This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
most bautiful azan from the world
የፌደራል ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ ፍትሐዊ ነው።
በዚህ ገጽ በተደጋጋሚ ለማቅረብ እንደተሞከረው ሁሉ (ለተጨማሪ መረጃ ወረድ ብለው ይመልከቱ) ሐረር የሐረሪዎች ብቻ ሳትሆን የመላው ኢትዮጵያዊና የዓለም ህዝብ ቅርስ ናት። እንደሐረር ያሉ ጥንታዊና በህይወት ያሉ ከተሞች ቢበዙ አራት ናቸው። እነዚህ ቅርሶች ጠብቀን ለመጭው ትውልድ የማስተላለፍ ኃላፊነት አለብን። ኢትዮጵያ እንደ አክሱም፣ ላሊበላ፣ ነጃሺና ሐረር ያሉ ቅርሶች ባለቤት በመሆኗ ዕድለኛ ናትና ይህን ዕድሏን ወደ ገንዘብና ኃይል የምትቀይርበት ጊዜ እሩቅ አይሆንም ብዬ አምናለሁ።
ምንም እንኳን ሐረሪ እራሷን በራሷ እንድታስተዳድር ሐረሪዎች ብቻ ሳይሆኑ መላው የሐረር አካባቢ ኦሮሞዎችና ሱማሊዎች አጅግ ወሳኝ ትግል ያካሄዱ ቢሆንም የኢትዮጵያ ሽግግር መንግሥት አስፈላጊውን አምኖበት በሽግግር ቻርተሩና በሕገ መንግሥቱ ማስቀመጡ ትልቅ ውሳኔ ነበር።
ሐረሪ ክልል በአዎንታዊ እርምጃ (affirmative action) እውን መሆኗ ወደፊት እንደሐላላ ፣ ኮንሶ፣ ያሉ እስካሁን ትኩረት ያልተሰጣቸው ታሪካዊ ቅርሶቻን ልምድ እንዲቀስሙ የሚያስችል ነው። በበኩሌ ሐላላ አሁን ሰው ባይኖርበት እንኳን የዚያ አካባቢ ሰዎች ነን የሚሉ ሰዎች ሠመራ እንደተደረገው ሁሉ ሁኔታዎች ( ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መዋቅር) ተሟልተውላቸው እንዲሰፍሩ ቢደረግ ትልቅ ነገር ነበር።
ስለሆነም ፍርድ ቤቱ ሐረር ተጠብቃ ትቆይ ዘንድ ውሳኔ ማስተላለፉ ነገን ማየት ነው ብዬ አምናለሁ።