Ethio Job Vacancy
46.1K subscribers
23.2K photos
63 videos
157 files
19.5K links
አዳዲስ እና ወቅታዊ የሥራ ቅጥር ማስታወቂያዎችን ከተለያዩ ጋዜጦችና ድረ ገጾች ለሥራ ፈላጊዎች መረጃ መስጠት ነው።
Post New Job vacancies to Who are looking jobs.
Group discussion https://t.me/+uGe3tVg5jF4yZjk0
Download Telegram
#ዛሬም_ለማስታወስ_ያህል
አጓጊ ደመወዝ እና ብዛት ያላቸውን ሠራተኞች NGO / Sales ሌላም ተቋማት ላይ ማስቀጠር እንፈልጋለን በማለት ከሚያጭበረብሩ ሕገወጥ ኤጀንሲዎች ተጠንቀቁ።
አጭበርባሪ መሆናቸውን ከምታውቁባቸው መንገዶች መካከል
የማመልከቻ ዘዴ በቴሌግራም ወይንም በኢሜይል ያደርጉና ለሥራ ማስኬጅ ወይንም ለሥልጠና በሚል ከ400 ብር ጀምሮ እንድትከፍሉ ይጠይቋችኋል።
እሺ ይሁን ብላችሁ ከከፈላችሁ በኋላ ጠብቁ ከሳምንት፣ ከወር ወይንም ቀጣሪው ድርጅት ስለከሰረ ሌላ ቀጣሪ ተቋም እያፈላለግን ስለሆነ ታገሱን እንደውልላችኋለን ይሏችኋል።
ብትጠብቁ ብትጠብቁ ሥራ የለም አያስቀጥሯችሁም።
ይሔው ነው መጨረሻቸው።
በዚህ ምስኪን ስራ ፈላጊ የማይሰራ ግፍ/ሕገወጥ ተግባር/ የለም።
ወገኔ አንዳንድ የሥራ ማስታወቂያ ቻናሎች የሚለቁትን አጓጊ የኤጀንሲ ማስታወቂያ ተጠንቀቁ። ከዚህ በፊት ስማቸው A Agency ወይንም A አሠሪና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ የሚል ስያሜ ነበራቸው፤ ዛሬ ደግሞ A** PLC ሆነው መጥተዋል።
A** (የአጭበርባሪዎችን የመጀመሪያ ስያሜ) ያመለክታል።
በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የአጭበርባሪ ኤጀንሲዎችን ማስታወቂያ Promote ባለማድረግ ሥራ ፈላጊዎችን ከመጭበርበር እንታደግ ለማለት እወዳለሁ።
ሌሎች ጓደኞቻችሁ ከመሰል አጭበርባሪዎች እንዲጠነቀቁ #Share #Forward በማድረግ ይተባበሩ።