አ.አ የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን - AACAPRAC 🇪🇹
263 subscribers
580 photos
23 videos
45 links
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እንኳን ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን!

መልካም በዓል!

የአዲስ አበባ ከተማ የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን
👍2
የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን ባለፉት ስድስት ወራት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት የሰራው ስራ አበረታች መሆኑ ተገለጸ ።
ጥር 20/2017 ዓ.ም

ኮርፖሬሽኑ የ2ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸም ከባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ ገምግሟል።ለውይይት መነሻ የሆነ ሰነድ የኮርፖሬሽኑ ዋና አማካሪ ዶ/ር ግርማ መንገሻ ያቀረቡ ሲሆን ውይይቱን የኮርፖሬሽኑ ዋና ሰራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ነጻነት ዳባ መርተውታል።

በከተማችን ፖርኮች፣ ኘላዛዎች በየጊዜው እየተስፋፋ እና እየዘመኑ እንደመጡ በተለይ ከኮሪደር ልማቱ ጋር ተያይዞ በርካታ መዝናኛ ቦታዎች መገንባታቸው እና ወደ ህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን መካተታቸው እና እነዚህ ፓርኮች ለህብረተሰቡ የላቀ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ የባለድርሻ አካላት ሚና ከፍተኛ እንደነበር ተጠቁሞ ያለፉት ስድስት ወራት አፈጻጸም አበረታች መሆኑ ተገልጿል።

ተሳታፊዎች ከመጡበት ተቋም አንጻር እሰካሁን ከኮርፖሬሽኑ ጋር በቅንጂት የተሰራው አበረታች መሆኑን ጠቅሰው በቀጣይነት የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ለማድረግ እና በቅንጅት ለመሰራት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ነጻነት ዳባ ባለፉት ስድስት ወራት በትስሰር ለተሰራው ስራ እና ለተገኘው ውጤት ባለድርሻ አካላትን አመሰግነዋል። አያይዘውም በከተማችን እየተፈጠረ ካለው ሁልንተናዊ እድገት ጋር በተለይ ከኮሪደር ልማቱ ጋር ተያይዞ የተፈጠረውን ለውጥ የሚመጥን የመዝናኛ አገልግሎት በማቅረብ ውጤታማ ለመሆን ሁላችንም ተቀናጅተን መስራት ይጠበቅብናል በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።