Ethio Job Vacancy
45.1K subscribers
23.2K photos
63 videos
156 files
19K links
አዳዲስ እና ወቅታዊ የሥራ ቅጥር ማስታወቂያዎችን ከተለያዩ ጋዜጦችና ድረ ገጾች ለሥራ ፈላጊዎች መረጃ መስጠት ነው።
Post New Job vacancies to Who are looking jobs.
Group discussion https://t.me/+uGe3tVg5jF4yZjk0
Download Telegram
#UPDATE

በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ከ24 ሺህ አለፉ!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 11,881 የላብራቶሪ ምርመራ 584 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ20 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 285 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 24,175 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 440 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 10,696 ናቸው።

አዳዲስ ወቅታዊ መረጃ በቴሌግራም ቻናል ይከታተሉ።

@citizensjouranalethiopia
@citizensjouranalethiopia
#UPDATE

የከፍተኛ ትምህርት ማስቀጠያ ቅድመዝግጅት እና የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ተግባራት አፈፃፀም ግምገማ መድረክ በጅማ ዩኒቨርስቲ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በመድረኩ በያዝነዉ አመት ትምህርት ለማስቀጠል እንደ ቅድመ-ሁኔታ የቀረቡ ሃሳቦች ናቸዉ በዉይይትና ግምገማ መድረኩ ላይ ሃሳብ ተሰጥቶባቸዉ እንደሚፀድቁ ይጠበቃል።

በዚህም:-

- በክፍል ዉስጥ የተማሪዎችን ቁጥር ከ25 እስከ 30 ማድረግ

- የመማሪያ ክፍሎች ከዚህ ቀደም ከሚይዙት የተማሪ ብዛት በግማሽ መቀነስ

- በአንድ መኝታ ክፍል ከ4 ያልበለጡ ተማሪዎችን መመደብ

- የመማር ማስተማር ሂደቱን በክፍል ዉስጥ ዉስን ግዜ አድርጎ ተማሪዎች አብዛኛዉን ግዜ በመኝታ ክፍላቸዉና በቤተ-መፅሐፍት እንዲያደርጉ ማመቻቸት

- የአንድ ክፍለ ግዜ ርዝመት እስከ 35 ደቂቃ እንዲሆን ማድረግ እና ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲረጋገጥ ከፌደራል

- ክልሎች እና እስከ ዞኖች ድረስ ካለዉ መዋቅር ጋር በቅንጅት መስራት እንደ ሀሳብ ቀርበዋል።

በዛሬው ዕለት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጉዳዩ ላይ እደደሚወያይና ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል።
Via TIKVAHETH