አ.አ የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን - AACAPRAC 🇪🇹
262 subscribers
580 photos
23 videos
45 links
Download Telegram
በህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽ የአስተዳደር ዘርፍ የ2017 በጀት አመት የግማሽ አመት እቅድ አፈጻጸም ገመገመ።
ግምገማውን የመሩት የኮርፖሬሽኑ የአስተዳደር ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ውብነት በላይ ሲሆኑ በዘርፉ ስር የሚገኙ የግዥ፣የፋይናንስ እና የሰው ሀብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬቶች የ6 ወር እቅድ አፈጻጸማቸውን አቅርበው ውይይት ተካሄዶበታል።
ባለፉት 6 ወራት በዘርፉ የነበረው አፈጻጸም ውጤታማና በጣም አበረታች እንደነበር የውይይቱ ተሳታፊዎች ጠቅሰዋል።
በቀጣይ ወራቶችም ከእስካሁኑ የበለጠ ውጤት ለማስመዝገብ በትጋት እና በከፍተኛ ተነሳሽነት መስራት እንደሚገባ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል።
በመጨረሻም በዘርፉ ስር በሚገኙ ዳይሬክቶሬቶች በስራ ላይ እየዋሉ በሚገኙ መመሪያዎች እና አሰራሮች ዙሪያ ለዘርፉ ሰራተኛች በሙሉ ግንዛቤ ለመፍጠር ተሞክሯል።
Follow Like, Share

🌐 Website
www.AACAPRAC.gov.et
👉FaceBook
fb.com/AACAPRAC
👉Instagram
instagram.com/AACAPRAC
👉Telegram
t.me/AACAPRAC
👉Titkok
www.Tiktok.com/@AACAPRAC
👉YouTube
www.youtube.com/@AACAPRAC
👉Twitter( X )
twitter.com/AACAPRAC
🥰1
የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን የስራ መሪዎች እና ሙያተኞች በኮርፖሬሽኑ የእቅድ እና በጀት ዳይሬከቶሬት አስተባባሪነት ከአዲስ አበባ ከተማ ቄራዎች ድርጅት ጋር የልምድ ልውውጥ አድርገዋል።
የልምድ ልውውጡ በፋይናንስ አስተዳደር ፣በግዥ እና ንብረት አስተዳደር ፣በሰው ሃብት ልማት እና አስተዳደር ፣በደንበኞች አያያዝ እና ገቢ አሰባሰብ ፣በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ እና ኮሙኒኬሽን፣በእቅድና በጀት ዝግጅት እና ግምገማ ፣ በኦዲት እንዲሁም በስነ-ምግባር እና ጸረ ሙስና ስራዎች ዙሪያ ያተኮረ ነበር።
በእለቱ ከኮርፖሬሽኑ የተውጣጡ የሚመለከታቸው ዳይሬክተሮች እና ሙያተኞች በቄራዎች ድርጅት ተገኝተው ያገኙት ልምድ ለስራቸው ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ጠቅሰው ያገኙትን ተሞክሮ ከተቋማቸው የስራ ባህሪ አንጻር እያጣጣሙ ለመተግበር እና ውጤት ለማምጣት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።
Follow Like, Share

🌐 Website
www.AACAPRAC.gov.et
👉FaceBook
fb.com/AACAPRAC
👉Instagram
instagram.com/AACAPRAC
👉Telegram
t.me/AACAPRAC
👉Titkok
www.Tiktok.com/@AACAPRAC
👉YouTube
www.youtube.com/@AACAPRAC
👉Twitter( X )
twitter.com/AACAPRAC
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እንኳን ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን!

መልካም በዓል!

የአዲስ አበባ ከተማ የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን
👍2
የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን ባለፉት ስድስት ወራት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት የሰራው ስራ አበረታች መሆኑ ተገለጸ ።
ጥር 20/2017 ዓ.ም

ኮርፖሬሽኑ የ2ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸም ከባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ ገምግሟል።ለውይይት መነሻ የሆነ ሰነድ የኮርፖሬሽኑ ዋና አማካሪ ዶ/ር ግርማ መንገሻ ያቀረቡ ሲሆን ውይይቱን የኮርፖሬሽኑ ዋና ሰራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ነጻነት ዳባ መርተውታል።

በከተማችን ፖርኮች፣ ኘላዛዎች በየጊዜው እየተስፋፋ እና እየዘመኑ እንደመጡ በተለይ ከኮሪደር ልማቱ ጋር ተያይዞ በርካታ መዝናኛ ቦታዎች መገንባታቸው እና ወደ ህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን መካተታቸው እና እነዚህ ፓርኮች ለህብረተሰቡ የላቀ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ የባለድርሻ አካላት ሚና ከፍተኛ እንደነበር ተጠቁሞ ያለፉት ስድስት ወራት አፈጻጸም አበረታች መሆኑ ተገልጿል።

ተሳታፊዎች ከመጡበት ተቋም አንጻር እሰካሁን ከኮርፖሬሽኑ ጋር በቅንጂት የተሰራው አበረታች መሆኑን ጠቅሰው በቀጣይነት የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ለማድረግ እና በቅንጅት ለመሰራት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ነጻነት ዳባ ባለፉት ስድስት ወራት በትስሰር ለተሰራው ስራ እና ለተገኘው ውጤት ባለድርሻ አካላትን አመሰግነዋል። አያይዘውም በከተማችን እየተፈጠረ ካለው ሁልንተናዊ እድገት ጋር በተለይ ከኮሪደር ልማቱ ጋር ተያይዞ የተፈጠረውን ለውጥ የሚመጥን የመዝናኛ አገልግሎት በማቅረብ ውጤታማ ለመሆን ሁላችንም ተቀናጅተን መስራት ይጠበቅብናል በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።