‹‹ በ2017 በጀት ዓመት ከ1.5 ሚሊዮን በላይ ጎብኚዎች ፓርኮቻችንን እንዲጎበኙ ጠንክረን በመስራት 121 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ እንሰበስባለን›› ወ/ሮ ፀሐይ ኪባሞ የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አሰኪያጅ ፡፡ 26/11/2016
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን አመራሮች ፣ዳይሬክተሮች እና ቡድን መሪዎች በ2016 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም እና በ2017 በጀት ዓመት እቅድ ላይ ውይይት አካሄዱ ።
ለውይይት የተዘጋጀውን እቅድ አፈጻጸም እና ለ2017 በጀት ዓመት የተያዘውን እቅድ ያቀረቡት የተቋሙ የእቅድ እና በጀት ሃላፊ አቶ ውብእሸት አደፍርስ ሲሆኑ የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ፀሐይ ኪባሞ እና የኢኮቱሪዝም ና ደንበኞች አገልግሎት ዘርፍ ም/ ኃላፊ አቶ መዝገቡ ይነበብ ውይይቱን መርተውታል፡፡
በ2016 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ላይ የነበሩ ጥንካሬ እና እጥረቶች በዝርዝር የተገመገሙ ሲሆን ጥንካሬዎችን በማስቀጠል ጉድለቶችን በማረም በ2017 በጀት ዓመት ሊተኮርባቸው የሚገቡ ግቦች፣ዒላማዎች እና ዝርዝር ተግባራት ተመላክተዋል።
በተለይ የመዝናኛ ቦታዎችን /የፓርኮችን መሰረተ ልማት የማሻሻል፣በስታንዳርዱ መሰረት የማስዋብ እና የማልማት፣ የኢኮቱሪዝም እና የደንበኞች አገልግሎት በማሻሻል የጎብኚዎችን ቁጥር የማሳደግ፣አዳዲስ የዱር እንስሳት የማስገባትና ጤና አጠባበቅን የማሻሻል ፣ የፓርኩን ደረጃ እና መስህብ የማሳደግ እንዲሁም የመዝናኛ ቦታዎች ክትትልና ድጋፍ በማጠናከር የሰራተኞችን የስራ ተነሳሽነት በማሳደግ የተቋሙን ገቢ በከፍተኛ ደረጃ መጨመር ላይ በትኩረት እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡
የጎብኝዎችን ፍላጎት መሰረት ያደረጉ አገልግሎቶችን በጥራት በማቅረብ እና የተለያዩ ሁነቶችን በማዘጋጀት ከ1,5 በላይ ጎብኚዎችን በመሳብ እንዲሁም ሌሎች የገቢ አማራጮችን በማስፋት 121,122,836 ብር /አንድ መቶ ሃያ አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ሃያ ሁለት ሽ ስምንት መቶ ሰላሳ ስድስት ብር /ለመሰብሰብ ታቅዷል፡፡
በውይይቱ የተሳተፉ አመራር እና የስራ ኃላፊዎች ዕቅዱ የሚያሰራና ተገቢ መሆኑን ገልጸው ለውጤታማነቱ የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡
የኮርፖሬሽኑ የበላይ አመራሮች እና የውይይቱ ተሳታፊዎች በብሔረ ጽጌ ፓርክ እየተከናወነ ያለውን ስራ ተዟዙረው ተመልክተዋል። በተለይ አመራሮቹ በፓርኩ እየተሰራ ያለውን የችግኝ ልማት ስራ አበረታች መሆኑን ጠቅሰው በቀጣይ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን ህጋዊ ድረ ገፅ 🇪🇹
Addis Ababa City Public Recreation Areas Adm.Corporation Official Page 🇪🇹
ህጋዊ ድረ ገፁን ቢከተሉ ቢወዱ ቢያጋሩ ያተርፋሉ!!
Follow Like, Share
🌐 Website
www.AACAPRAC.gov.et
👉FaceBook
fb.com/AACAPRAC
👉Instagram
instagram.com/AACAPRAC
👉Telegram
t.me/AACAPRAC
👉Titkok
www.Tiktok.com/@AACAPRAC
👉YouTube
www.youtube.com/@AACAPRAC
👉Twitter( X )
twitter.com/AACAPRAC

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
👍2