ዳሰሳ አዲስ-Access Addis
8.87K subscribers
1.41K photos
131 videos
23 files
183 links
በዳሰሳ አዲስ ኅትመት እና ማስታወቂያ

ፊልም፣ ሙዚቃ፣ ኮንሰርት፣ የተለያዩ ኪነ-ጥበብ ቱርፋቶች፣ የታዋቂ ሰዎች ግለ ታሪክ እንዲሁም በወር አንዴ ጊዜ "ዙር ሰላሳ" የተሰኝች በመዝናኛው ዘርፍ ላይ ብቻ አትኩሮቷን ያደረገች ዲጂታል መፅሔት ተዘጋጅቶ ይቀርባል!

ለማንኛውም አስተያየት
👇

info@dasesaaddis.com

+251924312097

@InfoDasesaBot
Download Telegram
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለታላቁ የረመዳን ወር በሰላም አደረሳችሁ እያልን በዚህ ወር ዳሰሳ አዲስ ኅትመት እና ማስታወቂስ መልካም የፆም ጊዜ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።
ረመዳን ከሪም!
@AccessAddis
ዘመናዊ ቴአትር በኢትዮጵያ የተጀመረበት 100ኛ አመት ክብረ በዓል ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፣የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶ/ር ሂሩት ካሳ ፣የትምህርት ሚኒስትር ዶ/ር ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያን ጨምሮ አንጋፋ እና ወጣት የኪነጥበብ ባለሙያዎች በተገኙበት በሸራተን አዲስ ሆቴል ተከብሯል ።

በዝግጅቱ ላይ በቴአትር ያልተማረ የለም ያሉት ወ/ሮ አዳነች በቴአትር ኢትዮጵያውያን በጋራ ሆነው ታሪክ ሰርተዋል፤መስራታቸውንም ይቀጥላሉ ብለዋል።

በከተማዋ ያሉ ቴአትር ቤቶች ከፍተኛ በጀት ተመድቦላቸው ተገቢው እድሳት ተደርጎላቸው ለአገልግሎት እንዲበቁ ከማድረግ ባለፈ እየተሰሩ ባሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ውስጥ የአምፊ ቴአትር ቦታዎች እንዲካተቱ መደረጉን ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ጠቁመዋል ።

ኪነጥበብ ለሀገር ግንባታ ትልቅ ሚና አለው ያሉት ምክትል ከንቲባዋ የቴአትር እና የኪነ ጥበብ ስራዎች በሚፈለገው መንገድ እንዲጎለብት የከተማ አስተዳደሩ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።

ማምሻውን በተካሄደው መርሐግብር ቴአትር በኢትዮጵያ የ100 ዓመት ጉዞን የሚዘክሩ ዝግጅቶች ቀርበዋል።
@AccessAddis
አርቲስት መስፍን ጌታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እና በኢቢኤስ ቴሌቪዥን ሲቀርቡ የነበሩት ድራማዎች ደራሲና ዳይሬክተር የነበረው መስፍን ጌታቸው ዛሬ ማምሻዉን ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል፤

ለአርቲስቱ ቤተሰቦች፣ ወዳጅ እና አድናቂዎች ልባዊ መጽናናትን ይመኛል!
@AccessAddis
ዳሰሳ አዲስ-Access Addis
አርቲስት መስፍን ጌታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እና በኢቢኤስ ቴሌቪዥን ሲቀርቡ የነበሩት ድራማዎች ደራሲና ዳይሬክተር የነበረው መስፍን ጌታቸው ዛሬ ማምሻዉን ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል፤ ለአርቲስቱ ቤተሰቦች፣ ወዳጅ እና አድናቂዎች ልባዊ መጽናናትን ይመኛል! @AccessAddis
መስፍን ላለፉት ሁለት ወራት በኮቪድ ተይዞ በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ህክምናውን ሲከታተል የነበረ ሲሆን ካለፈው ሳምንት ወዲህ በፅኑ ህሙማን ክፍል ገብቶ ነበር።

አርቲስት መስፍን ጌታቸው በርካታ የጥበብ ስራዎችን በድርሰት፣ በአዘጋጅነት እና በትወና ለአገሩ ያበረከተ ሁለገብ ባለሞያ ነበር።

አርቲስቱ በኢትዮጵያ ሬድዮ ዝነኛ የነበረው የቀን ቅኝት ድራማ ደራሲ እንዲሁም በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያገኘው የሰው ለሰው ተከታታይ ድራማ ደራሲ እና ተዋናይ ነበር።

አርቲስት መስፍን ጌታቸው የዙምራ ፊልም፣ መንታ መንገድ የሬድዮ ተከታታይ ድራማ እና ሌሎችም ስራዎችን በተለያዩ የቴሌቪዥን እና የሬድዮ ጣቢያዎች ለህዝብ ማድረስ ችሏል።

አርቲስት መስፍን ጌታቸው ባለትዳር እና የሶስት ልጆች (የሁለት ሴት እና የወንድ ልጅ) አባት ነበር።

ዳሰሳ አዲስ ለአርቲስቱ ቤተሰቦች፣ ወዳጅ እና አድናቂዎች ልባዊ መጽናናትን ይመኛል!
@AccessAddis
በ50 ዓመቱ ኮቪድ-19 በሽታ ምክንያት ህይወቱ የተቀጠፈው ታዋቂው የኢትዮጵያ የጥበብ አርቲስት መስፍን ጌታቸውን የቀብር ስነ ስርዓት ቤተሰቦቹ፣ ወዳጆቹ፣ የስራ አጋሮቹ፣ ጓደኞቹ በተገኙበት ትላንት በቅድስት ስላሴ ካቴድትል ቤተ ክርስቲያን ተፈፅሟል።

እስክንድር ላቀው የአርቲስት መስፍን ጓደኛ ሲሆን መስፍን በታመመበት ወቅት የነበረውን ሁኔታ እንዲህ ገልፆታል፥ "የነበረው ጉጉት ድኖ ለመነሳት ነበር፥ ይህ ጊዜ አልፎ ብዙ ነገር ሰራለሁ የሚል ህልም ነበረው ድንገት ግን ተለይቶናል። አሁን የሚያሳዝነኝ እንደቀላል ነበር ነገሮችን ያያቸው ደግሞ የነበረበት ሁኔታ ጥሩ ነበር በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ብዙ ርብርብ ተደርጎለታል ፤ አለ የሚባለው ጥረት ሁሉ ተደርጎለታል ፤ እንደፈጣሪ ሆነና መስፍን ሄደ እንጂ እንደ ተደረገው ጥረት ቢሆን መስፍን አይሞትም" ነበር።

ሌላኛው የአርቲስት መስፍን ጌታቸው ጓደኛ አበበ ፈለቀ ፥"...ይሄ ምስክር ነው ጓደኛችንን ከ15 ቀን በፊት አውርቼዋለሁ ደህንና ነበረ ፤ አሞኝ ገባሁ እያለ ነው ገብቶ ሳይወጣ የቀረው። አንድ ሰው ጠንካራ ነኝ ፣ ወጣት ነኝ ፣ አይዘኝም ፣ እንደዚህ ነው የምበላው ሽንኩርት ነው፣ ቃሪያ ነው የምበላው ማለት አይሰራም፤ በሽታው የምር ነው ፤ የምናውቃቸው ከአጠገባችን ያሉ ሰዎችን እየነጠቀን ነው ፤ ስለዚህ ሁሉም ሰው ለራሱ፣ ለቤተሰቡ፣ ለዘመድ ለጓደኞቹ ሲል እራሱን መጠበቅ አለበት" ብሏል።

በዘመን ፣ በሰው ለሰው ፣ በሌሎችም የጥበብ ስራዎች የሚታወቀው አርቲስት መስፍን ጌታቸውን ባለትዳር እና የ2 ሴቶች እና የአንድ ወንድ ልጅ አባት ነበር።
@AccessAddis
ኮከቦቹን ያሰባሰበው ሙዚቃ ዛሬ ይለቀቃል

ኩኩ ሰብስቤ፣ ፍቅራአዲስ ነቃጥበብ፣ ዘሪቱ ከበደ፣ ሳያት ደምሴ፣ ራሄል ጌቱ፣
ጌታቸው ሃ/ማሪያም፣ ልጅ ሚካኤል፣ አስጌ ዴንነሾው፣ ኤፍሬም አስራት

በጥረታቸው ከፍ ብለው የታዩ ሴቶችን የሚያወድሰው ሙዚቃው ፣ በሀገር ሰላም ፣ ፍቅር እና አንድነት ፣ በሀገር ከፍ ብሎ መታየት ላይ ሁሉ የሴቶች ሚና ትልቅ መሆኑን ያነሳል።

ቅንብሩን ሚካኤል ሐይሉ (ሚኪ ጃኖ)
ዜማ ምህረታብ ደስታ
ተጨማሪ ዜማ ዘሪቱ ከበደ
ግጥሙን ናትናኤል ግርማቸዉ እና ፍርድያዉቃል ንጉሴ ፅፈውታል።

በUN WOMEN እና ሎሚ ሚዲያ ፕሮዱዩስ የተደረገው ሙዚቃው ዛሬ ከሰዓት የሚለቀቅ ሲሆን የሙዚቃ ቪዲዮ ደግሞ በሚቀጥለው ሳምንት ሮዕብ ይለቀቃል ተብሏል።
@AcceesAddis
እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ!
@AccessAddis
እንኳን ለ1442ኛዉ የኢድ አል ፊጥር በአል በሰላም አደረሰን! አደረሳችሁ!🌙
#ኢድ_ሙባረክ❤️
@AccessAddis
ሮፍናን 3 አዳዲስ ስራዎችን አወጣ።

ድምፃዊው ከረጅም ጊዜ በኃላ በሀገር ጉዳይ ላይ ትክረትን ያደረገ 3 መልክት አዘል ስራዎችን ለቋል።

ሮፊ ሦሥት የተሰኝ 3 የተለያዩ አዳዲስ ስራዎችን በራሱ ዩትዩብ ቻናል ለቋል።
@AccessAddis
ጁሊያን ማርሊ በጥቅምት ወር ወደ አዲስ አበባ ሊመጣ ነው።

እውቁ የሬጌ ንጉስ የቦብ ማርሊ ልጅ የሆነውን ጁሊያን ማርሊ በአይዞን ፋውንዴሽን ግብዣ በአዲስ አበባ የራሱንና የአባቱን የሙዚቃ ሥራዎች ሊያቀርብ ነው።

የሙዚቃ ዝግጅቱ በጥበብ እና መዝናኛ አማካኝነት ኢትዮጵያን ለማስተዋወቅ፤ በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ሰዎችን በአንድ ላይ ለማሰባሰብ እና በአለምአቀፍ ደረጃ የኢትዮጵያን በጎ ገጽታ ለመገንባት ያለመ ነው።

እንዲሁም የጥቁር ሕዝቦች ባህልን እና ሙዚቃን አጉልቶ በሚያሳየው ጥበብ ውስጥ ኢትዮጵያ በአለም ላይ ያላትን ስፍራ ለማሳየት ያለመ ነው።

በአይዞን ፋውንዴሽን የተዘጋጀው ይህ የሙዚቃ ዝግጅት በጥቅምት 06 ቀን 2014 ዓ.ም ጊዮን ሆቴል ይደረጋል ተብሏል፡፡
@accessaddis
ታላቁ የሙዚቃ ሰው ጥላሁን ገሠሠ በሕይወት ቢኖር ኖሮ ዛሬ 80 ዓመት የልደት በዓሉ ነበር።

ጥላሁን ለአራት አስርት ዓመታት በዘለቀ የሙያ ሕይወቱ የተጫወታቸው ዜማዎች የየዘመኑ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ሁነቶች ማኅደር ለመሆን በቅተዋል።

ጥላሁን በረጅሙ የድምፃዊነት ሕይወቱ፣ በቁጥር ብዙ ዘፈኖች ብቻ ሳይሆን፣ በብዙ ርዕሰ ጉዳዮችም ላይ ዘፍኗል። በሕይወት ዘመኑ የዘፈናቸውን ዘፈኖች ትክክለኛ ቁጥር ደፍሮ ለመናገር ያስቸግራል።
@AccessAddis
ድምፃዊ ዮሀና ሁለተኛ አልበሙን መልቀቁ አሳወቅ።

በሬጌ ስልት በማቀንቀን እና በመጀመሪያ አልበሙ ተወዳጅነት ያተረፈው ዮሀና ዕረፍት የተሰኝውን ሁለተኛ አልበም በራሱ የዩቲዩብ ቻናል መልቀቁን ነው የገለፀው።
@AccessAddis
አንጋፋው እና ተወዳጁ ድምፃዊ ቴዎድሮስ ታደሰ ጎዳና ወጣ።

በርካታ ዘመን አይሽሬ ስራዎችን ያበረከተው ድምፃዊ ቴዎድሮስ
በዋሽግተን በሚኖርበት ጊዜ ማንነታቸው በማይታወቅ ሰዎች ተደብድቦ ጉዳት እንደረሰበት እና ህክምና ተደርጎለት ወደ ቀድሞ ጤንነቱ ቢመለስም ከባለቤቱ ጋር በተፈጠረው አለመግባባት ጉዳዩ ከሽምግልና አቅም በላይ በመሆኑ ባለቤቱ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ወስዳው ነበር፣ ፍርድ ቤትም ቴዲ ሚስቱ እና ልጁ ጋር እንዳይደርስ ወስኗል ይላል ኢትዮጵካሊንክ።

ከዚህ በፊትም ጥሩ ያልነበረው የቴዲ ጤንነት አሁን ተባባሰ ይላል የኢትዮፒካሊንክ ዘገና።

አሁን በቅርቡ ከዲሲ ለቆ ሄዶ በኒውዮርክ ጎዳናዎች ላይ በአስከፊ ሁኔታ ላይ እንደሆነ ታይቷል ተብሏል።
@AccessAddis
ድምፃዊ ያሬድ ነጉ ከድምፃዊት ሚለን ኃይሉ ጋር ...

"አንዳንዴ ነፍስ ማረፊያዋን አታውቅም? እኔ ከሚለን ጋር በዚህ ደረጃ እቀራረባለሁ ብዬ አስቤ አላውቅም:: እውነታው ግን እንደሚታየው ነው:: በአንቺ ውስጥ የማላውቀው እኔን አግኝቻለሁ ፣በአንቺ ውስጥ ምግባርሽን ፣ባህልሽን፣ ፍቅርሽን፣ አስተሳሰብሽን ተካፍያለሁ ስለሁሉም አመሰግንሻለሁ ::

ሲል ድምፃዊት ያሬድ ሃሳቡን በይፋዊ ፌስቡክ ገፁ ሀሳቡን አስፍሯል።
"ከክሊፑ ቀረፃ ቀን በኋላ ያሬድ ነጉን አግኝቼው አላውቅም" ሚለን ኃይሉ

ድምፃዊ ያሬድ ነጉ ስለ ድምጻዊት ሚለን ሀይሉ ትላንት በይፋዊ ፌስቡክ ገፁ ያሰፈረውን መልዕክት ለእናት ማቅረባችን ይታወሳል።

ድምፃዊት ሚለን ዛሬ ከታዲያስ አዲስ ሰይፍ ጋር በነበራት ቆይታ ይህን ብላለች "ያሬድ ነጉን ከክሊፑ ቀረፃ በኋላ አግኝቼው አላውቅም ለምን እንደዛ ብሎ እንደለቀቀም ለመጠየቅ እና ማስተካክያ እንዲያደርግ በሶስቱም ስልክ ሲደወል ስልኩ ዝግ ነው፣ መኖሪያ ቤቱም ሄደን ነበር ቤት የለም።" በማለት ተናግራለች።
@AccessAddis
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የምትወጂውን ነገር ሳትሰስቺ ስለሰጠሽን፤ የላቀ ክብር እና ምስጋና ይገባሻል። 🙏
ባለ ቅኔዋ ድምፃዊት እጅጋየው ሽባባው (ጂጂ)
መልካም ልደት! 🎂🍾
@AccessAddis
የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ Maal Mallisaa አልበም ለ2022 የግራሚ ሽልማት እጩ ሆኖ ቀርቧል!

የቢልቦርድ መፅሄት በዛሬው እትሙ "የአለም ምርጥ የሙዚቃ አልበም- Best Global Music Album" በሚባለው ምድብ ለ2022 የግራሚ ሽልማት የአርቲስቱን አልበም በእጩነት አቅርቧል።

መፅሄቱ በአለም ዙርያ ላሉ የግራሚ ሽልማት ድምፅ ሰጪዎች የሚሰራጭ ሲሆን በዚህ እትም ላይ ከወጡ ሌሎች አርቲስቶች መሀል ድሬክ፣ ቢሊ ኤሊሽ፣ ሊል ናስ ወዘተ ይገኙበታል
Via:- Eliyas Mesert
@AccessAddis
ቴዲ አፍሮ ለ 'ኢትዮጵያ ወደ ፍቅር' ኮንሰርት አዘጋጁን አስር ሚሊየን ብር እንዲከፍለው ክስ አቀረበ

የቴዲ አፍሮ ክስ የካቲት 14 2012 ዓ.ም "ኢትዮጽያ ወደ ፍቅር" የተሰኘ ኮንሰርት አቅርቦ እንደነበር ይታወሳል።

በመስቀል አደባባይ የተዘጋጀውን ይህን ኮንሰርት ካዘጋጀው ከላየን ኢቨንትስ ጋር የሙዚቃ ኮንሰርቱን ላቀረብኩበት አስር ሚሊዮን ሊከፍለኝ የፅሁፍ ውል ስላደረግን ይክፈለኝ የሚል ነው ያቀረበው ክስ።
@AccessAddis