አ.አ የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን - AACAPRAC 🇪🇹
263 subscribers
580 photos
23 videos
45 links
Download Telegram
በአዲስ አበባ ከተማ የኮተቤ መካነ እየሱስ ቅድመ መደበኛ፣የኘራይም፣የዊዝደም፣የስኘሪንግ ኖሌጂ እና የጀነሲስ አካዳሚ (ከ1020 በላይ) ተማሪዎች እና መምህራን በቀን 9/9/2016 ዓ.ም በአዲስ ዙ ፓርክ ትምህርታዊ ጉብኝት አካሄደዋል።በጉብኝቱ እንደተዝናኑ እና እንደተደሰቱ ተማሪዎቹ እና መምህራኑ ገልጸዋል።
👍2
የአዲስ አበባ ከተማ የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን ከእሺ ሚዲያ ጋር በጋር ለመስራት ተፈራረሙ ።

ግንቦት 10/2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ

እሺ ሚዲያ እና የአዲስ አበባ ከተማ የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን የፕሮሞሽን እና የኮምኒኬሽን ስራዎችን በጋር ለመስራት ዛሬ ግንቦት 10 2016 ዓ.ም ተፈራርመዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን በአሁን ወቅት አሥር የሚደርሱ የህዝብ መዝናኛ ቦታዎችና ፓርኮች በማስተዳደር ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል።

ኮርፖሬሽኑ እነዚህን የሕዝብ መዝናኛና ፓርኮችን በማልማትና በማስተዋወቅ በከተማዎ እየተካሄደ ያለውን ሁሉን አቀፍ ልማትና ገፅታ የመገንባት ስራ አንድ አካል በማድረግ ሰፊ የህብረተሰብ ንቅናቄ መድረክ ለማዘጋጀት አቅዷል፡፡

በዚህ የማነቃቂያ መድረክ መዝናኛ ቦታዎቹና ፓርኮቹን በሚሊዮን በሚቆጠሩ ነዋሪዎች እንዲጎበኙ እንዲሁም የንግዱ ማህበረሰብም ፓርኮቹን ለሕብረተሰብ አገልግሎት ለሚውሉ ተግባራት እንዲያለሙ ለማነቃቃት ብሎም ከፓርኮቹ የተሻለ ገቢ በማመንጨት ከተማ አስተዳደሩ ለወጠናቸው የልማት ተግባራትን እንዲደግፉ የማስቻል ዓላማ ተይዟል ተብሏል።

በዚህ የማነቃቂያ መርሐግብር ላይ የሰርግና ልደት ትዝታዎች የፎቶግራፍ አውደርዕይ፣ የዲፕሎማቶች እና አምባሳደሮች እንዲሁም የሚዲያ ባለሞያዎች ጉብኝት ፣ የሰርከስ ትርዒት ፣ የልጆች ጨዋታ ዝግጅቶችን ጨምሮ በርካታ መሰናዶዎች እንደተዘጋጀ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።
ተማሪዎችን የእረፍት ጊዜያቸው ወደ ፓርኮች እና መናፈሻዎች ወስዶ ማዝናናት  የመማር ማስተማር ሂደቱን ያጠናክራል ተነሳሽነትን ያሳድጋል ተበሎ በብዙ የትምህርት ባለሙያዎች ዘንድ ይታመናል።

ከዚህም በመነሳት በከተማችን ውስጥ የሚገኙ በርካታ  የግል እና የመንግስት ት/ት ተቋማት መምህራን ተማሪዎቻቸውን በመያዝ በኮርፓሬሽኑ በሚገኙ የዙ ፓርኮች መናፈሻዎች እና መዝናኛ ቦታዎች በአካል ተገኝተው ትምህርታዊ ጉብኝት ያካሂዳሉ ይዝናናሉ ከመምራኖቻቸው ጋር ይመካከራሉ::
 
በኮርፓሬሽኑ ስር የሚተዳድሩ  ፓርኮችና መዝናኛ ቦታዎች ለትምህርታዊ ጉብኝት፣ለመዝናኛነትም  ሆነ ለልዩ ልዩ ዝግጅቶች ምቹ ከመሆናቸውም በላይ የአገልግሎት ክፍያቸው ተመጣጣኝ በመሆኑ በብዙ ት/ቤቶች ዘንድ  ተመራጭ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል:

የኮርፖሬሽኑ አሁናዊ ሪፖርት እንደሚያሳየው ከ800ሺ በላይ የሃገር ውስጥ አና የውጭ ሃገር ጎብኝዎች ወደ ፓርኮቹ  በመመጣት ጎብኝተው፣ የማይረሳ ጊዜ አሳልፈው ተመልሰዋል።

በተለይ ደግሞ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር  ስር የሚገኙ በርካታ የመንግስት እና የግል ት/ቤቶች  በ10 ሽዎች የሚቆጥሩ ተማሪዎቻቸውን ይዘው  ወደ ፓርኮቹ በመምጣት ትምህርታዊ ጉብኝት  አድርገዋል። ተማሪዎቹ በፓርኮቹ ውስጥ ደስ የሚል ጊዜ ማሳለፋቸውን ተናግረዋል።
   
የከተማችን ነዋሪዎችም በማንኛውም ጊዜ በቡድንም ሆነ በተናጥል  ወደ  ፓርኮቻችን ብትመጡ የማይረሳ ጊዜ አሳልፋችሁ ደስ ብሏችሁ ትመለሳላችሁ።

    ለበለጠ መረጃ👇
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን ህጋዊ ድረ ገፅ 🇪🇹
Addis Ababa City Public Recreation Areas Adm.Corporation  Official Page 🇪🇹

ህጋዊ ድረ ገፁን ቢከተሉ ቢወዱ ቢያጋሩ ያተርፋሉ!!
Follow Like, Share

🌐 Website
                  www.AACAPRAC.gov.et
👉FaceBook
                 fb.com/AACAPRAC
👉Instagram
                 instagram.com/AACAPRAC
👉Telegram
                 t.me/AACAPRAC
👉Titkok
                 www.Tiktok.com/@AACAPRAC
👉YouTube
                 www.youtube.com/@AACAPRAC
👉Twitter( X )
                 twitter.com/AACAPRAC
የአዲስ አበባ ዪኒቨርሲቲ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (ASTU) ተማሪዎች ቅዳሜ በቀን 17/9/2016 ዓ.ም በእንጦጦ ፓርከ ተገኝተው ጉብኝት አና ቆይታ አደረጉ::

ተማሪዎቹ በቆይታቸው በጣም አንደተደሰቱ ገለፀው እንደዚህ ዓይነት ጉዞዎችን በፓርኮችና መዝናኛ ቦታዎች ማካሄድ ትውስታን ከማኖር ባሻገር መንፈስን ለማደስ ተማሪዎች አንዲቀራረቡ አንዲተዋወቁ እና አብሮነት አንዲጎለብት ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው መሆኑን ገልፀዋል::

የዩኒቨርሲቲው ተወካይም በጉዞው መደሠታቸውን ገልፀው ሌሎች በከተማው እና በአቅራቢያው የሚገኙ ዪኒቨርሲተዎች ተመሳሳይ ጉዞዎችን ቢያደርጉ ከፍተኛ ጠቀሜተ ያለው መሆኑን አሳውቀዋዋል።