አ.አ የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን - AACAPRAC 🇪🇹
262 subscribers
580 photos
23 videos
45 links
Download Telegram
የ2017 በጀት ዓመት የ5 ወሩ እቅድ አፈጻጸም አበረታች መሆኑ ተገለጸ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን አመራር እና ሰራተኞች በ2017 በጀት አመት የ5 ወራት እቅድ አፈጻጸም ላይ ውይይት አድርገዋል ።

ለውይይት የተዘጋጀውን እቅድ አፈጻጸም ያቀረቡት የተቋሙ የእቅድ እና በጀት ሃላፊ አቶ ውብእሸት አደፍርስ ሲሆኑ የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ነጻነት ዳባ ውይይቱን መርተውታል፡፡

በውይይቱ ባለፉት 5 ወራት እቅድ አፈጻጸም ላይ የነበሩ ጥንካሬ እና እጥረቶች በዝርዝር ውይይት የተካሄደባቸው ሲሆን ጥንካሬዎችን በማስቀጠል ጉድለቶችን በማረም ውጤታማ ስራ መስራት እንደሚገባ ተመላክተዋል።

የኮርፖሬሽኑ አመራር እና ሰራተኛች እስካሁን ከተደረገው ጥረት በላይ በመትጋት የተሰጣቸውን ሃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡

በመጨረሻም የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ነጻነት ዳባ በላፋት ወራቶች የተከናወኑ ተግባራት አበረታች መሆናቸውን አንስተው አመራሩና ሰራተኛውን አመሰግነዋል።አያይዘውም ተቋሙ ከተሰጠው ተልኮ አንጻር አሁንም ብዙ መስራት ይጠበቅብናል ካሉ በኋላ በቀጣይ በሚተኮርባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ግንዛቤ ፈጥረው የስራ አቅጣጫ ሰጥተዋል።
Addis Ababa City Public Recreation Areas Adm.Corporation Official Page 🇪🇹

ህጋዊ ድረ ገፁን ቢከተሉ ቢወዱ ቢያጋሩ ያተርፋሉ!!
Follow Like, Share

🌐 Website
www.AACAPRAC.gov.et
👉FaceBook
fb.com/AACAPRAC
👉Instagram
instagram.com/AACAPRAC
👉Telegram
t.me/AACAPRAC
👉Titkok
www.Tiktok.com/@AACAPRAC
👉YouTube
www.youtube.com/@AACAPRAC
👉Twitter( X )
twitter.com/AACAPRAC