አ.አ የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን - AACAPRAC 🇪🇹
263 subscribers
580 photos
23 videos
45 links
Download Telegram
ጽዱ  ፣ውብ እና ማራኪ መዝናኛ ስፍራ ለሁላችን!
       የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር  የህዝብ   መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን  አመራር አና ሰራተኞች በሁሉም ፓርኮች የጽዳት ዘመቻ አካሄዱ።
      በቀጣይ ቀናቶች የሚከበሩ የመስቀል እና እሬቻ በአል ታዳሚዎች ወደ ፓርኮቻችን እንዲመጡ እና በአግባቡ እንዲስተናገዱ ለማድረግ የሚደረግ ቅድመ  ዝግጅቶች  እካል የሆነው  በተለይ ፓርኮችን  ጽዱ ውብ አና ማራኪ  የማድረግ  የጽዳት ዘመቻ በሁሉም ፓርኮች ዛሬ ተካሄዷል።
       በኮርፓሬሽኑ ስር ያሉ ፓርኮች በሙሉ ለመዝናናት፣ለሰርግ፣ለልደት፣ለምረቃ፣ለኮንሰርት፣ለኢግዚቢሽን.ለባዛር ወዘተ ምቹ አስተማማኝ እና በቂ ስፍራዎች ያሏቸው ሲሆን  ዘመናዊ እና ደህንነታቸው የተጠበቁ የህጻናት መጫዎቻዎች፣ውብ እና ማራኪ የሆኑ አረንጓዴ ስፈራዎች፣በጽሞና ዝግ ብለው የሚራመዱበት እና ንጹህ አየር የሚወሰዱበት ረጅም ፣የአማረና ምቹ የመናፈሻ መንገድ/ወክ ወይ/፣ ፋውንቴን ...ያሏቸውን  መዝናኛ ስፍራዎች ለጎብኝዎች ዝግጁ አድርጎ የሚጠብቃችሁ በመሆኑ በማንኛውም ጊዜ መጥታችሁ እንድትገለገሉባቸው ኮርፖሬሽኑ ግብዣውን ያስተላልፋል።
የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን 🇪🇹

🌐 Website
                  AACAPRAC.gov.et
👉FaceBook
                 fb.com/AACAPRAC
👉Instagram
                 instagram.com/AACAPRAC
👉Telegram
                 t.me/AACAPRAC
👉Titkok
                 Tiktok.com/@AACAPRAC
👉YouTube
                 youtube.com/@AACAPRAC
👉Twitter( X )
                 twitter.com/AACAPRAC
የጽዳት ዘመቻ በብሔረ-ጽጌ ፓርክ !
ጽዱ ፣ውብ እና ማራኪ ፖርክ ለሁላችን!
መስከረም 11/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር  የህዝብ   መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን  በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ከሳሪሰ ቀጠና ወረዳ 7,8,9,10 የመንገድ ጽዳት ሽርክና ማህበር ጋር በመተባበር  በብሔረ- ጽጌ ፖርክ የጽዳት ዘመቻ አካሄደ።
  የዘመቻው አላማ ፖርኩን የማጽዳት፣ ውብ እና ማራኪ የማድረግ  በተለይ በቀጣይ ቀናቶች በከተማችን በሚከበሩ የመስቀል እና እሬቻ በአል ታዳሚ ወገኖቻችን ወደ ፓርኩ መጥተው እንዲጎበኙ ፣በአግባቡ እንዲስተናገዱ እና በቆይታቸውም ረክተው እንዲመለሱ ለማድረግ የሚያስችል የቅድመ  ዝግጅት ስራ እንደሆነ ተግባሩም በሁሉም ፓርኮች እየተከናወን መሆኑን እና በቀጣይነትም ተጠናከሮ እንደሚቀጥል የኮርፖሬሽኑ ዋና ሰራ አስኪያጅ ወ/ሮ ነጻነት ዳባ ገልጸዋል።
   ፓርኩ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ልዩ ቦታው አደይ አበባ አካባቢ የሚገኝ ሲሆን  1955 ዓ. ም የመናፈሻ አገልግሎት መስጠት እንደጀመረ ይነገራል።

  መናፈሻው  የሚያምር መልካ-ምድራዊ ገጽታ ያለው ሆኖ  ደረጃውን የጠበቀ ውብ እና ማራኪ አረንጓዴ ስፍራም ተዘጋጅቶለታል፡፡
በግቢው ውስጥ በዲዛይን የተዘጋጀው/ቴራዞ የተነጠፈለት እግረኛ መንገድ ንጹህ አየር እየወሰደ ወክ ማድረግ ለሚፈለግ ተናፋሽ የተለየ ምቾት ይሰጣል፣በፋሲል ግንብ አምሳያ የተሰራው ባለ አንድ ፎቅ ህንጻ፣በግቢው መሃሉ አቋርጦ የሚያልፈው ትንሹ የአቃቂ ወንዝ፣እድሜ ጠገብ ሀገር በቀል ዛፎቹ፣ከ50 በላይ የተለያዩ ዝርያ ያላቸው ወፎች እና ጦጣዎቹ..…ለፓርኩ ጎብኝዎች የተለየ ስሜት ይፍጥራሉ፡፡
ፓርኩን በርካታ የከተማችን ነዋሪዎች ለሰርግ፣ለቀለበት፣ለልደት፣ለምርቃት፣ለእንስሳት ጉብኝት…እንዲሁም የተለያዩ ሁነቶችን ለማዘገጀት ይመርጡታል..
     
ርስዎም በማንኛውም ጊዜ በግልም ሆነ በቡድን መጥተው መዝናኛ ስፍራውን ይገልገሉበት ሲል  ኮርፖሬሽኑ ግብዣውን ያስተላልፋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን ህጋዊ
ድረ ገፁን ቢከተሉ ቢወዱ ቢያጋሩ ያተርፋሉ!!
Follow Like, Share

🌐 Website
                  www.AACAPRAC.gov.et
👉FaceBook
                 fb.com/AACAPRAC
👉Instagram
                 instagram.com/AACAPRAC
👉Telegram
                 t.me/AACAPRAC
👉Titkok
                 www.Tiktok.com/@AACAPRAC
👉YouTube
                 www.youtube.com/@AACAPRAC
👉Twitter( X )
                 twitter.com/AACAPRAC
YOU GO PARK