጥ ብለን ሳንቆለመም መቆም፡፡
✔️ ክብደት ያላቸውን ዕቃዎች በአግባቡ ማንሳት፡- ክብደት ያላቸውን በምናነሳበት ጊዜ ክብደቱን ከወገባችን/ከጀርባችን ይልቅ በእግሮቻችን ላይ እንዲያርፍ ማድርግ ተገቢ ነው፡፡ ዕቃዎችን በምናንቀሳቅስበት ጊዜ ከመጎተት ይልቅ መግፋትተመራጭ ነው፡፡
✔️ ጫማ፡- የጀርባ ሕመም እንዳይሰማን የምንጫማቸው ጫማዎች ምቹ ሊሆኑ ይገባል፡፡
✔️ መኪና በምንሽከረክርበት ወቅት ጀርባችንን መደገፍ፡፡ ለረጅም ሰዓት የምናሽከረክር ከሆነ በየማሃሉ ከመኪና በመውረድ ሰውነትን ማንሳሰቀስና ዕረፍት መውሰድ ተገቢ ነው፡፡
✔️ የአልጋ ፍራሽ ምቾት፡- የምንተኛበት የአልጋ ፍራሽ ቀጥ ያለ መሆን አለበት፡፡
የጀርባ ሕመም ከባድ የሆኑ የጤና ችግሮች ምልክት ሊሆን ስለሚችል በቀላሉ ሊመለከቱት አይገባም፡፡በመሆኑም ከዚህ በታች የሚጠቀሱት ተጫማሪ ምልክቶች ካሉ ወደ ሕክምና ማዕከል በመሄድ መመርመር ያስፈልጋል፡፡እነዚህም፤
✔️ በድንገተኛ የመኪና አደጋ ወይንም መውደቅን ተከትሎ የመጣ የጀርባ ሕመም
✔️ ከወር በላይ የቆየ እና እየባሰ የመጣ የጀርባ ሕመም
✔️ በሕመም ማስታገሻ እና ዕረፍት በመውሰድ ለውጥ የማያመጣ የጀርባ ሕመም
✔️ ከወገብ በታች የመደንዘዝ ስሜት
✔️ ደም የቀላቀለ ሽንት መኖር
✔️ ከፍተኛ ትኩሳት መኖር እና ሆድ ሕመም መሰማት ናቸው፡፡
ዶክተር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር
በቤትዎ ሆነው ሊያከናውኑት የሚችሉትን ይህን ቀላል የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በዚህ አድራሻ ማግኘት ይችላሉ። [ http://honeliat.com/?p=471 ]
ጤና ይስጥልኝ
የሮዝመሪ (የጥብስ ቅጠል) ሻይ እንደሚሆን ያውቁ ኖሯል?
አሰራሩ
 አንድ መካከለኛ ኩባያ ውሃ ማላፍት
 ውሃው ከፈላ በኋላ ግማሽ የሻይ ማንኪያ የሮዝመሪ ቅጠል (ደረቅ ወይም እርጥብ መሆን ይችላል) መጨመር
 እሳቱን ቀንሰን ለ5 ደቂቃ ማንተክተክ እና ማውጣት
 ውሃውን ማጥለል እና የሚቻል ከሆነ ትንሽ ማር ጨምሮ መጠጣት
 ይሄንን ሻይ በቀን አንድ ጊዜ ብቻ እና በሳምንት ከሶስት ጊዜ በላይ እንዳንጠጣ ይመከራል፡፡
የሮዝመሪ (የጥብስ ቅጠል) ሻይ መጠጣት ለጤናችን ምን አይነት ጥቅም ይሰጣል?
1. ቆዳችን እንዳያረጅ ያደርጋል፡- በሮዝመሪ ሻይ ውስጥ የሚገኙት ፓይቶኬሚካልስ ቆዳችን እንዳይሸበሸብ ያደርጋሉ፡፡ በብጉር እና በፀሀይ ምክንያት ቆዳችን ላይ የሚፈጠሩ ጥቋቁር ምልክቶች እንዲጠፉ እና ፊታችን እንዲጠራ ይረዳል፡፡
2. የማስታወስ ችሎታን ያሳድጋል፡- በሮዝመሪ ሻይ ውስጥ የሚገኘው ካርኖሲክ አሲድ የተባለው ንጥረ ነገር የማስታወስ ችሎታችንን በማሳደግ እና የነርቮቻችንን ጤንነት በመጠበቅ የሚታወቅ ነው፡፡ እድሜያችን እየጨመረ በሄደ ቁጥር የሚፈጠረውን የመርሳት ችግር እና ከመርሳት ጋር ተያይዞ የሚመጣውን አልዛይመረስ በሽታ ለመከላከል የሮዝመሪ ሻይ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡
3. ካንሰርን ለመከላከል ይጠቅማል፡- በሮዝመሪ ሻይ ውስጥ የሚገኙት ሮዝማሪክ እና ካፊክ አሲዶች ካንሰርን ለመከላከል ይጠቅማሉ፡፡በተለይ ደግሞ ለትልቁ አንጀት ካንሰር፤ ለጡት ካንሰር እና ለደም ካንሰር መድሃኒት ሊሆን እንደሚችል የሚጠቁሙ ጥናቶች ብቅ ብቅ እያሉ ነው፡፡
4. የምግብ መፈጨትን ያፋጥናል፡- በምግብ አለመፈጨት፤ በሆድ መነፋት፤ እና በሆድ ድርቀት ለሚሰቃዩ ሰዎች የሮዝመሪ ሻይ ፍቱን መድሃኒት ሊሆን ይችላል፡፡ የሮዘመሪ ሻይ አንጀታችን በማረጋጋት የሆድ መነፋት እና ጋዝን ይቀንሳል፡፡ በተጨማሪም በውስጡ ካርነሲክ አሲድ ስላለው በአንጀታችን ውስጥ ያሉትን ጤናማ ባክቴሪያዎች ያበረታታል፡፡
5. የበሽታ መከላከል አቅማችንን ያሳድጋል፡- በሮዝመሪ ሻይ ውስጥ እንደ ቫይታሚን ሲ፤ ቫይታሚን ኤ፤ ፖታሲየም፤ ማግኒዚየም እና ካልሲየም የመሳሰሉ ለጤንነታችን ጠቃሚ የሆኑ እና የበሽታ መከላከል አቅማችንን የሚያዳብሩ ንጥረ ነገሮች ይገኛሉ፡፡ በተለይ ደግሞ ቫይታሚን ሲ የበሽታ መከላከል አቅማችንን ከማሳደጉ በላይ በባክቴሪያ እና በቫይረስ የሚመጡ በሽታዎችን ይከላከልልናል፡፡
6. የአይንን ጤና ይጠብቃል፡- በሳንፈርድ እና በርንሃም የምርምር ተቋሞች የተደረገ አንድ ጥናት እንዳሳየው ከሆነ በሮዝመሪ ሻይ ውስጥ ያለው ካርነሲክ አሲድ የተባለ ንጥረ ነገር የአይናችንን ጤና ይጠብቃል እንዲሁም ከእድሜ ጋር የሚመጣውን የአይን እይታ መቀነስ እነዲስተካከል ይረዳል፡፡
7. የሰውነት መቆጣትን ይቀንሳል፡- የሮዝመሪ ሻይ አንታይ ኢንፍላማቶሪ ነው፡፡ ማለትም በሰውነታችን ውስጥ የሚነሱ መቆጣቶችን/ህመሞችን ያስታግሳል፡፡ በተለይ ደግሞ በጡንቻዎቻችን፤ መገጣጠሚያዎቻችን እና በጅማቶቻችን ላይ የሚነሱ ህመሞችን ለማስታገስ እና ለማዳን ጠቃሚ ነው፡፡
8. የአፋችንን ጠረን ጥሩ ያደርግልናል፡- በአፋችን ውስጥ ባሉ ባክቴሪያዎች ምክንያት የአፋችን ጠረን መጥፎ ሊሆን ይችላል፡፡ የሮዝመሪ ሻይ መጠጣት ግን እነዚህን ባክቴሪያዎች ከአፋችን ውስጥ ያጠፋል፡፡ ስለዚህ የአፋችንን ጠረን እና የአፋችን ጤና ይስተካከላል፡፡
9. የስኳር መጠናችንን ያስተካክላል፡- የሮዝመሪ ሻይ ውስጥ ካምፊን፤ ካርኖሶል እና ሉቲሊን የተባሉ ንጥረ ነገሮች ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ንጥረ ነገሮች የልባችንን ጤና ከመጠበቅ ባሻገር በሰውነታችን ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን ያስተካክላሉ፡፡ በተጨማሪም የደም ግፊታችን እንዲስተካከል ያደርጋሉ፡፡
የሮዝመሪ የጎንዮሽ ጉዳት
 አንዳንድ ሰዎች ለሮዝመሪ አለርጂክ ሊሆኑ ስለሚችሉ መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ እንደ አስፕሪን ላሉ መድሃኒቶች አለርጂክ የሆነ ሰው ለሮዝመሪም አለርጂክ ሊሆን ይችላል፡፡
 የደም ግፊት መድሃኒቶችን፤ የደም ማቅጠኛ መድሃኒቶችን፤ የስኳር ህመም መድሃኒቶችን እና የልብ ህመም መድሃኒቶችን የሚወስዱ ከሆነ የሮዝመሪ ሻይ ከመጠጣቶ በፊት ሀኪም ማማከር ይኖርቦታል፡፡
 የሮዝመሪ ሻይ ለእርጉዝ ሴቶች እና ለሚያጠቡ ፍፁም የተከለከለ ነው፡፡
 የሮዝመሪ ሻይ የሚጥል በሽታ ላለባቸው ሰዎች አይመከርም፡፡ የነርቭ ወይም የአእምሮ መድሃኒቶችን የሚወስዱ ከሆነ የሮዝመሪ ሻይ ከመጠጣትዎ በፊት ሀኪም ማማከር ይኖርብዎታል፡፡
ለጤንነትዎ ሼር ያድረጉ
ምንጭ - መረጃ ለጤና
*ለሁሉም ይድረስ፦

በአካውንታችሁ ላይ, friend የሆኑ follow and Like አድርጋችሁ የምትከተሏቸው ሰዎች መካከል፦

1.የጥላቻ መልዕክት የሚያስተላልፉትን ለምሳሌ እውነትን የማጣጣል፥ የማዋረድ፥ የንቀት መልዕክት ሲያሰራጩ የነበሩትንና እያሰራጩ ያሉትን፣

2.ጎጠኝነት የሚሰብኩትን ለምሳሌ ብሔርን ከብሔር ሕዝብን ከሕዝብ የሚከፋፍሉትን፣

3.ያልሆነውን ሆነ እያሉ በተሳሳተ መረጃ የሚያወናብዱትን፣

4.የሆነውን እውነታ አልሆነም ብለው በሐሰት የሚከራከሩትን፣ ሰዎች unfriend, Unfollow, unlike በማድረግ ከአካውታችሁ ልታስወግዷቸው ይገባል። በተሳሳተ እና ባልሆነ መረጃ ጭንቅላታችሁን እረፍት እንዲያጣ አታድርጉት።

*እነዚህ ግለሰቦች ማንነታቸው፣ አድራሻቸው አይታወቅም። ነገር ግን የሚያሰራጩት ነገር ለአንድ ብሔር ወይንም ክልል ሕዝብ ተቆርቋሪ መስለው በመሆኑ ተጠንቀቁ!! ዋና አለማቸው ብሔርን ከብሔር መከፋል፥በሐሰተኛ መረጃ ማወናበድ፥ የሚወደዱ ሰዎችን ስም በማጥፋት ማስጠላትና በአጠቃላይ የአንድን ብሔር ወይንም ክልል ሕዝብ እረፍት እንዳይኖረው ማድረግ ዋነኛ አጀንዳቸው ነው። ሕብረሰባዊ እረፍት የሌለው ማህበረሰብ ደግሞ ተረጋግቶ መኖርና መስራት አይችልም። ሁሌም የፖለቲካ ሴራ በሚሉት ወጥመድ ተይዞ ሲንደፋደፍ መሽቶ ይነጋበታል።

*በተቻላችሁ መጠን እንዲህ አድርጉ፦

1.ትኩስ መረጃ ለማንበብ ታማኝና ማንነታቸው የሚታወቁ ሰዎችን Like and follow አድርጉ።

2.ታሪክም ሆነ ሃይማኖታዊ ጉዳይ ለማንበብ የመረጃ ምንጫቸው ትክክለኛ የሆኑና ማንነታቸው የሚታወቁ ሰዎችን ተከተሉ።

3.አጫጭር መረጃ ከሚለቁት ይልቅ ከባህልና ከታሪክ ጋር አዛምደው የሚጽፉትን ብትከተሉ እውቀታችሁን ታዳብራላችሁ። ለሁሉም ነገር ምክንያታዊ ትሆናላችሁ። ካለ ስሌት በስሜት ከሚነዱት ትጠበቃላችሁ።

*ምዕመናን ሆይ ሰምታችሁኛል አይደል? በስሜት የሚነዱትን ከአካውንታችሁ አስወግዱ። ሁሌም ጥላቻ የሚነዙትን Block አድርጉ። የተሳሳተ መረጃ የሚያሰራጩትን አባሩ። የፌስቡክ ቤታችሁን አጽዱ።
በቤታችሁ እንዲኖሩ መፍቀድ ያለባችሁ፦

=>ምክንያታዊ ጽሐፊዎች፣

=>እውነተኛ ታሪክ ጽሐፊዎች፣

=>እውነተኛ መረጃ አቀባዮች፣

=>እውነተኛ ሃይማኖታዊ ተንታኞች፣

=>በእውቀት የሚጽፉ ኢኮኖሚስቶች፣

=>በእውቀት የሚጽፉ ፖለቲከኞች ብቻ ይሁኑ። በዚህ መልኩ አካውንታችሁን እንድታደራጁ እጠይቃለሁ።

*በሚባረሩት ፈንታ አዲስ ሰው confirm ስትቀበሉ ሆነ ferind request ስትልኩ ፕሮፋይሉን በሚገባ መርምሩት። እውነት ይጽፋል አይጽፉም፣ የመረጃ ምንጩ ታማኝ ነው አይደለም፣ ምክንያታዊ ነው አይደለም፣ አዋቂ ነው አይደለም የሚሉትን በሚገባ ከአያችሁ በኋላ ተቀበሉት ወይንም ጓደኝነት ላኩለት። ከዛ ውጭ አጭበርባሪ፥ አጭቤ፥ እውቀት የሌለው፥ ቀኑን ሙሉ ሰው ሲፎግር የሚውል ከሆነ እዛው confirm ላይ እንዳለ delete በሉት። አለቀ!!
ሰላም ለሰው ዘር ሁሉ ይሁን።
ኢትዮጵያ በሕዝቦቿ ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
🙏🙏🙏💚💛
New Job vacancy!
ORDA
#New -Job vacancy!
ORDA
ሰኔ 27/2011 (04 July 2019)
Advert on The Ethiopian Herald
Humanwell Pharmaceutical Ethiopian PLC
1 - ቦታ ልምድ ላለው/ላላት
ሰኔ 27/2011 (04 July 2019)
Advert on Addis Zemen
Metal Industry Development Institiution
5 - ቦታዎች ልምድ ላላቸው
Ethiopian Airlines would like to invite qualified candidates for the following position.
Position: Junior Driver
Qualification Required:
A Minimum of 12th Grade Complete per old curriculum or 10th complete per new educational policy with a minimum of Taxi II/Dry I/ Public I/Auto Driving License with Minimum of Three Years Driving Experience in a known Organization.
Age-(18-35)years old.

Registration Date: July 8, 2019 – July 12, 2019.
Registration Place: Ethiopian Airlines Group, Recruitment & Placement Office situated inside the premises of Ethiopian Airlines Group headquarters.
Interested applicants must bring all original and copy of their supporting documents, including 6th /8th Grade Ministry Card and Kebele ID with copy & one passport size photograph when they come for registration on the dates stated above.
ሰኔ 27/2011 (04 July 2019)
Advert on Addis Zemen
Somail Region Bio Gas Dissemination Scale Up Program (NBPE)
2 - ቦታዎች ልምድ ላላቸው
ሰኔ 27/2011 (04 July 2019)
Advert on Addis Zemen
Ethiopian Roads Autority
24 - ቦታዎች በ0አመት
Specilly to MA holders